የእዣ ወረዳ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት

በእዣ ወረዳ የተማሪዎች ውጤትና ስነ ሞግባር ለማሻሻል የሚያስችል በወረዳው ለሚገኙ ለ152 መምህራን በወልቂጤ ዩኒቨርስቲ መምህራን ስልጠና እየተሰጠ መሆኑን የወረዳው ትምህርት ፅ/ቤት አስታወቀ ።

*=======================*

በእዣ ወረዳ የተማሪዎች ውጤትና ስነ ሞግባር ለማሻሻል የሚያስችል በወረዳው ለሚገኙ ለ152 መምህራን በወልቂጤ ዩኒቨርስቲ መምህራን ስልጠና እየተሰጠ መሆኑን የወረዳው ትምህርት ፅ/ቤት አስታወቀ ።
ጋበር የበጎ አድራጎት ማህበር ከወልቂጤ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር በአገና ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ እየሰጠ የሚገኘውን ስልጠና ተጠናክሮ መቀጠሉንም ፅ/ገልጿል።
የእዣ ወረዳ ም/አስተዳዳሪና የትምህርት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ተጠምቀ በርጋ የስልጠናው አጠቃላይ ሂደት ተዘዋውረው በተመለከቱበት ወቅት እንደገለፁት እንደ ሀገር ብሎም እንደ ወረዳው የገጠመውን የውጤት ስብራት ለማካካስ በተለይም እንደ በወረዳው የተለይ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ ይገኛል ።
ከነዚህም መካከል እንደ ሀገር የገጠመው የመፅሀፍ እጥረት ችግር ለመፍታት ለመፍታት ከ5ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ከጋበር ድርጅት ጋር በመተባበር ለተማሪዎች ተሰራጭቷል ያሉት ሀላፊው ከዚህ በተጨማሪም ከመምህህራን ፡ ከማህበረሰቡና ከተማሪዎች ጋር በዘርፉ ያሉት ጉለቶች በለየ መልኩ የተለያዩ ውይይቶችና የስልጠና መድረኮች ተካሂደዋል ብለዋል ።
አሁን እየተሰጠ ባለው ስልጠና ከ9 – 12ኛ እንግሊዝኛ ማትስ ፡ ፊዚክስ ፡ ኬሚስትሪና ኢኮኖሚክስ የሚያስተምሩ መምህራን እንዲሁም ከ7-8ኛ የሚያስተምሩ እንግሊዝኛና ማትስ መምህራን ስልጠናው እየተሰጣቸው ይገኛ ያሉት አቶ ተጠምቀ በአጠቃላይ 152 መምህራን በወልቂጤ ዩኒቨርስቲ 2ኛ ዲግሪና 3ኛ ዲግሪ ያላቸው መመህራን ስልጠናው እየሰጡ መሆኑንም አብራርተዋል።
እነዚህ መምህን ይህን ስልጠና ማግኘታቸው በቀጣይ በተማሪዎች ውጤትና ስነ-ምግባር ለውጥ ማምጣት እንደሚያስችስ አቶ ተጠመቀ ተናግረዋል ።
ስልጠናው ከየካቲት12/2016 ዓሞ ለተከታታይ 6ቀናት በመሰጠት ላይ ይገኛል ያሉት ሀላፊው መጪው ቅዳሜ የካቲት 16/2016 ዓም ማጠቃለያና የሰርተፊኬት ፕሮግራም እንደሚኖርም ጠቁመዋል ።
ለዚህም ስልጠና የበጀት ድጋፍ ያደረገው ጋበር የበጎ አድራጎት ማህበር ትልቅ ምስጋና ይገባዋስ ያሉት አቶ ተጠምቀ መምህራንም የሰለጠኑትን ስልጠና በቀጥታ ለሌሎች መምህራን ጭምር በማሰልጠን እንደ ወረዳው በተማሪዎች ውጤትና ስነ-ምግባር ላይ መሰረታዊ ለውጥ እንዲመጣ ፅ/ቤቱ የተጠናከረና ዘላቂነት ያለው ድጋፍና ክትትል ያደርጋልም ብለዋል።
በስጠናው እየተካፈሉ የሚገኙ መምህራኖች በሰጡት አስተያየትም ይህ ስልጠና እጅግ አስፈላጊ የሆነ ተጨማሪ እውቀት እየቀሰሙበት እንደሆነና በተማሪዎች ውጤትና ስነ ምግባር መሻሻል ላይ ለውጥ ማምጣት የሚያስችል ስልጠና በመሆኑ በንቃት እየተከታተሉ መሆኑንም በአስተያየታቸው ተናግረዋል ሲል የዘገበው የእዣ ወዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው ።