ሐምሌ 21/2018 ዓ.ም (ወልቂጤ)
========================================================================
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት “ሁሉ አቀፍ እምርታ ለሁለንተናዊ ከፍታ” በሚል መሪ ቃል በሆሳዕና ከተማ ባካሄደው የ2018 ዓ.ም የፓርቲ ስራዎች ማጠቃለያ መድረክ፣ የጉራጌ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት በክልሉ ካሉ ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች በላቀ አፈፃፀሙ የ1ኛ ደረጃ እውቅናና የሞተር ሽልማት ተበርክቶለታል።
ይህ አበረታች ስኬት ሊመዘገብ የቻለው በዞኑ አመራር፣ በፓርቲው አባላትና በሰፊው የጉራጌ ህዝብ የተቀናጀ ጥረት፣ ጠንካራ ህዝባዊ አደረጃጀትና የጋራ ስራ ውጤት በመሆኑ ነው።
ፅህፈት ቤቱ ላስመዘገበው ውጤት አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት በሙሉ ምስጋናውን እያቀረበ፤ በቀጣይም የፓርቲውን እሳቤዎች በመተግበር፣ የህዝባችንን የሰላም፣ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በላቀ ደረጃ ለመመለስ ዝግጁ መሆኑን አረጋግጧል።
ለተመዘገበው ታላቅ ውጤት በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ፤ እንኳን ደስ አለን!
“ሁሉ አቀፍ እምርታ ለሁለንተናዊ ከፍታ!








