የእዣ ወረዳ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት

ምክር ቤቶች በህገ-መንግስቱ የተሰጣቸውን ሀላፊነት በአግባቡ እንዲወጡ የእዣ ምክር ቤት አስታወቀ ።

===========================

ምክር ቤቶች በህገ-መንግስቱ የተሰጣቸውን ሀላፊነት በአግባቡ እንዲወጡ የክትትልና የቁጥጥር ስልታቸውን በማጠናከርና ተግባራትን በተቀናጀ ሁኔታ ሊሰሩ እንደሚገባ የእዣ ምክር ቤት አስታወቀ ።
ምክር ቤቱ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ለባለድርሻ አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል ።
በእለቱም የእዣ ወረዳ ዋና አፈ-ጉባኤ አቶ ሙከረም በደዊ እንደገለፁት በየደረጃው የሚገኙ ምክር ቤቶች የክትትልና ቁጥጥር አቅማቸው በማጎልበት ለህብረተሰቡ ተጠቃሚነት መስራት አለባቸው ።
የወረዳው ምክር ቤትም በየዓመቱ ለባለድርሻ አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየሰጠ ሲሆን በተሰጡ ስልጠናዎችም በርካታ ለውጦች ቢመዘገቡም አሁንም ክፍተት መኖሩን ጠቁመዋል።
በቀጣይም የክትትልና ቁጥጥር ተግባር በማጠናከር በቀበሌ ደረጃ ያለው ክፍተት ማረም ያስፈልጋል ያሉት አቶ ሙከረም በተቋማት 60 በ40 እቅድ ዝግጅትና ምዘና ስርዓት ተጠናክው የህዝቡ የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመፍታት በሚያስችል መልኩ በተገቢው መስራት ይገባልም ብለዋል።
የእዣ ወረዳ ም/አስተዳዳሪና የትምህርት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ተጠምቀ በርጋ በበኩላቸው እንደገለፁት ምክር ቤቶች በህገ-መንግስቱ የተሰጣቸውን ሀላፊነት በአግባቡ እንዲወጡ የክትትልና የቁጥጥር ስልታቸውን በማጠናከርና ተግባራት በተቀናጀ መንገድ መስራት ይገባል ።
የዜጎች መሰረታዊ መብቶችና ነፃነቶች መከበራቸውን፡ መልካም አስተዳደርን ለማስፈን ግልፅ አሰራር መዘርጋቱንና ፓሊሲዎች ፡ ስትራቴጂዎችና ህጎች በአግባቡ ስራ ላይ መዋላቸውን መከታተል የምክር ቤቶች ተግባር መሆኑን ያነሱት ም/አስተዳዳሪው ይህንን ለማሳካት የቁጥጥር የስልት መርሆች የስራ እቅድና የአፈጻጸም ሪፖርት በመመርመር እንዲሁም የተሰሩ ስራዎች በተግባር በመመልከት በሚደረገው ክትትሉ ውጤት ማምጣት እንደሚቻል አስገንዝበዋል።
ተቋማት በተግባራቸው ውጤታማ አንዲሆኑ ከእቅዱ ጀምሮ ያሉ ተግባራቶች በአግባቡ በመፈተሽና በመከታተትል ህብረተሰቡ በልማትና መልካም አስተዳደር ፍትሃዊ ተጠቃሚ መሆን እንዳለበትም ተናግረዋል።
በየደረጃው ከህዝቡ ለሚነሱ አቤቱታዎች፣ ጥቆማዎች እና ቅሬታዎች አስፈፃሚ አካላት በየደረጃው ምላሽ እንዲያገኙ እንደ ወረዳው ትኩረት ተሰጥቶ መሰራት አለበት ያሉት አቶ ተጠምቀ ለዚህ የቀበሌ ምክር ቤቶች ሳይቆራረጡ በጊዜ ጉባኤ በማካሄድ ህዝቡን የሰጣቸው አደራ በአግባቡ ሊወጡ እንደሚገባም አሳስበዋል።
የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በየደረጃው የሚገኙ ምክርቤቶች አቅም መጎልበት የላቀ አስተዋጽኦ የሚያበረክት በመሆኑ የግንዛቤ መድረኩ በቀጣይ በየምክር ቤቱ የሚስተዋሉ ጉለቶችን የሚያርም ስልጠና በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተሳታፊዎች በአስተያየታቸዎ ገልፀዋል።
በእለቱም በሚመለከታቸው የስራ ሀላፊዎች የስልጠና ሰነድ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ማድረግ ተችሏል ሲል የዘገበው የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው ።