የእዣ ወረዳ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት

የማህበረሰቡ የተሻሻለ መፀዳጃ ቤት ሽፋንን በማሰደግ ከተለያዩ ተላላፊ በሽታዎች እራሱን መከላከል እንዲችል በትኩረት መሰራት እንዳለበት የእዣ ወረዳ ጤና ጥበቃ ፅ/ቤት አስታወቀ ።

=====================

የማህበረሰቡ የተሻሻለ መፀዳጃ ቤት ሽፋንን በማሰደግ ከተለያዩ ተላላፊ በሽታዎች እራሱን መከላከል እንዲችል በትኩረት መሰራት እንዳለበት የእዣ ወረዳ ጤና ጥበቃ ፅ/ቤት አስታወቀ ።
ፅ/ቤቱ ሜዳ ላይ ከመፀዳዳት ነፃ የሆነ ቀበሌያት በመፍጠር እና የገበያ መር ስነ-ንፅህና ግብይት ማዕከላት ማስፋፋት ትኩረት ያደረገ የንቅናቄ መድረክ ከባለድርሻ ጋር አካሂዷል።
የእዣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘውዱ ዱላ በዚሁ እለት እንደገለፁት በሀገራችን ብሎም እንደ ወረዳው ህብረተሰቡን በጤናው ዘርፍ ተጠቃሚነቱ ለማረጋገጥ መከላከልን መሰረት ያደረገ የጤና ፖሊሲ ተቀርፆ ለረዥም ዓመታት ሲተገበር ቆይቷል ፡፡
በወረዳው ባለፉት ዓመታት ጤናው የተጠበቀ አምራች ማህበረሰብ ለመፍጠር ርብርብ ሲደረግ መቆየቱን ጨምረው የገለፁት ዋና አስተዳዳሪው በሂደቱም የተደራጀና የተጠናከረ የጤና ልማት ሰራዊት በመገንባት የተሰሩ አበረታች ስራዎች ቀጣይነት ባለው መልክ እንድሄዱ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን እንድወጣ ጥሪ አቅርበዋል።
እንደ ወረዳው ከዚህ በፊት የተሻሻለ ሽንት ቤት ግንባታ ስራ በማስፋፋት በርካታ ተላላፊ በሽታዎችን መቀነስ መቻሉን ያነሱት አቶ ዘውዱ በአሁን ሰዓት እየተስተዋሉ ያሉት መዘናጋቶች ለማስተካከል በየደረጃው አደረጃጀቶች በመጠቀም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በትኩረት መሰራት እንደለት አሳስበዋል ።
የእዣ ወረዳ ጤና ጥበቃ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ መሀመድ ሰይድ በበኩላቸው ማህበረሰቡ የተሻሻለ መፀዳጃ ቤት ሽፋንን በማሰደግና ከተለያዩ ተላላፊ በሽታዎች እራሱን መከላከል እንዲችል በትኩረት መሰራት አለበት።
ሽንት ቤት ገንብቶ መጠቀም ታክሞ ለማዳን አዳጋች የሆኑ በሽታዎች ለመከላከል የሚያስችል ነው ያት ሀላፊው ይህንኑ በመገንዘብ እያንዳንዱ ቤተሰብ የተሻሻለ መፀዳጃ ቤት በመጠቀም አየራች ህበረሰብ መገንባት ያስፈስጋልም ብለዋል።
በቀጣይም የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች በሙሉ ጊዜያቸው ዶጋፍ በማድረግ ፡ የቀበሌ ሴቶች ልማት ቡድን በማጠናከር በአጠቃላይ የድጋፍና መሠል ጉዳዮች በቅንጅትና በትኩረት በመስራት ተግባሩ እንዲሳካ መረባረብ እንደሚገባ አቶ መሀመድ መልዕክታቸው አስተላልፈዋል።
በጤና ተግባር ሞዴል ቀበሌ መፍጠር ጤናማና አምራች ዜጋን ለመፍጠር ፋይዳው የጎላ መሆኑን የነበሩ ጉለቶችን በማረም ሁሉም ማህበረሰብ የተሻሻለ የመፀዳጃቤት እኖዲኖረው የድርሻቸውን ለመወጣት መዘጋጀታቸውን ተሳታፊዎች በአስተያየታቸው ተናግረዋል ሲል የዘገበው የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው ።