የእዣ ወረዳ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት

ከፊታችን ያሉት መጪዎቹን በዓላቶች ስናከብር የተቸገሩ ወገኖቻችንንና አቅመ ደካሞች በመርዳት መሆን እንዳለበት ተገለጸ።

ከፊታችን ያሉት መጪዎቹን በዓላቶች ስናከብር የተቸገሩ ወገኖቻችንንና አቅመ ደካሞች በመርዳት መሆን እንዳለበት ተገለጸ።

መጋቢት 07/2018 ዓ.ም (አገና)

በእዣ ወረዳ መንግስት ተቋማት በሚሰበሰበው የ1% ገንዘብ በማቀናጀት የእዣ ወረዳ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉጉዳዮች ጽ/ቤት ለአቅመ ደካሞች የምግብ ድጋፍ አደረገ።

የእዣ ወረዳ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳዮች ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ትግስት መንግስቴ እንዳሉት መረዳዳት ፈጣሪ የሚወደው መልካም ተግባር መሆኑንና በየጊዜው የተቸገሩ ወገኖችን በመርዳት ከማህበረሰቡ ጎን መሆን እንደሚገባ ገልፀው

የተቸገሩ ወገኖች እንዲታገዙ ለማድረግ የመንግስት ተቋማቶች ከማህበረሰቡ ጋር በቅንጅት እየሰሩ እንዳለና ይህም ተግባር ተጠናክሮ ሊጠቀጥልና በቅንጅት መስራት እንደሚያስፈልግ አሳስበው ተቋማቸውም ይህንን መሰል ተግባር አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

አክለውም መጪዎቹን በዓላቶች ስናከበር በመተጋገዝና ከተቸገሩ ወገኖችን ጋር በጋራ በመሆን ማሳለፍ እንደሚገባ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

ድጋፍ የተደረገላቸው የማህበረሰብ ክፍሎች በሰጡት አስተያየት በተደረገላቸው ድጋፍ መደሰታቸውን ገልጸው ይህን ላደረጉ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል ሲል የዘገበው የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ነው