የእዣ ወረዳ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት

የአገና ኮንስትራክሽንና ኢንደስትሪያል ኮሌጅ ነው!!

=========

ህዳር 3/2016

በማናቸውም የሰለጠኑ ሀገራት ለስልጣኔያቸው መረት የሆነው የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ዘርፍ ላያ የፈሩ ባለሙሉ ክህሎት፤ዕውቀትና አስተሳሰብ ያላቸው አምራች ዜጎች መሆናቸው አያጠያይቅም።ዛሬም ሀገራችን ወደ ያደጉ ሀገራት ተርታ ለመሰለፍ በምታደርገው ጥረት በተለያዩ ኢንደስትሪዎች የሚፈለገውን የሰለጠነ የሰው ሀይል ምንጩ ይህንኑ ዘርፍ እንደመሆኑ መጠን የአገና ኮንስትራክሽንና ኢንደስትሪያል ኮሌጅ ዘርፉ የሚፈልገውን ብቁና የሰለጠነ የሰው ሀይል ለማፍራት የሚያስችል ቅድመዝግጅት በማጠናቀቅ ሰልጣኞች በመቀበል ላይ ይገኛል።በወረዳችንና በከተማችን ውስጥ እየተስፋፉ የሚገኙ የተለያዩ ኢንቨስትመንቶችና ሌሎች ከፍተኛ የሰው ሀይል የሚፈልጉ ተቋማት ፍላጎትና የወቅቱ የስራ ገበያ ጥናት መነሻ በማድረግ በሚከተሉት ሙያዎች ላይ 12ኛ ክፍል ያጠናቀቁ ተማሪዎች እስከ ህዳር 14/2016 ድረስ እየመዘገብን ስለሆንን ያለምንም ጊዜ ብክነት በአጭር ጊዜ ውስጥ የሙያ ባለቤት በመሆኑ የስራ ዕድል ተጠቃሚ ይሁኑ ይላል የአገና ኮንስትራክሽንና ኢንደስትሪያል ኮሌጅ!!