የእዣ ወረዳ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት

ጋበር በጎ አድራጎት ድርጅት

ጋበር በጎ አድራጎት ድርጅት በተመሰረት አጭር ጊዜ ውስጥ ያከናወናቸው ማህበረሰቡን ተጠቃሚ ያደረጉ ተግባራቶች በላቀ ደረጃ ለማስቀጠል የሁሉም ርብርብ የሚጠይቅ መሆኑን ተገለፀ ።

ድርጅቱ ለእዣ ወረዳና አገና ከተማ አስተዳደር ሚመለከታቸው አመራሮች በአመራር ሰጪነት እና ስትራቴጂካዊ አስተሳሰብ ዙሪያ ስልጠና ሰጥቷል።

የጋበር ድርጅት የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ኮሬ ባዌ እንደገለፁት በአካባቢው በተለያዩ ዘርፎች ያሉ ችግሮችን ያሳሰባቸው የአካባቢው ተወላጆች ጋበር የተሰኘ የበጎ አድራጎት ድርጅት በማቋቋም የህብረተሰቡን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮችን በዘላቂነት ለመቅረፍ እየተሰራ ይገኛል።

ድርጅቱ በትምህርት ፡ በጤና፡ በግብርናና በሌሎችም ዘርፎች ላይ የማህበረሰቡን ችግር ለማቃለል ባደረገው ስራ ከወዳው መንግስት ጋር በመቀናጀት የተለያዩ ውጤታማ የሆኑ ስራዎች መስራቱንም አቶ ኮሬ ጨምረው ገልፀዋል።

ጋበር በጎ አድራጎት ድርጅት በቀጣይም ከወረዳው አመራርና ከህብረተሰቡ ጋር ተቀናጅቶ የማምረት አቅም እንዲጨምር በግብርናው ዘርፍ ለአርሶአደሩ የትራክተር ድጋፍ ፡ ለአገና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለህክምና ግብዓትና ሌሎችም ስራዎች ለመስራት አልሞ ርብርብ እያደረገ ነውያሉት አቶ ኮሬ ይህም እውን እንዲሆን ከሀገር ውጭ ከሚገኙ የአካባቢው ተወላጅ አንስቶ በተለያየ መልኩ መደገፍ አለበትም ብለዋል።

የእዣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘውዱ ዱላ እንደገለፁት ጋበር በጎ አድራጎት ማህበር እያከናውናቸው ያሉት ተግባራቶች እንደ እዣ ወረዳ ብሎም እንደ ጉራጌ ዞን በራስ አቅም ለህብረተሰቡ ልማቶች እንዲስፋፉና ድህነትን እንዲቀንስ ትልቅ አቅምና መነሳሳት የሚፈጥር ነው ብለዋል።

ጋበር በጎ አድራጎት ድርጅት ከተመሰረት አጭር ጊዜ ያከናወናቸው ማህበረሰቡን ተጠቃሚ ያደረጉ ተግባራቶች በላቀ ደረጃ ለማስቀጠል የሁሉም ርብርብ የሚጠይቅ ነው ያሉት አቶ ዘውዱ ያለማቸህ ስራዎች እንዲሳኩ ማህበረሰቡን በማስገንዘብ የወረዳው መንግስት በትኩረት እየሰራው ያለው ስራ አጠናክሮ ይቀጥላልም ብለዋል።

የአገና ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሀብቴ ዘርጋ በበኩላቸው ጋበር እያደረጋቸው ያሉ በተጨባጭ ለውጥ ያመጡ ስራዎች አርዓያነት ያላቸው ተግባራት በመሆናቸው ሁሉም ከድርጅቱ ጎን ቆሞ የማህበረሰቡ ችግር እንዲፈታ በባለቤትነት ሊንቀሳቀስ ያስፈልጋልም ብለዋል።

ድርጅቱ በአጭር ጊዜ የሰራቸው ስራዎች እጅግ አስተማሪና ማህበረሰቡ የተረዳቸው ናቸው ያሉት አቶ ሀብቴ የከተማ አስተዳደሩም ነዋሪውን በማስተባበር ለጋበር ሁለንተናዊ ድጋፍ ለማድረግ ጥረት ያደርጋልም ብለዋል።

ተሳታፊዎቹም በሰጡት አስተያየትም ይህ ድርጅት ቀጣይነቱ እንዲረጋገጥና ከዚህ አካባቢ አልፎ በሁሉም ጉራጌ አካቢዎች ተሞክሮ እንዲሰፋ በሚያደርገው ጥረት የድርሻቸውን ለመወጣት እንደሚሰሩም ተናግረዋል ።

ከስልጠናው በተጨማሪ አጠቃላይ ጋበር የሰራቸው ተግባራቶች የያዙ ሰነዶች በዶ/ር ደርብ ወ/ዮሀንስ ቀርበው ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸዋል ሲል የዘገበው የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው ።