







የካቲት 11/2017 ዓ.ም
የጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ የ2017 ዓ.ም የመምህራን፣ርዕሰ መምህራንና ሱፐርቫይዘር ምዘና፣ የቲቶሪያል ኦሮንቴሽንና ወቅታዊ ስራዎች በተመለከተ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በወልቂጤ ከተማ እያካሄደ ይገኛል።
የጉራጌ ዞን የትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ መብራቴ ወልደማሪያም በመክፈቻ ንግግራቸው እንዳሉት የተማሪዎች ውጤትና ስነምግባር ለማሻሻልና በዘርፉ ውጤታማ ስራ ለመስራት የባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ አሰራር ሚናው የላቀ ነው።
የ2016 የመምህራን ርዕሰ መምህራንና ሱፐርቫይዘር የምዘና አፈጻጸም ግምገማ፣ በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ድጋፍ በተመረጡ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚሰጠው ቲቶሪያል አስመልክቶ ውይይት እንደሚደረግ ገልጸዋል።
በመድረኩም የጉራጌ ዞን ምክር ቤት ሴቶች ህጻናትና ማህበራዊ ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ ጥሩነሽ ምኑታ፣ የጉራጌ ዞን ብልጽግና ፓርቲ የወጣቶችና የሴቶች ክንፍ ኃላፊዎች፣ የወረዳና የከተማ አስተዳደር የትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች፣ የዞኑ የወላጅ መምህር ህብረትና የመምህራን ማህበር ተወካዮችና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።







