
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በትግርኛ ባደረጉት ቃለ መጠይቅ ላይ ያነሷቸው አንኳር ሀሳቦች…
የትግራይ ሕዝብ ከጦርነት ይልቅ ሰላምና ልማት ይገባዋል
ወጣቶች በአሮጌ አስተሳሰብ ለጦርነት ከሚገፋፏቸው አካላት ራሳቸውን ሊጠብቁ ይገባል
መንግሥት በትግራይ ክልል ሰላም እንዲሰፍንና ዳግም ጦርነት እንዳይከሰት ጽኑ ፍላጎት አለው
ሕወሓት ከ50 ዓመት በፊት በነበረ ኋላቀር አስተሳሰብ የታሰረና ለውጥን ለመቀበል ፍላጎት የሌለው ድርጅት ነው
ሕወሓት በአሮጌው መንገድ ለመጓዝ መሞከሩ ለግጭት ዳርጎታል
ቆሞ ቀሩ ኃይል ኢትዮጵያ ትፈርሳለች የሚል የተሳሳተ ስጋት በመዝራት የለውጡን ኃይል እንደ ጠላት ሲመለከት ቆይቷል
በኢትዮጵያ የነበረው የተሳሳተ ትርክት ዜጎች በጥርጣሬ እንዲኖሩ አድርጓል
መንግሥት የትግራይ ሕዝብ ሰላም እንዲያገኝ ባንክ፣ መብራትና ቴሌኮም የመሳሰሉ አገልግሎቶችን በፍጥነት እንዲመለሱ አድርጓል
ሆኖም ቆሞ ቀሩ ቡድን የፕሪቶሪያውን ስምምነት “መርጦ የመተግበር” ዝንባሌ እያሳየ ነው
የሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ውሳኔ አላከበረም
ድርጅቱ ለልማት የተመደበውን በጀት ለጦርነት ዝግጅትና ለታጣቂዎች ቀለብ እያዋለ ነው
ይህም በትግራይ ሕዝብ ላይ ተጨማሪ መከራ እያመጣ ይገኛል
በጦርነቱ ወቅት ለተፈጸሙት ጥፋቶች ከፖለቲካ ወገንተኝነት ነፃ በሆነ መንገድ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ የሽግግር ፍትሕ አስፈላጊ ነው
ወንጀል የፈጸሙ አካላት በሕግ መጠየቅ አለባቸው
በጦርነቱ ወቅት የተፈጸሙ ማናቸውም ዓይነት ጥፋቶች፣ ግድያዎችና ዘረፋዎች (በተለይም በአክሱም፣ ዓድዋና ሽሬ አካባቢዎች) የሚወገዝ ተግባር ነው
መንግሥት ማንኛውንም የውጭ ኃይል ጣልቃ ገብነት አጥብቆ ይቃወማል፥ የሀገርን ሉዓላዊነት ለማስከበር ይሰራል






