የእዣ ወረዳ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት

ኮሌጆች ችግር ፈቺ የሆኑ ቴክኖሎጂዎችን በአግባቡ በመለየት ፣ በመቅዳትና በማሸጋገር ለተጠቃሚው ህብረተሰብ ክፍል ለማድረስ በትኩረት መስራት እንዳለባቸው ተገለፀ።

============================

ኮሌጆች ችግር ፈቺ የሆኑ ቴክኖሎጂዎችን በአግባቡ በመለየት ፣ በመቅዳትና በማሸጋገር ለተጠቃሚው ህብረተሰብ ክፍል ለማድረስ በትኩረት መስራት እንዳለባቸው ተገለፀ።
የአገና ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ የቦርድ አባላት የ2016 በጀት ዓመት የ6ወራት የኮሌጁ እቅድ አፈፃፀም ገምግሟል ።
የጉራጌ ዞን ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና መምሪያ ሀላፊ አቶ መስፍን ሰርገማ በውይይቱ ወቅት እንደገለፁት ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ለአንድ ሀገር ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖሊቲካዊ ዕድገት ቁልፍ መሳሪያ ነው ።
በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተራቀቁና በኢኮኖሚ ያደጉ ሀገራት ከዚህ የደረሱት የሰው ሀይል አቅማቸውን በትምህርትና ስልጠና በመገንባታቸው ነው ያሉት ሀላፊው ከዚህም አንፃር ኮሌጆች አገር አቀፍ የሙያ ደረጃና የሙያ ብቃት ምዘና ሥርዓት በጠበቀ መልኩ በተለያየ መንገድ እውቀትና ክህሎት የጨበጡ የማህበረሰብ አባላት በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሚሆኑበትን ሁኔታ የማመቻቸት ሀላፊነት አለባቸው ብለዋል ።
በዞኑ ከሚገኙ ቴክኒኪና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት ግንባር ቀደም ከሆኑ የአገና ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ አንዱ ነው ያሉት አቶ መስፍን ኮሌጁ የሰለጠነ የሰው ሀይል በማፍራት ችግር ፈቺ የሆኑ የቴክኖሎጂ ውጤቶች አምርቶ ከማስተዋወቅ አንፃር እያከናወናቸው የሚገኙ ተግባራቶች እጅግ የሚበረታቱ መሆኑን አመላክተው በጉለት የተጠቁሱት በቀጣይ በጉለት የተጠቀሱ ጉዳዮች በማሻሻልና የራሱ አቅም በማዳበር የተሻለ ተግባር ላይ ትኩረቱ ማጠናከር እንዳለበትም አስገንዝበዋል።
የአገና ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሀብቴ ዘርጋ በቴክኖሎጂና በምርምር ስራዎች የማህበረሰቡ ችግር በዘላቂነት በመፍታቱ ረገድ የቴክኒክና ሙያ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረክታሉ ብለዋል ።
በዕውቀትና በክህሎት ያደገ ማህበረሰብ ቴክኖሎጂ የመፍጠርና የመጠቀም አቅሙ ያድጋል ያሉት ከንቲባው የአገና ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅም የሰለጠነ የሰው ሀይል ከመፍጠሩም ባለፈ ማህበረሰቡ በተጨባጭ ተጠቃሚ እንዲሆን በቴክኖሎጂ ሽግግር ደረጃ የሚታዩ ስራዎች መስራቱን አመላክተዋል ።
ኮሌጁ ከዚህ በላይ ለመስራት ማነቆ የሆነበትን ችግሮች ቶሎ እንዲቀረፉ ለማድረግ የከተማ አስተዳደሩ በተቻለው አቅም ድጋፍ ያደርጋል ያሉት አቶ ሀብቴ በተለይም የሰልጣኞች ቁጥር ለማሳደግ የሚመለከተው ባለድርሻ አካል ትምህርታቸው ያጠናቀቁ ወደ ተቋሙ ገብተው እንዲሰለጥኑ የግንዛቤ ስራው በቅንጅትና በባለቤትነት በመውሰድ መስራት ያስፈልጋልም ብለዋል።
የአገና ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ዲን አቶ አስቻለው ስባኒ የግማሽ ዓመት ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን ለአምራች እና አገልግሎት ሰጭ ኢንዱስትሪዎች መለስተኛና በመካከለኛ ደረጃ ብቁ ሙያተኞችን በማዘጋጀት ሀገራችን ወደ ኢንዱስትሪ መር ኢኮኖሚ ለመሸጋገር ለምታደርገው ጥረት ቴክኒክኔ ሙያ ተቋማት ወሳኝ ዕገዛ እያደረጉ መሆናቸው የሚታመን ነው ብለዋል ፡፡
በኮሌጁ በ2016 በጀት ግማሽ ዓመቱ በግማሽ ዓመቱ ከተከናወኑት ዋና ዋና ተግባራቶች መካከል ምርጥ ተሞክሮ ሊወሰድበት በሚችል ደረጃ የአሰራር ስርዓት ሰነዶች ማዘጋጀት መቻሉ ፡ ተከታታይነት ያለው የአቅም ግንባታ ስልጠና ለባለሙያ/ለአመራር መስጠት መቻሉ ፡ አረንጓዴ ተቋም መፍጠር ላይ አበረታች ለውጥ መኖሩን ተግባራዊ ጥናትና ምርምር ስራዎች በተሻለ ጥራት ደረጃ እየተሰሩ መሆኑንና ሌሎችም ስራዎች መሰራታቸውን የኮሌጁ ዲን በሪፖርቱ አመላክተዋል።
በቀጣይም ችግር ፈቺ የሆኑ ቴክኖሎጂዎችን በአግባቡ በመለየት፣ በመቅዳትና በማሸጋገር ለተጠቃሚው ህብረተሰብ ክፍል ከማድረስ አኳያ ያሉትን ችግሮች እንዲፈቱ ለማድረግ ከኮሌጁ ድርሻ በተጨማሪ የሚመለከተው አካል በተቀናጀ መንገድ እንዲፈታ አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረግ እንደሚያስፈልግም አቶ አስቻለው ጨምረው ተናግረዋል።
በእለቱም የጉራጌ ዞን ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና መምሪያ ሀላፊ አቶ መስፍን ሰርገማ ፡ አቶ ኸይሩ አህመዲን የወልቂጤ ፖሊቴክኒክ ዲን ፡ አቶ አበበ ባበኬር በወልቂጤ ዩኒቨርስቲ የማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፍ ሀላፊ ፡ የእዣ ወረዳ እና አገና ከተማ አስተዳደር የቦርድ አባል አመራሮች የኮሌጁ የማኔጅመንት አባል በውይይቱ ተሳታፊ ሆነዋል።
በተጨማሪም የኮሌጁ መተዳደሪያ ደንብ ቀርቦ የፀደቀ ሲሆን በኮሌጁ እየተከናወኑ የሚገኙ የቴክኖሎጂ ሽግግር ስራዎች የቦርድ አባላቱ ተዘዋውረው ጎብኝተዋል ሲል የዘገበው የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮቾ ፅ/ቤት ነው ።