


የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ሱፐር ቪዥን ቡድን በእዣ ወረዳው በፓርቲና በመንግስት ደረጃ የተከናወኑ ስራዎች ተዘዋውሮ ከተመለከተ በኋላ ከወረዳው አመራሮች ጋር በመገናኘት የቃል ግብረ መልስ ሰጥተዋል ።
እንደ ወረዳው በፖርቲውና በመንግስት ደረጃ የተከናወኑ ተግባራቶች አደረጃጀቶች በመጠቀም የበለጠ ውጤታማ ማድረግ እንደሚያስፈልግም ተመላክቷል ።
እንደ ወረዳው ለመለወጥ ህዝቡ ላይ ያለው ስሜት እጅግ የሚበረታታ መሆኑንም ተመላክቷል ።
ከተረጂነት ወደ ምርታማነት በሚሰሩ ስራዎች ላይ በራስ አቅም የተለያዩ ስራዎች መሰራታቸውን ገልጸው በቀበሌ ደረጃ ባለቤት በመፍጠርና የተናበበ ስራን በመስራት በዘላቂነት ስራዎች መሰራት እንዳለባቸው አፅኖት ተሰጥቶበታል።
በአጠቃላይ በጤና ፡ በግብርና ፡ በትምህርትና በሌሎችም ዘርፎች ማህበረሰቡ በማሳተፍ የተሰሩ ስራዎች የሚበረታቱ መሆኑንም ተገልጿል ።
በቀጣይም በቀበሌ ደረጃ የአደረጃጀት ስራዎች ማጠናክር እንደሚገባ የተገለፀ ሲሆን በጉለትና በጥንካሬ የተሰጡት አስተያየቶችን በመያዝ አመራሩ ብሎም አባሉ ከማህበረሰቡ ጋር በመቀናጀት መስራት እንደሚያስፈልግም ተመላክቷል ።







