
=====================
በማዕከላዊ ክልል ርዕሰ መስተዳደር በአቶ እንዳሻው ጣሰው የተመራ ክልል አቀፍ የኢንቨስትመንት ጉብኝት በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ ተካሂዷል ።
በጉብኝቱም የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ እንዳሻው ጣሰው ፡ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ ፡ የክልልና የዞን ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ፡ የእዣ ወረዳ ካቢኔ አባላት ተሳታፊ ሆነዋል ።
በጉብኝቱም ፍቅር ውሃ ፡ ኤግል ኧይ አግሮ ኢንዱስትሪ ፡ እና ቲናው አበባ ልማት አክሲዮን ማህበር የስራ እንቅስቃሴ ምልከታ የተደረገ ሲሆን እዣ ወረዳ በዞኑ ምቹ የኢንቨስትመንት አካባቢዎች መካከል ግንባር ቀደም ተጠቃሽ እንደሆነም ተመላክቷል ።
የእዣ ወረዳ መንግስትም ኢንቨስትመንት በማበረታታት ረገድ እያደረገው ያለው አስተዋፅኦ ውጤታማና ተጨማሪ እንቅስቃሴ ለማድረግ የሚያነሳሳ በመሆኑ በጥንካሬ የሚገለፅ እንደሆነም በኢንቨስትመንቱ ዘርፍ የተሳተፉ አካላት በጉብኝቱ ወቅት ገልፀዋል ።
በእለቱም በኢንቨስትመንቱ ዘርፍ ከባንክ ብድርና ሌሎችም ተያያዥነት ያላቸው ተግዳሮት የሚሆኑ ጉዳዮች ተነስተው እልባት ሚያገኙበት ጉዳይ ላይ በርዕሰ መስተዳደሩ በአቶ እንዳሻው ጣሰው የመፍትሄ አቅጣጫ ተቀምጧል ሲል የዘገበው የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው ።






