የእዣ ወረዳ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት

የዲር መስጅድ

======================================

                         የዲር መስጅድ

የዲር መስጅድ የሚገኘው በጉራጌ ዞን በእዣ ወረዳ በቦዠባር ቀበሌ በላይኛው ኢላስ በሚባል ጎጥ የሚገኝ ሲሆን, መስጅዱ ከወረዳው ዋና ከተማ አገና በ28 ኪ.ሜ እና ከዞኑ ዋና ከተማ ወልቂጤ በ58 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በስተምስራቅ አቅጣጫ ይገኛል፡፡ ከቦዠባር ከተማ ትንሽ ከፍ ብለው ከዋናው አስፋልት መንገድ ትንሽ ፒስታ መንገድ በመኪናም ሆነ በእግር ተጉዘው ያገኙታል፡፡ መስጅዱ የተመሰረተው በ1942 በሀጅ መሀመድ ሙዘየር ሲሆን፡፡ የመስጅዱ አሰራር በሳር ክዳን የነበረ ሲሆን አሁን ግን የሳር ክዳኑን ቆርቆሮ ለብሶ እናገኘዋለን፡፡ መስጅዱ አካባቢ በተለያዩ የዛፍ ዝርያዎች የተከበበና ነፋሻማ ተስማሚ የአየር ንብረት ያለበት ስፍራ ነው፡፡ በመስጅዱ ውስጥ ጥንታዊ የሆኑ የሃይማኖት መገለጫና መገልገያ የሆኑ ቁሳቁሶች የሚገኙ ሲሆን, አሁንም አገልግሎት የሚሰጡ ናቸው፡፡ እንግዲህ ውድ አንባቢያን ይህንን ጥንታዊና ታሪካዊ መስጅድ እንድትጎበኙ መልዕክታችን እናስተላልፋለን፡፡ በመጨረሻ አስተያየት ሆነ ጥያቄ ካላቸሁ በስልክ ቁ.0113290217 ሆነ በአካል እ/ወ/ባ/ቱ//ፅ/ቤት በመቅብ መስጠት ትችላላችሁ፡፡