




====የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አገና ቅርንጫ እዣ ወረዳ ለአርሶአደሮች የግብርና ብድር አገልግሎት ላይ ለባለድርሻ አካላት ግንዛቤ ሰጠ ።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለባለአነስተኛ ይዞታና ለተደራጁ አርሶ አደሮች የሚሰጥ የግብርና ብድር አገልግሎት በወረዳ ደረጃ ለማስጀመር የፊርማ ስነ ስርአት መከናወኑን ይታወቃል ።
በዛሬው እለትም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እዣ ወረዳ ለአርሶአደሮች የግብርና ብድር አገልግሎት ላይ ለባለድርሻ አካላት ግንዛቤ ሰጥቷል ።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተወካይ እትእንዳሉት፥ ንግድ ባንክ አዳዲስ አገልግሎቶችን በመተግበር ቀልጣፋና አስተማማኝ አገልግሎት እየሰጠ ነው ብለዋል።
የፋይናንስ አገልግሎት ተደራሽነትና አካታችነትን ይበልጥ ለማሳደግም በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸው፤ በተለይም ለግብርና ዘርፍ የሚሰጠውን የብድር አገልግሎት ለማስፋትና ለማጠናከር ትኩረት ተደርጓል ብለዋል።
ባንኩ ለአርሶ አደሮች የግብርና ስራዎችን ለማሳደግ ልዩ የብድር አገልግሎት ማስጀመሩ የገጠር ኢኮኖሚ ዕድገትን ለማሳደግ ያስችላል ነው ያሉት።
በአገልግሎቱ የእርሻ መሬት ያላቸው፣ በኩታገጠም በቡድን የተደራጁ፣ በባንኩ 6 ወርና ከዚያ በላይ የቆጠቡ፣ በሰብል ልማት፣ በአትክልትና ፍራፍሬ፣ በወተትና ወተት ተዋጽኦ እንዲሁም በእንስሳት ሀብት ልማት የተሰማሩ አርሶ አደሮች ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሏል።






