የእዣ ወረዳ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት

በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ አንበሊ ቀበሌ ከ13.5 ኪሎ ሜትር በላይ ጥራቱን የጠበቀ የጠጠር መንገድ ግንባት ስራ በመጠናቀቅ ላይ እንደሚገኝ የወረዳ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ፅ/ቤት አስታወቀ ።

==================================

በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ አንበሊ ቀበሌ ከ13.5 ኪሎ ሜትር በላይ ጥራቱን የጠበቀ የጠጠር መንገድ ግንባት ስራ በመጠናቀቅ ላይ እንደሚገኝ የወረዳ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ፅ/ቤት አስታወቀ ።
የመንገድ ግንባታ ስራው ከ10 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት ሲሆን ይህም በአካባቢው ማህበረሰብ ፡ በባለሀብቱና በወረዳው መንግስት ድጋፍ መሆኑንም ተጠቁሟል።
የእዣ ወረዳ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ኢብራሂም አወል እንደገለፁት በወረዳው ማህበረሰቡና ባለሀብቱ የተሳተፈባቸው እንዲሁም መንግስት ድጋፍ ያደረገባቸው በርካታ የመንገድ ልማት ስራዎች ከሌላ ጊዜአት በተሻለ ሁኔታ በስፋት እየተሰሩ ይገኛሉ ።
ሁሉም ልማት ሊሳለጥ የሚችለው የመንገድ መሰረተ ልማት ሲኖር መሆኑ በተገቢው በመረዳት እንደ ወረዳው በመንገድ ልማት ዘርፍ በበጀት ዓመቱ ከ38.5 ኪ .ሜትር በላይ የሚሆኑ የጠጠር መንገድ በአዲስ ተሰርተዋል ያሉት አቶ ኢብራሂም ሌሎች ነባር መንገዶች ከ56 ኪ.ሜ በላይ የጥገና ስራ መሰራቱን እንዲሁም ከዚህ ስራ የተያያዙ የተለያየ መጠንና አገልግሎት ያላቸው ከ5 በላይ ስትራክቸሮች መሰራታቸውን አብራርተዋል ።
በአጠቃላይ በዚህ አመት በወረዳው ደረጃ በርካታ የመንገድ ስራዎች የተሰሩ መሆኑንና እነዚህም በማህበረሰቡና በመንግስት ደረጃ ከ48.5 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ እንደተደረገ ያስታወሱት አቶ ኢብራሂም ይህም እንደ መንግስትም ይሁን እንደ ማህበረሰብ ትልቅ ሀብት ኢንቨስት የተደረገበት ልማት ነው ብለዋል።
እንደ ወረዳው ከሌላ ጊዜ ከሚደረገው አስተዋፅኦ በማሻሻል ከ5ሚሊየን ብር የሚጠጋ ገንዘብ በተለያዩ ቀበሌዎች በዓመቱ ለመንገድ ልማት ድጋፍ መደረጉን የጠቆሙት ሀላፊው በተመሳሳይ መልኩ የማህበረሰቡ ድጋፍ ከፍተኛ ድርሻ የሚይዝ ሲሆን እስካሁን ተሳታፊ ከሆነባቸው ዓመታቶች እጅግ የላቀ በመሆኑ ትልቅ ምስጋና ይገባልም ብለዋል ።
በወረዳው በዚህ አመት የመንገድ ልማት በስፋት ከተሰራባቸው ቀበሌዎች አንዱ አንበሊ ቀበሌ ሲሆን ከ13.5ኪ ሜ በላይ የሚሆን የጠጠር መንገድ በተሻለ ስታንዳርድ መሰራቱን ያመላከቱት ሀላፊው ለዚህም ከ10 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት ሲሆን ይህም በህብረተሰቡ በባለሀብቱና በመንግስት አስተዋፅኦ የተሰራ ነው ብለዋል ።
በአንበሌ ቀበሌ የተሰራው መንገድ አጎራባች ከሆነው ሙህር አክሊል ወረዳ : ከወረዳው 3 ያህል ቀበሌዎች እንዲሁም መንደር ለመንደር የሚያገናኝ ሲሆን ለማህበረሰቡ ያለው ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊው ፋይዳው እጅግ የጎላ ነው ብለዋል።
የአካባቢው ማህበረሰብ በጉልበቱ ብሎም በገንዘቡ ያደረገው ከፍተኛ አስተዋፅኦ የወረዳው መንግስት ትልቅ ምስጋና አለው ያሉት አቶ ኢብራሂም መንገድ የአገልግሎት ጊዜው በአግባቡ ለማቆየት ባለቤት ሆኖ በንቃት መጠበቅ እንዳለበት መልዕክት አስተላልፈዋል።
አስተያየት የሰጡን የቀበሌው ነዋሪዎች በበኩላቸው የመንገድ ግንባታው ለረጅም ዘመናት የሚፈልጉት በመሆኑ በዚህ መልኩ ሁሉም አካባቢዎች በሚያገናኝ መልኩ በመሰራቱ እንዳስደሰታቸው ገልፀዋል።
አስተያየት ሰጪዎቹ አክለውም ቀበሌያቸው ከፍተኛ አምርች አርሶአደር ያለበትን በመሆኑ ምርቶቻቸውን ለገበያ ለማቅረብ ሰፊ እድል የሚፈጥር እንደሆነና በአጠቃላይ ከቦታ ወደ ባታ ለተለያዩ ጉዳዮች ለመንቀሳቀስ ተሽከርካሪን በመጠቀም ጊዜና ጉልበታቸውንም ጭምር እንዳይባክን የሚያደርግ በመሆኑ ለዚህ አስተዋፅኦ ያደረጉላቸው አካላት በሙሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል ሲል የዘገበው የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው።