
እዣ ወረዳ በጉራጌ ዞን ከሚገኙ እጅግ አስደናቂ የሆኑ ታሪካዊ ፡ ተፈጥሮአዊ እና ባህላዊ የሆኑ ለቱሪስት ቀልብ የሚስቦ መስህቦች መገኛ ከሆኑት አካባቢዎች ውስጥ በግንባር ቀደም ተጠቃሽ ስትሆን እጅግ ማራኪና የአየር ንብረ ለውጥ ለመከላከል የሚያስችሉ ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ ደኖች ፡ ውብና ማራኪ ፏፏቴዎች ፡ ትክል ድንጋዮች ፡ ጥንታዊና በውስጣቸው እድሜ ጠገብ ቅርሶችን የያዙ ገዳማት ፡ መስጂዶች እና ካቴድሪያሎች ተጠቃሾች ናቸው ።
ከነዚህም መካከል እንደናኪያር ፏፏቴ የሚገኘው በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ ከአገና ከተማ በ3 ኪሜትር ገደማ ዌራደባነ ቀበሌ ውስጥ ይገኛል።
ቦታው የተለያዩ የተፈጥሮ እፅዋእቶች አጅበውት የአረንጓዴ ልምላሜ መገለጫ ከመሆኑም በተጨማሪ የአእዋፍ ዝማሬው የተለያዩ የዱር አራዊቶች በውስጡ ይገኛሉ ።
የፏፏቴው መገኛ ቦታ መንገድ ዳር በመሆኑ እጅግ ለመዝናናት ተመራጭ ያደርገዋልና ቦታው በመሄድ ጥሩ ትዝታ ያኑሩ መልዕክታችን ነው ።






