
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት መስተዳድር ምክር ቤት በአራት የተለያዩ ረቂቅ አዋጆች ላይ ዉይይት አደረገ።
ጥር 21/2018 ዓ.ም (አገና)
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት መስተዳድር ምክር ቤት በአራት የተለያዩ ረቂቅ አዋጆች ላይ ዝርዝር ዉይይት በማድረግ አዋጆቹን ለክልሉ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መርቷል።
መስተደድር ምክር ቤቱ ዛሬ ማምሻዉን በበይነ መረብ አማካይነት ባካሄደው ስብሰባ የተወያየባቸዉ ረቂቅ አዋጆች፦
1/ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 10/2016 (ማሻሻያ) ረቂቅ አዋጅ፣
2/ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የኤክሳይዝ ታክስ ረቂቅ አዋጅ፣
3/ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የጫት ኤክሳይዝ ታክስ ረቂቅ አዋጅ፣
4/ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ባህላዊ ፍርድ ቤቶችን ለማቋቋም እና እውቅና ለመስጠት የወጣ ረቂቅ አዋጅ የሚሉት መሆናቸዉ ተመልክቷል።
መረጃው የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ነው።







