የእዣ ወረዳ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት

በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ 20ኛው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን ምክንያት በማድረግ ወረዳዊ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተደረገ ።

በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ 20ኛው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን ምክንያት በማድረግ ወረዳዊ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተደረገ ።

ህዳር 2ቀን 2018 ዓ.ም

በእለቱም የእዣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘውዱ ዱላ እንዳሉት የማስ ስፖርት ከአካላዊ እንቅስቃሴ ባሻገር ለአብሮነት እና ወንድማማችነት ያለው ድርሻ የጎላ በመሆኑ ስፖርቱን ማደበር የሚገባ ሲሆን ተነቃቅሶ ስፖርትን መስራት በማህበረሰቡ ዘንድ ሊለመድ የሚገባው ተግባር ነው ብለዋል።

የእዣ ወረዳ ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ተሾመ ስራኒ የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ማዳበር ጤናን ከማስጠበቅ አኳያ በቀን ውስጥ ለምናደርገው የስራ እንቅስቃሴ ንቁ እንድንሆን የሚያደርግ በመሆኑ ሊዳብር የሚገባ ሲሆን ዛሬ 20ኛው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን ምክንያት በማድረግ የተካሄደው ወረዳዊ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በሌሎችም ጊዜያቶች ተጠናክሮ መቀጠል አለበትም ብለዋል።

የእዣ ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ፍቅሬ ነሪ በበኩላቸው ማስ ስፖርት ጤንነታችን ለመጠበቅ እና የእርስ በርስን ትውውቅን ለማዳበር ያለው አስተዋዕጾ የላቀ በመሆኑ ይበል የሚያሰኝ በመሆኑ ፕሮግራም በወረዳው በሁሉም ቀበሌዎች ተጠናክሮ ይቀጥላልም ብለዋል።

በዛሬው እለት ከጠዋቱ 12:00 ሰአትጀምሮ የወረዳ አመራሮችን ጨምሮ ሁሉም የወረዳችን ማህበረሰብ ያሳተፈ ማህበር አቀፍ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተዳካሂዷል።