የእዣ ወረዳ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት

ገዢ ትርክት ለትውልድ ማውረስ የሀገር ዘላቂነት ያለው ሰላምና ልማት ለማረጋገጥ የሚያስችል በመሆኑ ሁሉም በጋራ አንድነት ላይ መረባረብ እንደሚገባ በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ የስልጠና ተሳታፊዎች ገለፁ ።

=============================

ገዢ ትርክት ለትውልድ ማውረስ የሀገር ዘላቂነት ያለው ሰላምና ልማት ለማረጋገጥ የሚያስችል በመሆኑ ሁሉም በጋራ አንድነት ላይ መረባረብ እንደሚገባ በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ የስልጠና ተሳታፊዎች ገለፁ ።
በወረዳ 5 ኛ ዙር የቀበሌ አመራሮችና አባላት እየተሰጠ ያለውን የአቅም ግንባታ ስልጠና ዛሬም ተጠናክሮ ቀጥሏል።
ተዘዋውረን ያነጋገርናቸው የስልጠና ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት በዚህ ስልጠና እንደ ሀገር ማሰብ እንድንችልና እርስ በርስ ተረዳድተን ሀገራችንን እንዴት ማሻገር እንዳለብን ትልቅ ትምህርት እየወሰድንበት ነው ብለዋል።
እንደ አስተያየት ሰጪዎቹ ተጨማሪ ገለፃ በተለይም ገዢ ትርክት ለትውልድ ማውረስ የሀገር ዘላቂነት ያለው ሰላምና ልማት ለማረጋገጥ የሚያስችል በመሆኑ ሁሉም በጋራ አንድነት ላይ መረባረብ እንደሚገባ በስልጠናው ለመገንዘብ ችለናልም ብለዋል ።
በዚህ ስልጠና ያለንን ሀብት ማልማትና መጠቀም እንዳለብን ተረድተናል ያሉ አስተያየት ሰጪዎቹ በቀጣይም በሚኖሩን ቀናት በአግባቡ ስልጠናው በመከታተል ከዚህ በፊት የነበረን የተዛቡ ሀሳቡች ትተን በልማቱ ግንባር ቀደም ተሳታፊ በመሆን እንደ ሀገር የተያዘው የብልፅግና ጉዞ ስኬታማ እንዲሆን የድርሻችንን እንወጣለንም ብለዋል።
የስልጠናው ሂደት ተዘዋውረው የተመለከቱት የእዣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘውዱ ዱላ እንዲሁም የእዣ ወረዳ ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ተሾመ ስራኒ እንዳሉት በዚህ ስልጠናም ሀገራዊ የሆነ ገዢ ትርክት እና ህብረ ብሔራዊ ወንድማማችነትን ለማጠናከር ፋይዳዉ የጎላ ነው ብለዋል ።
በእውነተኛ ትርክ ላይ ተመስርተው ሀገራዊ አንድነትን በማጠናከር የኢትዮጵያን ታረክ ለመቀየር ትጥቅ አቅም ይፈጥራል ያሉት ሀላፊዎቹ ስልጠናውን ከንድፈ ሀሳብ ባሻገር የቀበሌ አመራሩና አባላቱ ወደ ተግባር ቀይሮት የራሱ የኑሮ ደረጃ በማሻሻል እንደ ሀገር ሁለንተናዊ ለውጥ ለማስመዝገብ የሚያስችል ነውም ብለዋል ሲል የዘገበው የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው ።