የእዣ ወረዳ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት

ጠንካራ መንግስት ለመፍጠር እንደ ሀገር የተቀመጡ ግቦችን ለተፈጻሚነታቸው የሚተጋ ፡ ጠንካራና ፅናት ያለው አመራሩና አባላት መገንባት እንደሚያስፈልግ ተገለፀ ።

============================

ጠንካራ መንግስት ለመፍጠር እንደ ሀገር የተቀመጡ ግቦችን ለተፈጻሚነታቸው የሚተጋ ፡ ጠንካራና ፅናት ያለው አመራሩና አባላት መገንባት እንደሚያስፈልግ ተገለፀ ።
“ከእዳ ወደ ምንዳ” በሚል መሪ ሀሳብ በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ ለቀበሌ አመራርና አባላት በ30 የስልጠና ጣቢያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና ኦረንቴሽን በዛሬው እለት ተሰጥቷል።
የእዣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘውዱ ዱላ የስልጠና ጣቢያዎች ተዘዋውረው ምልከታ ባደረጉበት ወቅት እንደገለፁት የስልጠናው አላማ የብልፅግና አመራሩና አባላቱ ሀገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ተለዋዋጭ ሁኔታዎችን ተገንዝበው፣ ፈተናዎችን ወደ ዕድል በመቀየር የመፈፀም ፡ የማስፈፀምና ምርትና ምርታማነቱን ለማሳደግ አቅም እንዲፈጥርለት ያለመ ነው ።
በስልጠናውም ሀብት መፍጠር ፡ ማስተዳደርና መጠቀም ፡ በተፈጥሮ ሀብት ዘንድ ያሉትን የመልማት አቅሞችን ማሳደግ ፡ ዘላቂነት ያለው ሰላም እንዴት ማምጣት እንዳለብን እና ሌሎችም ወቅታዊና አስፈላጊ የሆኑ ጉዳዮች በትኩረት ውይይት ሚደረግባቸው እንደሆነም ዋና አስተዳዳሪው አመላክተዋል።
በየደረጃው ያለው አመራሩና አባላቱ አቅም በተሻለ ሁኔታ በመገንባትና ማህበረሰቡ የሚያነሳቸውን ጥያቄዎች ምላሽ መስጠት ይገባል ያሉት አቶ ዘውዱ ሰላም የሰፈነበት አካባቢ በመፍጠር በልማትና መልካም አስተዳደር ስራ ላይ ግንባር ቀደም ሆኖ እንዲሄድና ለውጥ እንዲመጣ በየደረጃው ያለው አካላት የድርሻውን እንዲወጣ ታስቦ የተዘጋጀ ስልጠና መሆኑንም አብራርተዋል።
የእዣ ወረዳ መመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ተሾመ ስራኒ በበኩላቸው ስልጠናው በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ1ኛ እስከ 4ተኛ ዙር ሲሰጥ የነበረው ስልጠና መነሻ በማድረግ በወረዳ ደረጃ የሚሰጠው 5ተኛ ዙር የአመራርና አባላቱ አቅም ግንባታ ስልጠና በዚህ ዙሩ በቀበሌ ደረጃ ለአርሶአደሩ የሚሰጥ ስልጠና ነው ብለዋል ።
የአመራርን አቅም ግንባታ በማጠናከር ህብረብሄራዊ አንድነት የተረጋገጠበት ማህበረሰብ ከመፍጠር አንፃር በየደረጃው ያሉ አመራርና አባሎች በቂ እውቀት ኑሮአቸው በአላማው ዙሪያ ግልፀኝነት እንዲፈጠርና አቅም ለመገንባት ስልጠናው ፋይዳው የጎላ በመሆኑ በንቃት እንዲከታተሉ እንደ ወረዳው በቂ ዝግጅት ተደርጎበት በዛሬው እለት ኦረንቴሽን መሰጠቱንም ዋና የመንግስት ተጠሪው ገልፀዋል ።
ይህ ስልጠና ከታህሳስ 12-19/04/2016 ድረስ በወረዳው ለሚገኙ አርሶ አደር፣ የከተማው ነዋሪ፣ ፐብሊክ ሰርቫንትና ኢንተርፕራይዝ አመራርና አባላት የአቅም ግንባታ ስልጠና እንደሚሰጥ የገለፁት አቶ ተሾመ አመራሩና አባላቱ ስልጠናው በአግባቡ በመከታተል እንደ ሀገር ለመበልፀግ የተወጠነውን ውጥን ከግብ እንዲደርስ ሁሉም የድርሻውን መወጣት እንዳለበት መልዕክት አስተላልፈዋል ሲል የዘገበው የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው ።
ለበለጠ መረጃ በተለያዩ የሚዲያ አማራጮቻችን የምናደርሳቸው መረጃዎች ይከታተሉን !!
የቴሌግራም ቻናላችን ፡-
ዩቲዩ :-
እንዲሁም ዌብሳይት https://ezhaguraghe.gov.et/