የእዣ ወረዳ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት

የጉራጌ ክትፎ ባህልና እውቀትን በዩኔስኮ የሰው ልጆች ወካይ የማይዳሰስ ቅርስነት ለማስመዝገብ በተካሄደው ጥናት ዙሪያ የምክክር መድረክ በወልቂጤ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

የጉራጌ ክትፎ ባህልና እውቀትን በዩኔስኮ የሰው ልጆች ወካይ የማይዳሰስ ቅርስነት ለማስመዝገብ በተካሄደው ጥናት ዙሪያ የምክክር መድረክ በወልቂጤ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

ጥር 30/2018 ዓ.ም(አገና)

የጉራጌ ማህበረሰብ ከጥንት ጀምሮ በሀገሪቷና በአለም አቀፍ ደረጃ ስሙን ከሚተኩትና መጠሪያው ከሆኑት ምግቦች ውስጥ ክትፎ በቀዳሚነት ይጠቀሳል።

የጉራጌ ክትፎ አሰራር ልዩ እውቀትና ጥበብ የሚጠይቅ ሲሆን ከዝግጅቱ እስከ አመጋገቡ በብሔሩ ልዩ ጥንቃቄና ትኩረት ተሰጥቶት የሚዘጋጅ የምግብ አይነት መሆኑና ለዚህም የጉራጌ ህዝብ ኑሮውን በእንሰት ላይ የተመሰረተ ሲሆን የእንሰት ውጤት የሆነው ቆጮ እና ክትፎ ደግሞ የማይነጣጠሉና የአንድ ሣንቲም ሁለት ገፅታዎች ናቸው።

የጉራጌ ክትፎ ዛሬ ላይ ብሄራዊ ምግብ ከመሆኑም ባሻገር ከምግብ ስያሜነት አልፎ የንግድ ምልክት እየሆነ ሲሆን የጉራጌ ክትፎ ስጋን በመክተፍና በማሳነስ የሚጠናቅ ሳይሆን ልዩ ልዩ ማጣፈጫ ቅመሞችና የእንሰሳት ውጤቶችም በውስጡ የሚይዝ ነው።

ክትፎ ለማዘጋጀት ከንጹህ ቂቤ ባሻገር በዋነኝነት ስርና ጮማ የሌለለው ቀይ የሽንጥ ስጋ፣ ሚጥሚጣ፣ ኮሰረት፣ ኮረሪማ፣ ነጭና ጥቁር አዝሙድ፣ ጨውና ሌሎችም መቀመሚያዎች ይጠቀማል፡፡

የጉራጌ ክትፎ በዩኔስኮ የሰው ልጆች ወካይ የማይዳሰስ ቅርስነት ለማስመዝገብ በርካታ ስራዎች ሲሰራ ቆይቷል።

በምክክር መድረኩም የኢፌድሪ ቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረ/ፕሮፌሰር አበባው አያሌው፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ባህል ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል መንገሻ፣ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ፣ የምስራቅ ጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙስጠፋ ሀሰን፣የኢፌድሪ ቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ኤሊያስ ሽኩር ጨምሮ የፌደራል፣ የክልል፣ የዞንና የወረዳ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የወልቂጤ ዩኒቨርስቲና የጉልባማ አመራሮችና ሌሎችም ተገኝተዋል።

ጉራጌ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን እንደዘገበው