የእዣ ወረዳ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት

ሞዴል የሴቶች ልማት ሕብረት

በህብረት መሥራት በመቻላቸው ለኢኮኖሚና ማህበራዊ ህይወታቸው ስኬት ቁልፍ ሚና እየተተጫወት እንደሚገኝ በእዣ ወረዳ መንጠር ቀበሌ በቃጫ ስራ ተሰማርተው የሚገኙ የቶትም ብራ ማህበር አባላት ገለፁ።

መጋቢት 5/2018 (ወልቂጤ)

ሞዴል የሴቶች ልማት ሕብረት እንዲበራከቱ በመደረጉ በወረዳው ኢኮኖሚያዊ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ተጠቃሚነታቸው እያደገ ስለመምጣቱ የእዣ ወረዳ ሴቶችና ሕፃናት ፅ/ት ቤት አስታውቋል።

በወረዳው መንጠር ቀበሌ ቶትም ብራ የቃጫ ስራ ማህበር ውስጥ ተደራጅተው ከሚገኙ አባላት መካከል ወ/ሮ አለም ደረግ ፣አበበች ቲመርጋ እና አምሳለች ለጋ ይገኙበታል ተደራጅተው በህብረት መስራት ከጀመሩ ወዲህ በዘርፉ እውቀት እና ክህሎት በማዳበር ተጠቃሚ መሆን ችለናል ይላሉ።

ከማህበሩ አባላት ውስኖቹ አስቀድመው በአካባቢው የሚዘወተረው የጅባ እና መሠል የዕደጥበብ ስራ ላይ ተሰማርተው ይሰሩ እንደነበር ጠቁመው ዛሬ ላይ በህብረት በቃጫ ስራ ላይ በመሰማራት የተለያዩ የእጅ ስራ ውጤቶችን በማምረት የበለጠ ውጤታማ መሆን እንደቻሉ አስረድተዋል ።

በቶትም ብራ ማህበር ተደራጅተው ከሚሰሩ የቃጫ ስራ ውጤቶች መካከል የተለያዩ ቦርሳዎችና፣ ጌጣጌጦች ለተጠቃሚዎች እያቀርቡ መሆናቸውንም ተናግረዋል።

በዚህም ገንዘብ በመቆጠብ ኢኮኖሚያቸውን ከማሳደጉ ባሸገር በርካታ ተሞክሮ በመለዋወጥ ያገኙትን ልምድ ለተተኪው ትውልድ ልምዳቸውን እያካፈሉ እንደሚገኙም አውስተዋል።

ከዚህ የበለጠ ተጠቃሚ እንዳንሆን ምቹ የመሥሪያና የመሸጫ ቦታ በስራቸው ላይ እክል እየፈጠረባቸው እንደሚገኝም ገልጸዋል።

የእዣ ወረዳ ሴቶችና ህፃናት ፅሕፈት ቤት ሀላፊ ወ/ሮ አሰለፍች ክብሩ እንደገለፁት በወረዳው በ18ቱም ቀበሌያት ውስጥ የሚገኙ ሴቶች በልማት ሕብረት አደራጅቶ ወደ ስራ በማስገባት ተጠቃሚ እንዲሆኑ የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛል።

እንደወረዳ 4መቶ64 የልማት ሕብረት በማቋቋም በአካባቢ ፅዳት በኢኮኖሚና ማህበራዊ መሠል የህብረተሠቡ ወቅታዊና ቀጣይነት ያላቸው መሠረታዊ ጉዳዮች ላይ እንዲወያዩ ፣ አቅም እንዲፈጥሩም ስልጠና ከመስጠት ጀምሮ የድጋፍና ክትትል ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን አስረድተዋል።

ከዚህ በፊት በተናጥል የነበራቸውን የእደጥበብ እውቀት እና ክህሎት በስልጠና በመደገፍ እንደ ቶትም ብራ የመሠሉ በርካታ ሞዴል የሴቶች ማህበራት ማፍራት መቻሉን ሃላፊዋ ጠቁመዋል።

ማህበራቱ በአቅም እንዲጎለብቱ ኤግዚቢሽኖች እንዲሳተፉ እና ልምድ እንዲወስዱ እየተደረገ መሆኑን አመላክተው ምቹ የመስሪያና መሸጫ ቦታ እንዲኖራቸው ለማድረግ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን አመላክተዋል።