የእዣ ወረዳ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት

ከሀገሪቱ እድገት ምጣኔ የተመጣጠነ የህዝብ ቁጥር እንዲኖር ባለድርሻ አካላት በትኩረት መስራት እንዳለባቸው ተገለፀ።

===========================

ከሀገሪቱ እድገት ምጣኔ የተመጣጠነ የህዝብ ቁጥር እንዲኖር ባለድርሻ አካላት በትኩረት መስራት እንዳለባቸው ተገለፀ።
የእዣ ወረዳ ፕላን ልማት ፅ/ቤት ለትምህርት ቤት የስነ-ህዝብ ክበባት ተጠሪ መምህራን እና ለባለድርሻ አካላት ስልጠና ሰጥቷል ።
የፅ/ቤቱ ሀላፊ አቶ ሰለሞን ዘርጋ በስልጠናውም ወቅት እንደገለት ስነ-ህዝብ ማለት የህዝብ ብዛት ስብጥር ፍልስት እንዲሁም የነዋሪዎች የአሰፋፈር ሁኔታ በአጠቃላይ በማህበረሰቡ ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊና አስተዳደራዊ ጉዳዮች ላይ የሚያሳድረውን አዎንታዊ ሆነ አሉታዊ ተፅዕኖዎችን የሚያጠና እና መፍትሔ የሚጠቁም ሳይንስ ነው ።
ፈጣን የህዝብ ቁጥር እድገት በአግባቡ ካልተመራ በሀገር ኢኮኖሚ ላይ ከባድ ተጽዕኖ እንደሚፈጥር ጨምረው የገለፁት ሀላፊው በተጨማሪም በህዝብ ቁጥር መጨመር የመሬት ጥበት መፈጠሩ ደግሞ የሠው ልጅ በልቶ ለማደር ወይም ኑሮን ለማሸነፍ ሲባል በደን መጨፍጨፍ ምክንያት የአፈር መሸርሸር በማስከተል መሬት ምርታማነት እንዲቀነስ የሚያደርግ መሆኑ በጥልቀት መገንዘብ ያስፈልጋልም ብለዋል።
በመሆኑም የሰነ-ህዝብ ክበባት በትምህርት ቤት የህዝብ ቁጥር መጨመር ያለው ተፅእኖ ከቤተሰብ አቅሞ ጋር የተገናዘበ የቤተሰብ ብዛት ያለውን ጠቀሜታ እና የወጣቶች ስነ-ልቦናዊ ችግሮች በመለየት በትምህርት ቤት እና በተገኘው አጋጣሚ በስነ-ፅሁፍ በጭውውት በጥያቄ መልስ ወዘተ ግንዛቤ መፍጠር እንደሚገባም አቶ ሰለሞን መልዕክት አስተላልፈዋል ።
በፅ/ቤቱ የስነህዝብ ስራ ሂደት አስተባባሪ ወ/ሮ ሰፊነሽ ሺሰማ የስልጠናው ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን በሰነዱም ያልተመጣጠነ ፈጣን የህዝብ ቁጥር እድገት በህብረተሰቡ ገቢና ፡ የአኗኗር ዘይቤ እና በኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እድገት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እንዳለውም አመላክተዋል ።
በመሆኑም በትምህርት ቤቶች የስነ ህዝብ ክበባትን በማጠናከር ለተማሪዎችና ለህብረተሰቡ ግንዛቤ መፍጠር እንደሚያስፈልግም ወ/ሮ ሰፊነሽ አሳስበዋል።
የስልጠናው ተሳታፊዎች የተሰጠው ግንዛቤ ጥሩ መሆኑንና እና በቀጣይ ጊዜ የስነ-ህዝብ ክበባት በትሞህርት ቤት የተሰሩ ተግባራት በማጠናከር በዘርፉ የሚፈለገውን ውጤት እንዲመዘገብ መስራት ያስፈልጋልም ብለዋል ሲል የዘገበው የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው ።