
=================================
ጥቅምት 14/2016 ዓም
የእዣ ወረዳ ግብርና ልማት ጽ/ቤት የ2016 መስኖ ልማትን በማስመልከት ለባለሙያዎች የክህሎት ስልጠና ሰጠ ፡፡
ስልጠናው በተሰጠበት ወቅት የእዣ ወረዳ ግብርና ልማት ፅ/ት ሀላፊ አቶ መቻል ተሰማ እንደገለፁት ይህ በተግባር የተደገፈው የክህሎት ስልጠና በባለፈው ዓመት መስኖ ልማት አፈፃፀም የታዩ የአፈፃፀም ክፍተቶችን የሚያርምና የነበሩትን መልካም ተሞክሮዎችን ለማስቀጠል የሚረዳ መሆኑን ገልፀዋል።
በወረዳው አርሶ አደሩ ባለፉት አመታት የሚታይበትን የአመለካከት ፡የግንዛቤና የክህሎት ክፍተቶች እንዲሞላ የተለያዩ ጥረቶች በማድረግ ከሌላ ጊዜ በተለየ መልኩ የተቀናጀ ስራ መስራት የሚጠይቅበት ወቅት እኖደሆነም ሀላፊው አመላክተዋል።
የፅ/ቤቱ ምክትል ሀላፊ አቶ ተካ ወርቁ በበኩላቸው በዘንድሮ መስኖ ልማትም በዓምና ደረጃ የተስተዋሉትን የአፈፃፀም ጉድለቶች በመለየትና እንዲታረሙ በማድረግ ያሉትን የውሃ አማራጮችን አሟጦ በመጠቀም በተጨባጭ የአርሶ አደሩን የማምረት አቅም ለማሳደግ በተለይም ባለሙያው ሀላፊነቱ ሊወጣ ይገባልም ብለዋል።
በእለቱም ከመስኖ ልማት በተጨማሪ በእንስሳት እርባታ ዘርፍም በሚመለከታቸው የስራ ሀላፊዎች ስልጠና ተሰቷል።
በ2016 ዓም መስኖ ልማት አብዛኛው አርሶአደር ተሳታፊ በማድረግ እና አሁን ያለው የኑሮ ውድነት ጫና ለመቋቋም ከሌላ ጊዜ በተለየ መልኩ ርብርብ እንደሚያደርጉም በክህሎት ስልጠናው ወቅት ያነጋገርናቸው ባለሙያዎች በአስተያየታቸው ተናግረዋል ሲል የዘገበው የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው።







