ሞዴል የሴቶች ልማት ሕብረት

በህብረት መሥራት በመቻላቸው ለኢኮኖሚና ማህበራዊ ህይወታቸው ስኬት ቁልፍ ሚና እየተተጫወት እንደሚገኝ በእዣ ወረዳ መንጠር ቀበሌ በቃጫ ስራ ተሰማርተው የሚገኙ የቶትም ብራ ማህበር አባላት ገለፁ።

መጋቢት 5/2018 (ወልቂጤ)

ሞዴል የሴቶች ልማት ሕብረት እንዲበራከቱ በመደረጉ በወረዳው ኢኮኖሚያዊ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ተጠቃሚነታቸው እያደገ ስለመምጣቱ የእዣ ወረዳ ሴቶችና ሕፃናት ፅ/ት ቤት አስታውቋል።

በወረዳው መንጠር ቀበሌ ቶትም ብራ የቃጫ ስራ ማህበር ውስጥ ተደራጅተው ከሚገኙ አባላት መካከል ወ/ሮ አለም ደረግ ፣አበበች ቲመርጋ እና አምሳለች ለጋ ይገኙበታል ተደራጅተው በህብረት መስራት ከጀመሩ ወዲህ በዘርፉ እውቀት እና ክህሎት በማዳበር ተጠቃሚ መሆን ችለናል ይላሉ።

ከማህበሩ አባላት ውስኖቹ አስቀድመው በአካባቢው የሚዘወተረው የጅባ እና መሠል የዕደጥበብ ስራ ላይ ተሰማርተው ይሰሩ እንደነበር ጠቁመው ዛሬ ላይ በህብረት በቃጫ ስራ ላይ በመሰማራት የተለያዩ የእጅ ስራ ውጤቶችን በማምረት የበለጠ ውጤታማ መሆን እንደቻሉ አስረድተዋል ።

በቶትም ብራ ማህበር ተደራጅተው ከሚሰሩ የቃጫ ስራ ውጤቶች መካከል የተለያዩ ቦርሳዎችና፣ ጌጣጌጦች ለተጠቃሚዎች እያቀርቡ መሆናቸውንም ተናግረዋል።

በዚህም ገንዘብ በመቆጠብ ኢኮኖሚያቸውን ከማሳደጉ ባሸገር በርካታ ተሞክሮ በመለዋወጥ ያገኙትን ልምድ ለተተኪው ትውልድ ልምዳቸውን እያካፈሉ እንደሚገኙም አውስተዋል።

ከዚህ የበለጠ ተጠቃሚ እንዳንሆን ምቹ የመሥሪያና የመሸጫ ቦታ በስራቸው ላይ እክል እየፈጠረባቸው እንደሚገኝም ገልጸዋል።

የእዣ ወረዳ ሴቶችና ህፃናት ፅሕፈት ቤት ሀላፊ ወ/ሮ አሰለፍች ክብሩ እንደገለፁት በወረዳው በ18ቱም ቀበሌያት ውስጥ የሚገኙ ሴቶች በልማት ሕብረት አደራጅቶ ወደ ስራ በማስገባት ተጠቃሚ እንዲሆኑ የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛል።

እንደወረዳ 4መቶ64 የልማት ሕብረት በማቋቋም በአካባቢ ፅዳት በኢኮኖሚና ማህበራዊ መሠል የህብረተሠቡ ወቅታዊና ቀጣይነት ያላቸው መሠረታዊ ጉዳዮች ላይ እንዲወያዩ ፣ አቅም እንዲፈጥሩም ስልጠና ከመስጠት ጀምሮ የድጋፍና ክትትል ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን አስረድተዋል።

ከዚህ በፊት በተናጥል የነበራቸውን የእደጥበብ እውቀት እና ክህሎት በስልጠና በመደገፍ እንደ ቶትም ብራ የመሠሉ በርካታ ሞዴል የሴቶች ማህበራት ማፍራት መቻሉን ሃላፊዋ ጠቁመዋል።

ማህበራቱ በአቅም እንዲጎለብቱ ኤግዚቢሽኖች እንዲሳተፉ እና ልምድ እንዲወስዱ እየተደረገ መሆኑን አመላክተው ምቹ የመስሪያና መሸጫ ቦታ እንዲኖራቸው ለማድረግ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን አመላክተዋል።

ተፈጥሮአዊ የሆኑ የቱሪስት መዳረሻ ስፍራዎች ለጎብኚዎች መቹ ማድረግ እንደሚገባ ተገለፀ።

ተፈጥሮአዊ የሆኑ የቱሪስት መዳረሻ ስፍራዎች ለጎብኚዎች መቹ ማድረግ እንደሚገባ ተገለፀ።

መጋቢት 7/2018 ዓ.ም ( አገና )

የእዣ ወረዳ ባህል-ቱሪዝም ጽ/ቤት እና የሶርገረፋ የሀገርህን እውቅ ክብብ ተማሪዎች የፎቅራ ፏፏቴ ጎበኙ።

የእዣ ወረዳ ባህል-ቱሪዝም ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ በለጠ ሳህሌ እዣ ወረዳ የበርካታ ታሪካዊና ተፈጥሮአዊ የሆኑ የቱሪስት መዳረሻ ስፍራዎች ባለቤት መሆኗን ገልፀው እንደ ወረዳው በተለያዩ መንገዶች የማስተዋወቅና ለጉብኝት መቹ የማድረግ ስራ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

አክለውም እንደ ሀገር ከፍተኛ ትኩረት ከተሰጣቸው ጉዳዮች አንዱ የሆነው የቱሪዝም ዘርፉ መሆኑ ገልፀው ተማሪዎች ይህን አውቃችሁ የተፈጥሮ ቅርሶቻቹ መጠበቅ እና ማወቅ እንዳለባቸው አሳስበዋል።

እንደ ወረዳው ያሉን ምቹ ሁኔታዎች በመጠቀም የቱሪስት መዳረሻ ስፍራዎችን በማልማትእና የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ደረጃቸውን በማሳደግ በዘርፉ የሚፈለገውን ውጤት እንዲመዘገብ በትኩረት መስራት ይገባልም ብለዋል።

የት/ቤቱ የሀገርህን እውቅ ክበብ አስተባባሪ መምህር እንዳለ እንደገለፁት ተማሪዎች አካባቢያቸው ያሉ የተፈጥሮ ቅርሶች ማወቅ እንዳለባቸው ገልፀው

በዚህም ተማሪዎች እቅድ በማውጣት በወረዳው ያሉ የተለያዩ የተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ ቅርሶቻችን ማውቅ እና ለቀጣይ ትውልድ በመንከባከብ ማስቀጠል እንዳለብን አሳስበዋል ።

ፎቅራ ፏፏቴ የሚገኘው በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ ዋሳማር ቀበሌ ሲሆን ከዞኑ ዋና ከተማ ወልቂጤ በ45 ኪ.ሜ እና ከወረዳችን ዋና ከተማ አገና በ3 ኪ.ሚ ርቀት ላይ ይገኛል።

ፏፏቴው በስተምስራቅ አቅጣጫ ከዋናው አስፋልት መንገድ ትንሽ ገባ ብሎ ያገኙታል። ፏፏቴው ቁመቱ 35 ሜትር እና ጎኑ ደግሞ እስከ 12 ሜትር ቦታ ይሸፍናል። ቦታው ከመሰህብነቱ በመተጨማሪ መስህብ የሚያስብለው ጋራና ሸንተረሩ የጎበኞች ቀልብ ይሰባሉ ቦታው የተለያዩ ዝርያዎች እና የዱር እንስሳቶችም ይገኙበታል።

ከፊታችን ያሉት መጪዎቹን በዓላቶች ስናከብር የተቸገሩ ወገኖቻችንንና አቅመ ደካሞች በመርዳት መሆን እንዳለበት ተገለጸ።

ከፊታችን ያሉት መጪዎቹን በዓላቶች ስናከብር የተቸገሩ ወገኖቻችንንና አቅመ ደካሞች በመርዳት መሆን እንዳለበት ተገለጸ።

መጋቢት 07/2018 ዓ.ም (አገና)

በእዣ ወረዳ መንግስት ተቋማት በሚሰበሰበው የ1% ገንዘብ በማቀናጀት የእዣ ወረዳ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉጉዳዮች ጽ/ቤት ለአቅመ ደካሞች የምግብ ድጋፍ አደረገ።

የእዣ ወረዳ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳዮች ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ትግስት መንግስቴ እንዳሉት መረዳዳት ፈጣሪ የሚወደው መልካም ተግባር መሆኑንና በየጊዜው የተቸገሩ ወገኖችን በመርዳት ከማህበረሰቡ ጎን መሆን እንደሚገባ ገልፀው

የተቸገሩ ወገኖች እንዲታገዙ ለማድረግ የመንግስት ተቋማቶች ከማህበረሰቡ ጋር በቅንጅት እየሰሩ እንዳለና ይህም ተግባር ተጠናክሮ ሊጠቀጥልና በቅንጅት መስራት እንደሚያስፈልግ አሳስበው ተቋማቸውም ይህንን መሰል ተግባር አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

አክለውም መጪዎቹን በዓላቶች ስናከበር በመተጋገዝና ከተቸገሩ ወገኖችን ጋር በጋራ በመሆን ማሳለፍ እንደሚገባ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

ድጋፍ የተደረገላቸው የማህበረሰብ ክፍሎች በሰጡት አስተያየት በተደረገላቸው ድጋፍ መደሰታቸውን ገልጸው ይህን ላደረጉ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል ሲል የዘገበው የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ነው