

*=============================*
የመምህራን ስልጠና በይፋ ስለመጀመሩ:
የካቲት 11-16 ድረስ ጋበር ከወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በተመረጡ የት/ርት ዘርፎች ላይ በአጠቃላይ ለ153 የመካከለኛና ከ/2//ደረጃ ት/ቤቶች መምህራን የሚሰጠው የአቅም ማጎልበቻ ሥልጠና በይፋ ተጀምሯል። በመክፈቻውም የዩኒቨርሲቲው ተወካዮች ረ/ፕ አበበ ያበኬር (Industry linkage Director) እና ረ/ፕ ቸርነት ዘርጋ (Director for Community Service) እንዲሁም የኧዣ ወረዳ መስተዳድር፣ የት/ት ፅ/ቤትና የጋበር ሥራ አስኪያጅ በተገኙበት መምህራን ስልጠናውን በከፍተኛ ትኩረትና ጥብቅ ሥነ-ሥርአት ይከታተሉ ዘንድ በማሳሰብ በይፋ እንዲጀመር አድርገዋል። ሰልጣኝ መምህራንም የሚወስዱት ስልጠና ውጤት የሚታየው ተማሪዎቻቸው ላይ እንደሆነ የመክፈቻ ፕሮግራሙ ላይ ከአደራ ጭምር ተነግሯቸዋል ከዚህም በተጨማሪም አሁን ከሚሰለጥኑት መካከል ተመርጠው ወደፊት አቅም በፈቀደ መጠን ከ1-6 ክፍል ለሚያስተምሩ መምህራን ከጋበር ጋር በመተባበር የሸመቱትን እውቀት እንዲያወርዱት ጥረት እንደሚደረግም ተገልፆላቸዋል። በዚህ አጋጣሚ ስልጠናው የሚሰጥበትን ክፍሎችና ቁሳቁሶች ለአስልጣኞች የመጠጥ ውሐ ጭምር በማቅረብ ታላቅ ትብብር ያደረገልንን የአገና ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪ ኮሌጅን እጅግ አድርገን እናመሰግናለን!!
ጋበር የበጎ/አ/ድ







