የእዣ ወረዳ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት

በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ በደጌ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሳይንስ ሳምንት በተለያዩ ፕሮግራሞች ተከብሯል ።

በትምህርት ተቋማት የሳይንስና ቴክኖሎጂ ክበባትን በማጠናከር ተማሪዎች በአንድ ሀሳብ ያገኙትን እውቀት እና ማህበረሰብ ችግር ፈቺ የፈጠራ ሀሳቦች እውን የሚያደርጉ ምቹ ሁኔታዎች መፍጠር እንደሚገባ ተገለፀ ።

በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ በደጌ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሳይንስ ሳምንት በተለያዩ ፕሮግራሞች ተከብሯል ።

የጉራጌ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን መምሪያ ተወካይ አቶ ታሪኩ ንዳ በእለቱም ባደረጉት ንግግር ሀገራችን ከድህነት ለማውጣት እና ብልፅግናን ለማረጋገጥ የመንግስት ትኩረት አቅጣጫ ከሆኑት 5 ዘርፎች መካከል አንዱ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢኖቬሽን ነው ።

ተወካዩ አክለውም የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት የተቋቋመበት ዋና አላማ የሳይንስና ቴክኖሎጂ በማልማትና በሁሉም ስፍራ በስፋት በመጠቀም ፡ የሳይንሳና ፈጠራ ስራዎች በማበረታታት ችግር ፈቺ የሆኑ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ስራዎች ፈልቀው ፡ ለምተውና ተሸጋግረው የህብረተሰባችን ኑሮ ማሻሻል አንዱ መሆኑንም ጠቁመዋል ።

እንደ ዞኑ ብሎም እንደ እዣ ወረዳ በዚህ ዘርፍ በተለይም ከቅርብ አመታት ጀምሮ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ ነው ያሉት አቶ ታሪኩ በቀጣይም በትምህርት ቤቶች ለፈጠራ ስራ የሚሆን ግብዓቶች እንዲሟሉ በማድረግ ሳይንስ እንደ ባህል የሚቆጥር ማህበረሰብ እንዲፈጠር መስራት ያስፈልጋል ብለዋል ።

የእዣ ወረዳ የትምህርት ፅ/ቤት ም/ ሀላፊ አቶ አስቻለው ወልዴ እንደተናገሩት ትምህርት የአንድ ሀገር እድገትና ስልጣኔ በር ከፋች መሳሪያ እንደሆነና ይህም ሊሆን የሚችለው በጥናትና ምርምር ፣ በፈጠራና በቴክኖሎጂ የተደገፈ ለሀገር እድገትና ስልጣኔ ሁለንተናዊ ፋይዳ ያለው መሆን እንዳለበት ገልጸዋል ።

ሳይንስና ቴክኖሎጂ በፈጠራ ስራዎች ዘርፍ የፈጠራ አቅም ያለቸውን ተማሪዎች በመደገፍ በማበረታታትና በማብቃት ለማህበረሰቡ አግልግሎት የሚሰጡ የቴክኖሎጂ ውጤቶች መፍጠር መቻሉንም ምክትል ሀላፊው አመላክተዋል ።

በትምህርት ቤት የሳይንስና የቴክኖሎጂ ዘርፍ በማጠናከርና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተቀናጅቶ በመስራት ተመራማሪ ትውልድ እንዲፈጠር መረባረብ ይእንደሚገባም አቶ አስቻለው ተናግረዋል ።

የእዣ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት ሀላፊ ወ/ሪት ራሂማ ሙህታጅ በበኩላቸው በት/ቤቶች ውስጥ የማህበረሰቡ ችግር ፈቺ የሆኑ የፈጠራ ሃሳብ ያላቸው እጅግ በርካታ ታዳጊና ወጣቶች እንዲሁም መምህራን የሳይንስና ቴክኖሎጂ ክበባትን በማቋቋም ተማሪዎች በአንድ ሀሳብ ያገኙትን እውቀት እና ማህበረሰብ ችግር ፈቺ የፈጠራ ሀሳቦች እውን የሚያደርጉ ምቹ ሁኔታዎች መፍጠር ፡ ማበረታታትና ማገዝ ይገባል ብለዋል።

እንደ ወረዳው 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች በእውቀት የበለፀገ ፡ በስነ ምግባር የታነፀ ሀገር ተረካቢ ዜጋ በማፍራት ሃላፊነታቸው እየተወጡ የሚገኙ ዘመናትን የተሻገሩ ብዙ ሙህራንን ያፈራና ለሀገር ያበረከተ ባለውለታ ትምህርት ቤቶች መኖራቸውንም ሀላፊዋ ጨምረው ገልፀዋል ።

በዛሬው ወረዳዊ የሳይንስ ሳምንት አከባበር በርካታ የፈጠራ ስራዎች ቀርበዋል ያሉት ወ/ሪት ራሂማ ይህም የእርስ በርስ ልምድ ልውውጥ በማድረግ ከፍተኛ ተነሳሽነት የፈጠረ በመሆኑ ለተዘጋጀበት የደጌ ሁለቱኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራንና ተማሪዎች ከልብ ምስጋና አቅርበዋል።

በእለቱም የተማሪዎች የፈጠራ ስራዎች ፡ የጥያቄና መልስ ውድድር ፡ ድራማና ስነፅሁፎች ለታዳሚ የቀረቡ ሲሆን በ2016 ዓም ወረዳዊ ውድድር ላይ የላቀ የፈጠራ ስራ ያቀረቡት መምህራንና ተማሪዎች ፡ በዛሬው ፕሮግራም የነቃ ተሳፎ ያደረጉ ተማሪዎች የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቷል ሲል የዘገበው የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው ።