
======================
የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አገልግሎት ጥራትና ተደራሽነት ለማሻሻል የእዣ ወረዳ ጤና ጥበቃ ፅ/ቤት ከወልቂጤ ዩኒቨርስቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እና ከአጣጥ ሆስፒታል ውል መፈፀሙን ተገለፀ ።
የእዣ ወረዳ ጤና ጥበቃ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ መሀመድ ሰይድ እንደገለፁት በወረዳው ማህበረሰቡ በጤናው ዘርፍ በህመሙ ልክ የህክምና አገልግሎት እንዲያገኝ የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆን በትኩረት እየተሰራ ይገኛል ።
በመሆኑም የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አገልግሎት ጥራትና ተደራሽነት ለማሻሻል የእዣ ወረዳ ጤና ጥበቃ ፅ/ቤት ከወልቂጤ ዩኒቨርስቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እና ከአጣጥ ሆስፒታል ውል መፈፀሙን ሀላፊ ገልፀዋል ።
የስምምነቱ ዋና አላማ የማዐጤመ ቤተሰቦችና አባላት በጤና አገልግሎት ያለምን እንግልት መጠቀም እንዲችሉ ነው ያሉት አቶ መሀመድ በዚህም ውል ከምርመራ ወይንም ማማከር አገልግሎት ጀምሮ ትኝቶ እስከመታከምና በርካታ የህክምና አይነቶች ማህበረሰቡ በነፃ መታከም የሚችልበት እድል እንደሆነም አብራርተዋል ።
ማህበረሰቡም ይህንኑ በመገንዘብ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ሊሆን ይገባል ያሉት ሀላፊው እንደ ወረዳ የማዐጤመ ተጠቃሚዎች ሽፋን ወደ 100 % ለማድረስ በሚደረገው ጥረት በወቅቱ በማደስና አባል በመሆን የእድሉ ተጠቃሚ መሆን እንደሚገባውም መልዕክት አስተላልፈዋል ሲል የዘገበው የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው ።







