የእዣ ወረዳ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት

የህዳሴው ግድብ እስኪጠናቀቅ የተለመደውን ድጋፍ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ተገለፀ ።

====================================

የህዳሴው ግድብ እስኪጠናቀቅ የተለመደውን ድጋፍ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ተገለፀ ።
በወረዳው “በህብረት ችለናል ” በሚል መርህ የህዳሴው ግድብ 13ኛ ዓመታት ጉዞና የ2016 ዓም የወረዳው የህዳሴ ቦንድ ግዢ እቅድ ዙሪያ የንቅናቄ መድረክ ተካሂዷል ።
በእለቱም የእዣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘውዱ ዱላ እንደገለፁት ሀገራችን ኢትዮጵያ ከጫፍ እስከ ጫፍ ያነቃነቀው እና የሰንደቅ አላማችን ፕሮጀክት የሆነው ታላቁ የህዳሴ ግድብ በቀድሞ መሪ አቶ መለስ ዜናዊ መጋቢት 24/2003 ዓም መሰረተ ድንጋይ ተቀምጦ ሁሉም ኢትዮጵያዊያን በአንድነት የዘመቱበት በራሳችን አቅም መስራት እንድምንችል ለአለም ያስደመምንበት ነው ።
የተፈጠሩትን በርካታ ፈተናዎች በጠንካራ አመራቅ ሰጪነት እና ጠንካራ ዲፕሎማሲያዊ ጎንኙነት በመፍጠር አሁን ላይ ግድቡ 95 % የደረሰ ሲሆን በሁለት ተርባይኖች 700 ሜጋ ዋት በማመንጨት የውጭ ምንዛሬ ማስገኘት ችሏል ያሉት አቶ ዘውዱ በተጨማሪም በጥቂት ሳምንታት ውስጥ አምስት ተርባይኖች 2000 ሜጋ ዋት ሀይል ማመንጨት የሚጀምሩ እና በ2017 ዓም ፕሮጀክቱ እንደሚያልቅም ይታመናልም ብለዋል ።
በመሆኑም የመጨወሻ የፕሮጀክቱ ማጠናቀቂያ ትልቅ ገንዘብ የሚያስፈልገው በመሆኑ ተገንዝበን የራሳችን የሆነው ፕሮጀክት በታቀደለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ ተጨማሪ ርብርብ በማስፈለጉ የሚፈለግብን የቦንድ ግዢ እያንዳንዱ ቤተሰብ ተግባራዊ እንዲሁን እንደ ወረዳው ጠንካራ ንቅናቄና ዘመቻ በመፍጠር መረባረብ እንደሚገባም አሳስበዋል ።
የእዣ ወረዳ ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ተሾመ ስራኒ በበኩላቸው የህዳሴ ግድብ ቦንድ ግዢ መግዛት የቁጠባ ባህላችን የሚያሳድግ ከመሆኑም በላይ በሀገር ዘላቂ ልማት ላይ አሻራ ማኖር ነውና የወረዳው ማህበረሰብ የግድቡ ግንባታ ስራ እስኪጠናቀቅ እስካሁን እያደረገው የነበረው አስተዋፅኦ አጉልቶ እንዲያስቀጥል የማስገንዘብ ተግባር ጠቃሚ ነው ብለዋል ።
የግድቡ መገንባትና እንደዚህ መድረስ መቻሉ ትላልቅ ፕሮጀክቶች በራስ አቅም ማጠናቀቅ እንደሚቻል ለአለም ያሳየንበት እንዲሁም የኢትዮጵያዊነት ስሜትና ህብረት ጎልቶ የታየበት ነው ያሉት ዋና የመንግስት ተጠሪው እስካሁን በተደረገው አስተዋፅኦ በወረዳችን 6ሚሊየን 213ሺህ 443ብር ቦንድ ግዢ መፈፀሙን አስታውሰዋል።
በዚህ ዙርያም እንደ ወረዳው 747 ሺህ ብር በተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ለመሰብሰብ መታቀዱን የገለፁት አቶ ተሾመ ይህም ካለው ሀገራዊ ፋይዳ በአጭር ጊዜ ለመሰብሰብ መረባረብ ያስፈልጋልም ብለዋል።
በእለቱም የህዳሴ ግድብ አጠቃላይ ገፅታ የእዣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ልዩ አማካሪ በአቶ አሸናፊ በቀለ ሰነድ ቀርቦ ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን ተሳታፊዎችም ይህ የጋራ አርማችን የሆነውን የህዳሴ ግድብ ግንባታ እስኪጠናቀቅ ድረስ ሁለንተናዊ ድጋፋችን እናጠናክራለን ሲሉ በአስተያየታቸው ተናግረዋል ሲል የዘገበው የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው ።