




====ጾታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶችን የመከላከል ስራ የሁሉም ማህበረሰብ ሊሆን እደሚገባ ተገለፀ
በእዣ ወረዳ ሴቶች እና ህፃናት ጽ/ቤት አዘጋጅነት የ20ኛ የብሔር ብሔረሰቦች ቀን ዲሞክራሲያዊ መግባባት ለህብረ-ብሔራዊ አድነት በሚል መሪ-ቃል እና በአለም ለ34ኛ ጊዜ እንዲሁም በሀገራችን ለ20ኛ ጊዜ የሚከበረውን የፀረ-ጾታዊ ጥቃት ቀን ተከበረ።
የሴቶች እና ህፃናት መብት እና ድህንነት ማስከበር ቡድን መሪ አቶ ከበደ ቢረዳ እዳሉት ሴቶችን የሚያሳንስ የሚጨቁን ወይም አካላዊና አዕምሯዊ ደህንነታቸውን የሚጎዳ የትኛውንም አይነት አመለካከት የተከለከለ እደሆነ እና በህገ-መንግሥቱ መሠረት ጎጂ ድርጊት ተብሎ እደሚፈረጅ ገልፀው ተጠቂዎች በሚኖሩበት ጊዜ ወደ ህግ እዲመጡ ከማረግ እና ከማበረታታት አንፃር እያንዳንዱ ተቋም እና ማህበረሰብ ሀላፊነት እዳለበት ገልፀው ።
ቅንጅታዊ አሰራርን አጠናክሮ በመቀጠል የግንዛቤ ስራዎችን በማጠናከር ከእምነት ተቋማት ከሀገር ሽማግሌዎች ከዕድሮች ጋር ጥምረት በማድረግ የሴቶችን ጥቃት የሚያወግዙ መግለጫዎች በማውጣት ከፖሊሲና የህግ ማዕቀፎች ከማስፈፀም አንፃር እና ከማህበራዊ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ጋር በመቀናጀት እየተሰራ እዳለና ለቀጣይም ክፍተቶችን በመሙላት ተጠናክሮ ሊቀጥል እደሚገባ ገልፀዋል።
የስርአተ-ፆታ ቡድን መሪ ወ/ሮ ሩቅያ ኑረዲን በበኩላቸው የሴቶች ጥቃት የሴቶችን የእኩልነት መብት ብቻ ሳይሆን ሌሎች ሰብዓዊ መብቶችን ማለትም በሂወት የመኖር መብትን የማንኛውም ዓይነት ልዩነት/መድሎ ነፃ የመሆን መብት የነፃነት እና የአካል ደህንነት መብት የመማር መብት የመስራት መብት የአካልና የአዕምሮ ጤንነትን መብት እደሚጨምር አብራርተው
ኩነቱን በአዳራሽ ከማክበር ባሻገር ሰረዓተ ፆታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶችን ለመከላከል ተጋላጭነትን ለመቀነስ ጥራት ያለው አገልግሎት እንዲሰጥ ለማረግ ብሎም ለማስወገድ መላው ህብረተሰቡ እዲወያዩ በማድረግ ጥቃትን የሚጠየፍ ማህበረሰብ መፍጠር እንደሚገባ ገልፀዋል።
በመድረኩም ነጭ እሪቫን ወንዶች በሴቶች እና ህፃናት ላይ ማንኛውም አይነት ጥቃት ፈፅሞ ላለመፈፀም እና ጥቃቱ በሌሎች ሲፈፀምም ዝም ላለማለት ቃል የሚገባቡበት የነጭ ሪቫን ምልክት በማድረግ ቃል የገቡ ሲሆን ሁሉም ባለ ድርሻ አካላት በአገኘው አጋጣሚ ሁሉ ለማህበረሰቡ ግንዛቤ መፍጠር እዳለበት እና ተግዳሮቶቹን ለመቅረፍ መሰራት እደሚገባም ተገልፆል
በጉባዔውም በእዣ ወረዳ ሴቶች እና ህፃናት ጽ/ቤት በስ/ፆታ/ማ/ተጠ/ማ/ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ የመነሻ ውይይት እና ግንዛቤ ማስጨበጫ ሰነድ የቀረበ ሲሆን የሴክተር መ/ቤት ኦፊሰሮች ፎካል ፐርሰኖች የህዝብ ክንፎች የጽ/ቤቱ ባለሙያዎች እና ሌሎች የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተገኝተውበታል ሲል የዘገበው የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት ነው







