
================================
በህብረተሰቡ የነቃ ተሳትፎ ከተሞች የማስፋፋትና የማሳደግ ስራ በመስራት ለነዋሪዎች ምቹ እንዲሆኑ የተቀናጀ ስራ መስራት እንደሚገባ የእዣ ወረዳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ፅ/ቤት አስታወቀ ።
ፅ/ቤቱ ትጉህና አገልጋይ ሲቭል ሰርቪስ ለብልፅግናችን በሚል መርህ ከተቋም ባለሙያዎችና ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሂዷል።
የእዣ ወረዳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ጌታቸው አየለ እንደገለፁት የከተሞችን ደረጃና የህዝቡን አዳጊ ፍላጎት ታሳቢ ያደረገ ስትራቴጂያዊ አመራር በመስጠት በብቃት ደግፎ ማሻገርና የነገ ዘመናዊ ከተሞችን የመገንባት ጉዞ ከወዲሁ መስራት ይጠበቃል።
እንደ ወረዳው በማዘጋጃ ቤቶች የሚሰጠው አገልግሎት ቀልጣፋ፣ ውጤታማና ተደራሽ እንዲሆን ለማድረግ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን በመስጠት ተቋማዊ የማስፈፀም አቅም ለመገንባት ሰፊ ጥረት የተደረገ ይገኛል ያሉት ሀላፊው ሆኖም ግን በከተሞች የሚሰጠው አገልግሎት አሁንም የቅልጥፍና፣ የፍትሀዊነት እና የጥራት ጉድለት በሚፈለገው ደረጃ ከመፍታት ጋር ቀሪ ስራዎች የሚጠይቁ መሆናቸውንም ጠቁመዋል።
ከመሰረተ ልማቶች አንፃር በእስካሁን ሂደትም በከተሞች 13.19 ኪ.ሜ የአዲስ መንገድ ጠረጋና ከፈታ ፣ የ 11.675 ኪ.ሜ የአዲስ ጠጠር መንገድ ግንባታ ፣ እንዲሁም 8.9 ኪ.ሜ የነባር ጠጠር መንገድ ጥገናና ደረጃ ለማሻሻል ለማከናወን ተችሏል ያሉት አቶ ጌታቸው በ2016 በጀት ዓም 9 ወራት ውስጥ በመኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበር ፕሮግራም 26 ቤቶች ግንባታ ለማስጀመር መቻሉ ፣በግለሰብ 30 ቤቶች ግንባታ ፣ የድሃ ድሃ ቤት ግንባታ 2 እንዲሁም 16 በገጠር የልማት ማዕከላት የተሻሻሉ ቤቶች መገንባት መቻሉንም አብራርተዋል።
እንደ ወረዳው ከተሞች በፕላን እንዲመሩ ድጋፍና ክትትል በማድረግ አገናን ወደ ፍረጅ 3 ለማሳደግ የተቻለ ሲሆን ዳርቻ ዝግባቦቶ ወደ ማዘጋጃ ቤት ለማሳደግ መስፈርቱ እንዲያሟላ ዝግጅቱ ተጠናቆ የክልሉ ሰርተፍኬት እየጠበቅን እንገኛለን ያሉት ሀላፊው በቀጣይም በከተሞች የተለዩትን የአፈፃፀም ጉለቶች ቶሎ እንዲታረሙ በማድረግ ከተሞች ምቹ ፡ ውብና ለነዋሪዎች የሚመቹ እንዲሆን የተጠናከር ድጋፍና ክትትል ስራ ይሰራልም ብለዋል።
የፅ/ቤቱ ም/ሀላፊና የአቅም ግንባታ ዘር አስተባባሪ አቶ ኑራዲስ ነስሩ እንደ ወረዳው በከተሞች የተጀመሩ ልማቶችን በተሻለ ፍጥነት ለማስቀጠልና ሌብነትንና ብልሹ አሰራሮችን ለማክሰምና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በአግባቡ መመለስ ይቻል ዘንድ ከሚመለከታቸው አካላት እና የአገልግሎት ተቀባዩ የህብረተሰብ ክፍል ጋር ውይይት መደረጉንም አስታውሰዋል።
ከተሞች የአስተዳደር ወሰናቸው በአግባቡ ማካለል እና የመሬት ይዞታዎች በአግባቡ በመለየት የመሬት ወረራን መከላከል ይገባል ያሉት ም/ሀላፊው ከዚህ በተጨማሪም ከተሞች ያላቸው የመሬት ሀብት በአግባቡ በመጠቀምና የሊዝ ገንዘብን በመሰብሰብ እድገታቸውን ማፋጠን አለባቸውም ብለዋል ።
በቀጣይም እንደ ወረዳው የከተሞች እውቅና አሰጣጥ ፣የፈርጅ ለውጥ አሰጣጥ፣ ከተሞች ፈርጃቸውን የሚመጥን አገልግሎት መስጠት ይገባል ያሉት አቶ ኑራዲስ መመሪያውን የተከተለ የቀበሌ አደረጃጀት ፣ የተጠናከረ የከተማ-ገጠር ቀበሊያት ትስስር በመፍጠር ከተሞቻችን ደረጃጀውን የሚመጥን አገልግሎት እንዲሰጡ በትኩረት መሰራት እንዳለበትም አሳስበዋል።
በእለቱም የመወያያ ሰነድ ቀርቦ ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን ወጣቱ ስራአጥ ሆኖ እንዳይኖር በከተሞች የስራ እድል እንዲፈጥሩ የመሬት አቅርቦትና ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮ ማሟላት ፡ የመሰረተ ልማት አቅራቢአዎች ከከተሞች ጋር በቅንጅት በመስራት የፕላን ጥሰትና ጥራትን በህብረተሰብ ተሳትፎ ማስጠበቅ እንደሚገባም የጋራ ግንዛቤ ተይዞአል።
ከተሞች እድገት ማነቆ የሆነው ህገወጥ ግንባታና የመሬት ወረራ ለመከላከል የድርሻቸውን እንደሚወጡም ተሳታፊዎች በአስተያየታቸው ተናግረዋል ሲል የዘገበው የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው






