


========የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ በአግባቡ በመስራት ግብርናውን በማዘመን ህብረተሰቡን ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለማሸጋገር አጋዥ የሆነውን SLM ፕሮጀክት በአግባቡ ውጤታማ እንዲሆን መስራት እንደሚገባ ተገለፀ።
በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ የSLM/RLLP2/ የሩብ ዓመቱ አፈፃፀም ላይ ትኩረት ያደረገ የወረዳው አብይ ኮሚቴ ውይይት አካሂዷል ።
የእዣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘውዱ ዱላ እንዳሉት እንደ ወረዳው በሚያከናወኑ ዘላቂነት ያላቸው የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራዎች እንዲጠናከሩ SLM ፕሮጀክት የራሱ ድርሻ ለመወጣት ያለመ በመሆኑ በአግባቡ እንዲከናወን ሁሉም ቅንጅት መስራት ያስፈልጋልም ብለዋል።
ፕሮጀክቱ በአፈርና ውሃ ጥበቃ ፡ በምርትና ምርታማነት እድገት እና በአርሶ አደር ኑሮ መሻሻል ላይ ከፍተኛ ውጤት ሊያመጣ የሚችል በመሆኑ የሚመለከታቸው ተቋማት ለአርሶአደሩ አስፈላጊውን ግንዛቤ እንዲኖረው በማድረግ ተጠቃሚ የሚሆንተት መንገድ መፈጠር እንደሚገባም አመላክተዋል ።
በቀጣይም እንደ ወረዳው የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራዎችን በማጠናከር ፡ ግብርናውን በማዘመን ህብረተሰቡን ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለማሸጋገር እያደረገ ያለው ጥረት በተሻለ ደረጃ ማስቀጠል ይገባል ያሉት አቶ ዘውዱ ፕሮጀክቱም እንደ ወረዳው ውጤታማ እንዲሆን ሁሉም በትኩረት በተቀናጀ መንገድ በመስራት ከድህነት የተላቀቀ ህብረተሰብ የመፍጠ ስራ መስራት ያስፈልጋልም ብለዋል።
የእዣ ወረዳ ግብርና ልማት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ መቻል ተሰማ በፕሮጀክቱ እስካሁን የተከናወኑና የቀጣይ ተግባራቶች ላይ ትኩረት ያደረገ ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን በሰነዱም በየንዑስ ተፋሰስ ተጠቃሚዎች ህብረት ስራ ማህበር ለማደራጀት በ9ኙም ንዑስ ተፋሰሶች መስራች ጉባኤዎች በመፍጠር በተለያየ መልኩ የግንዛቤና ስራዎቾ በመስጠት በርካታ ተግባራቶች መከናወናቸውን አመላክተዋል ።
የችግኝ ጣቢያዎች የሚሆኑ የተለያዩ የግብዓትና ሌሎችም አስፈላጊ ስራዎች መከናወናቸውን የገለፁት ሀላፊው በክላይሜት ስማርት አግሪከልቸር ላይ ፕሮጀክቱ ባቀፋቸው ተፋሰሶች የአርሶአደሩ ምልመላና ቡድን የማደራጀት ስራ የመስራትና በቡድን በማደራጀት ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል ብለዋል።
በቀጣይም የተደራጁ ቡድኖች ሁሉም ወደ ስራ መግባታቸው መከታተል ፡ የግንባታ ቦታዎች በመለየትና ወደ ግንባታ እንዲገቡ ማድረግ ፡ የችግኝ ጣቢያ ስራዎችን ማጠናከር እና ሌሎችም የድጋፍ አግባቦች የማጠናከር ስራ ትኩረት ተሰጦቷቸው ይሰራሉ ያሉት አቶ መቻል ይህም ስኬታማ እንዲሆን ሉም ባለድርሻ አካላት የድርሻቸውን መወጣት እንዳለባቸውም አስገንዝበዋል ።
አንዳንድ አስተያየት የሰጡት የፕሮጀክቱ አባይ ኮሚቴ አባላትም ፕሮጀክት ስራ ከጀመረ አጭር ጊዜ ውስጥ የተከናወኑ ተግባራቶች የሚበረታቱ ሲሆን በቀጣይም ፕሮጀክቱ ለተባለለት አላማ በአግባቡ እንዲውል በተቀናጀ መንገድ መስራት እንደሚያስፈልግም ተናግረዋል ሲል የዘገበው የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው።







