
==================================
የህብረት ስራ ማህበራት አሰራርና አደረጃጀት በማጠናከርና በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለይቶ በመፍታት የህብረተሰቡ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት መሰራት እንደሚገባው ተገለፀ ።
በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ በህብረት ስራ አደረጃጀትና አስተዳደር መመሪያ ፡ በሂሳብ አያያዝ ፡ የአፈር ማዳበሪያ አቅርቦትና ስርጭት እንዲሁም ፋይናንስ አስተዳደር ዙሪያ ስልጠና የተሰጠ ሲሆን በፅ/ቤቱ 9ወር አፈፃፀምና ዜጎች ቻርተር ዙሪያ ለሁለት ተከታታ ቀናት ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተደርጓል ።
የእዣ ወረዳ ህብረት ስራ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ፀጋዬ ደምስ እንደገለፁት የህብረት ስራ ማህበራት አሰራርና አደረጃጀት በማጠናከርና በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለይቶ በመፍታት የህብረተሰቡ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት መሰራት አለበት ።
ያደጉት ሀገራት መነሻቸውና የእድገታቸው መሰረት መሰረታዊ ህብረት ስራ ማህበራት ነው ያሉት ሀላፊው ይህንኑ በመገንዘብ እንደ ወረዳው የተደራጁት ህብረት ስራ ማህበራት በተገቢው መንገድ ሊጠናከሩ ይገባልም ብለዋል።
ከዚህ በተጨማሪ በወረዳው ከማዳበሪያ ስርጭት ጋር ተያይዞ አንዳንድ ቀበሌዎች ላይ የሚፈጠሩትን ክፍተቶች በዘላቂነት እንዲቀረፉ በማድረግ የአርሶአደሩ ምርትና ምርታማነት ማሳደግ እንደሚገባም አቶ ፀጋዬ አያይዘው ተናግረዋል ።
ከዚህ በተጨማሪ እንደ ወረዳው የሚመረቱ ምርቶችን ለማህበረሰቡ ፍጆታ በማቅረብ የኑሮ ውድነት ለማረጋጋትና የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በቅንጅትና በባለቤትነት መስራት እንደሚያስፈልግም ሀላፊው አሳስበዋል ።
በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ለሁለት ተከታታይ ቀናት በፅ/ቤቱ በሚመለከታቸው የስራ ሂደት አስተባባሪዎች የተለያዩ ሰነዶች ቀርበው ሰፊ ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን አሁን ላይ ያለውን የኑሮ ውድነት ለማረጋጋት መሰረታዊ ህብረት ስራ ማህበራት በየአካባቢው የሚመረቱ ምርቶችን ለማህበረሰቡ ማቅረብ እንዳለባቸው ተመላክቷል ።
የመድረኩ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየትም በተቋሙ የተከናወኑ የተሻሉ ተግባራቶችን በማስቀጠልና ውስንነቶችን በቀጣይ እንዲታረሙ በማድረግ በትኩረት በመስራት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሁሉም በቅንጅት መሰራት የሚጠይቅ በመሆኑ የድርሻቸውን እንደሚወጡም ተናግረዋል።
ለሁለት ተከታታይ ቀናት በተደረገው ስልናና ውይይት የህብረት ስራ ፅ/ቤትና ሁለገብ አደራጆች ፡ የአፈር ማዳበሪያ ሂሳብ ሰራተኞች ፡ የሽያጭ ባለሙያዎች ፡ የመጋዘን ሀላፊዎችና አሰራጮች እንዲሁም የቀበሌ እና የቁጠባና ብድር ክላስተር ለቀመናብርቶች ተሳታፊ ሆነዋል ሲል የዘገበው የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው።






