የእዣ ወረዳ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት

በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ ሲካሄድ የነበረው የብልፅግና ፓርቲ የ2 ዓመት ተኩል ኮንፈረንስ ተጠናቋል ።

=================

በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ ሲካሄድ የነበረው የብልፅግና ፓርቲ የ2 ዓመት ተኩል ኮንፈረንስ ተጠናቋል ።
በኮንፈንሱ የተገኙት የጉራጌ ዞን ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት መምሪያ ሀላፊ ወ/ሮ ትብለጥ እስጢፋኖስ እንደገለፁት ብልፅግና ፓርቲ ለሁለት አመት ከግማሽ ገደማ ባከናወናቸው ጠንካራ የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትና ተቋማት ግንባታ ሀገራችን ከአፍሪካና ከሌሎች የአለም ሀገራት ተወዳዳሪ እንድትሆንና ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና እየተጫወት ይገኛል።
ብልፅግና ፓርቲ በብዙ ፈተናዎች ውስጥ ሆኖ በርካታ ታምራዊ ለውጦች አስመዝግቦአል ያሉት ወ/ሮ ትብለጥ ለአብነትም የህዳሴ ግድብ ጨምሮ ትላልቅ ሀገራዊ ፕሮጀክቶችን በፍጥነትና በጥራት ማጠናቀቅ እንደሚቻል በተጎባር ጭምር ያሳየ ነው ብለዋል።
የእዣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘውዱ ዱላ በበኩላቸው ብልፅግና ፓርታ ሀገራችን መንታ መንገድ ላይ በቆመችበትና የውጭም የውስጥም ሀይሎች ግንባር በፈጠሩበት 210 ጀምሮ የሽግግር ወቅት በብቃት በመምራት በሁሉም ዘንድ ተቀባይነት በማግኘት በሂደቱም ትላልቅና ሊደፈሩ የማይቻሉ ሚመስሉ ሀገራዊ ልማትና መልካም አስተዳደር ተግባራቶች ያከናወነ ነው ብለዋል ።
ሀገራዊ ለውጦች እንደተጠበቁ ሆነው በወረዳውም ቢሆን ባለፉት ሁለት ዓመት ተኩል በማህበራዊ ፡ በኢኮኖሚያዊ እንዲሁም በመሰረተ ልማትና መልካም አስተዳደር ዘርፎች በርካታ ለውጦች እየተመዘገቡ ይገኛሉ ያሉት ዋና አስተዳዳሪው ለአብነትም ለ2132 ወጣቶች 11 ሚሊየን ብር ብድር በማመቻቸት የስራ እድል መፈጠሩ ፡ በከተሞች 10.2 ሄክታር መሬት በማዘጋጀት ለተለያዩ አገልግሎቶች መቅረባቸው ፡ 76.5 ኪ ሜ መንገድ በማህበረሰቡና በወረዳው መንግስት ድጋፍ እንዲሁም ባለሀብቶች በማስተባበር 50 ሚሊዮን ብር የሚገመት ስራ ላይ ማዋል መቻሉን ፡ ከ11.2 ሚሊየን ብር በላይ ማህበረሱቡና መንግስት በማስተባበር የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ስራዎች መሰራታቸውንም አብራርተዋል።
በግብርናው ዘርፍ 29167 ሄክታር በማረስ 2ሚሊየን 894ሺ 999 ኩንታል ማምረት መቻሉ ፡ 3111 እንስሳቶች በማዳቀል እንዲሁም 74ሺህ በላይ ዶሮዎች ለአርሶአደሩ ተሰራጭቷል ያሉት አቶ ዘውዱ በማህበራዊ ዘርፍ 131 የቅድመ አንደኛ ክፍል ጣቢያዎች ፡ ለረጅም አመታት ለቆዩት 2ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የወረዳው መንግስት ከ4ሚሊየን ብር በላይ በመደገፍ የማነቃቃት ስራ መስራቱን ፡ በጤናው ዘርፍም መከላከልና አክሞ ማዳንን መሰረት ያደረጉ በርካታ ስራዎች የተሰሩ ሲሆን የአገና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የማስጀመር እና ሌሎችም ህብረተሰቡን በተጨባጭ ተጠቃሚ ያደረጉ ተግባራቶች መሰራታቸውን ገልፀዋል ።
የእዣ ወረዳ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ተሾመ ስራኒ ብልፅግና ፓርቲ አሸንፎ የመጀመሪያ ጉባኤ በማካሄድ ህዝብና ሀገር ከፍ የሚያደርጉ የኢኮኖሚ ፡ የማህበራዊ ፡ የሰላምና ደህንነት እንዲሁም የአደረጃጀት ጉዳዮች ላይ በጥልቀት ገምግሞ አቅጣጫ በማስቀመጥ ላለፉት ሁለት ዓመት ተኩል ለተግባራዊነታቸው ሲተጋ ቆክቷል ብለዋል።
እንደ ወረዳውም ለረጅም ጊዜ ሲጠየቁ የነበሩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመመለስ ጥረት እየተደረገ ይገኛል ያሉት አቶ ተሾመ አሁንም ያልተፈቱ እና በፓርቲው የበላይነት መተግበር ያለባቸው ወደ ኋላ የቀሩ ተግባራቶች በተለይም ያልታረሱ መሬቶች የመስኖ ልማት ሜካናይዜሽን ፡ የተማሪዎች ውጤት ማሻሻልና በየደረጃው ፓርቲ የመትከል እና ጠንካራ ተቋማት የመገንባት ጉዳይ ተጠናክሮ የሚሰራበት እንደሆነም አስገንዝበዋል።
ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየትም ባለፉት ሁለት ዓመት ተኩል እንደ ሀገርም ብሎም እንደ ወረዳው ማህበረሰቡ ተጠቃሚ ያደረጉ በርካታ ስራዎች መከናወናቸው ጠቅሰው በቀጣይም ጠንካራና ቁርጠኛ አባላት በማፍራት የሀገር ብልፅግናን በማሳደጉ ሂደት የድርሻቸውን እንደሚወጡም ተናግረዋል።
በእለቱም የሁለት ዓመት ተኩል አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ የፀደቀ ሲሆን በኮንፈረንሱ መጨረሻም እዣ ወረዳን ወክለው ለክልል ጉባኤ የሚቀርቡ 10 አባላት ከተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ተመርጠዋል ሲል የዘገበው የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው።