




==============================
ተጋላጭ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎችና አረጋውያን በመርዳትና ለመንከባከብ ሁለም ባለድርሻ አካላት የበኩሉን ሊወጣ እንደሚገባ የእዣ ወረዳ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳዮች ፅ/ቤት አስታወቀ ።
ፅ/ቤቱ በተለያዩ ጉዳዩች ዙሪያ ለባለድርሻ አካላት ስልጠና ሰጥቷል ።
በእለቱም የእዣ ወረዳ ም/አስተዳዳሪና የትምህርት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ተጠምቀ በርጋ እንደገለፁት በተለያዩ ኢኮኖሚና ማህበራዊ ችግሮች የተጋለጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ሁሉም በየአካቢው ዘላቂነት ባለው መልኩ እንዲደገፉ ማድረግ ይገባል።
እንደ ወረዳው በተለያዩ ምክንያቶች ማህበራዊ ችግሮች ተጠቂ የሆኑ አረጋዊያን ፡ የአካልና አዕምሮ ጉዳተኞች ፡ ወላጆቻቸው በተለያ ምክንያት ያጡ ህፃናት በድህነት ምክንያት ለበሽታና ለልመና የተጋለጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ እንዲያገኙ በተለያየ መልኩ ሰፊ ስራ እየተሰራ ነው ያሉት ም/አስተዳዳሪው በቀጣይም ይህንኑ በተጠናከረ እና በዘላቂነት ሁኔታ ለማስቀጠል በተለይም በቀበሌ ደረጃ የመረጃ አሰጣጥና ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው የህብረተሰብክፍሎች በአግባቡ ከመለየት አንፃር ጠንካራ ስራ መስራት ይጠይቃልም ብለዋል።
ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችል ወጥነት ያለው የግንዛቤና ንቅናቄ ማስጨበጫ ስራዎችን በማከናወን የወንጀል ድርጊትን በመሰረታዊነት መቀነስ እንደሚገባም አቶ ተጠምቀ አሳስበዋል።
የእዣ ወረዳ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳዮች ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ሲሳይ አለሙ በበኩላቸው እንደገለፁት ተቋሙ ከሚያከናውናቸው ተግባራቶች አንዱ የሆነውን የህብረተሰቡ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮችን በመቀነስ ዜጎች ከተጋላጭነትና ከጉስቁልና ህይወት ለመታደግ የሚያስችሉትን ስራዎችን በመስራቱ በዘርፉ እንደ ወረዳው በተለያየ ሁኔታ ተጋላጮችን በመለየትና ችግሮቻቸውን እንዲፈቱ በርካታ እንቅስቃሴዎች በመደረግ ላይ ይገኛሉ ብለዋል ።
በተለያየ መልኩ የሚፈጠሩ ህገ -ወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችል ወጥነት ያለው የግንዛቤና ንቅናቄ ማስጨበጫ ስራዎችን በማከናወን የወንጀል ድርጊትን በመሰረታዊነት ለመቀነስ የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑንም ሀላፊው አክለው ተናግረዋል።
አካል ጉዳተኞችና ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎች ተደግፈው ከችግሮቻቸው ተላቀው በሀገር ኢኮኖሚ ላይ የበኩላቸው አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ቅንጅታዊ አሰራር የሚጠይቅ በመሆኑ ሁሉ በየደረጃው የድርሻውን መወጣት እንዳለበትም አቶ ሲሳይ መልዕክት አስተላልፈዋል ።
በእለቱም በፅ/ቤቱ ባለሙያዎች የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰነዶች ቀርበው ሰፊ ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን ሰው ለመርዳት ሰው ብቻ በቂ መሆኑን በመገንዘብ በተለያዩ መልኩ ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ለመርዳት ዝግጁ መሆናቸውንም ተሳታፊዎች በአስተያየታቸው ገልፀዋል ሲል የዘገበው የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው።






