








የግብርናው ዘርፍ ለሃገራዊ የኢኮኖሚ ዕድገት ያለውን ፋይዳ በመረዳት ያልተነኩ እምቅ አቅማችንን በመጠቀም እና በተለየ መንገድ በመስራት ምርትና ምርታማነታችንን ማሳደግ እንደሚገባ ተገለፀ።
ቀን19/05/2018
በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ “የተቀናጀ የግብርና ልማት ጥረት ለቤተሰብ ስኬት” በሚል መሪ ቃል የ2018 የበልግ የተቀናጀ የግብርና ልማት ስራዎች የንቅናቄ መድረክ ተካሄደ።
የእዣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘውዱ ዱላ እንዳሉት የግብርናው ዘርፍ ለአገራዊ ኢኮኖሚያዊ ዕድገትና ድህነትን በመቀነስ ረገድ ባለው ወሳኝ ምክንያት ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጠው ዘርፍ መሆኑን ገልፀው።
በወረዳችን የምግብና ስነ ምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ የገቢ ምርትን በመተካት የውጪ ምርትን በአይነት በብዛት በማሳደግ ለግብርና ኢንዱስትሪው በቂ ምርት በማምረት እና የስራ እድል ፈጠራን በማስፋፋት የምግብ ሉአላዊነትን በማረጋገጥ እና ድህነትን ማሸነፍ እንደሚገባ አስገንዝበው።
የተገኙ ውጤቶች ሳያዘናጉን ያልተሰሩ ስራዎች ላይ በማተኮር እንዲሁም ከመሬት አያያዝ አኳያ ያልተነኩ እምቅ አቅሞች መኖሯቸውንና እነዚህ እምቅ አቅሞችን በተለይ የመንገድ ተጠቅመን ሀገራችንን ማበልፀግና እንደሚገባ አሳስበው።
ይህህንንም ተግባር በማጠናከር የአርሶ-አደሮችን ገቢ ማሳደግ የተጠናከረ ጥልቅ ድጋፍ እና ክትትል በማድረግ እንዲሁም ማነቆችን በመለየትና በመፍታት የአርሶአደሩ ምርታማነት ማሳደግ እንደሚገባና ሁሉም ባለድርሻ አካላት ለዚህ ስራ የድርሻውን እንዲወጣ መልዕክት አስተላልፈዋል።
የእዣ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ መቻል ተሰማ በበኩላቸው በወረዳችን በሁሉም ቀበሌዎች ማበረሰባችን ከጠባቂነትና ጥገኝነት እንዲላቀቅ በርካታ የውይይት መድረኮች በመፍጠር ህዝቡን የማንቃት ስራዎች መሰራቱን አስታውሰው።
የተለያዩ ሀገር አቀፍ በክልል የታወጁ በወረዳ ደረጃ ልዩ ትኩረት ሊደረግባቸው የሚገቡ ኢኒሼቲቮችን ተግባራዊ በማድረግ ላይ የተሰራ መሆኑን እና ከነዚህ የተገኙ ውጤቶች መካከል የሰብል ልማት ዘርፍ የተፈጥሮ ሃብት ልማትና ጥበቃ እንዲሁም በእንስሳት ምርትና ምርታማነት ማሳደግ መቻሉን ገልጸው ።
በበልግ የተቀናጀ ግብርና ልማት ዋና ዋና ግቦችን ያስቀመጡ ሲሆን የተፋሰስ ልማትን 9850 ሄክታር ማልማት የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ 9.5 ሚሊዮን የአግሮ ፎረስትሪ ችግኝ ማዘጋጀት የበልግ ሰብል ምርት 8,750.5 በማልማት 2,325,252 ኩ/ል ምርት የቡናና ቅመማ ቅመም ማሳ ሽፋን ማሳደግ።
የሌማት ትሩፋት 259 መንደሮችን በመመስረት 271.7 ቶን ማምረት እንዲሁም 31 ሚሊዮን ብር ለ300 አርሶ-አደሮች የብድር ተጠቃሚ ማድረግ እና ሌሎች ተያያዣ አጀንዳዎችን ያቀረቡ ሲሆን።
ግብርናን ለመለወጥ በተለያዩ ዋና ዋና ማነቆችና አጀንዳዎች ላይ ጥልቀት ያለው ውይይትና ምክክር በማድረግ የመፍትሄ አቅጣጫ በማስቀመጥ መድረኩ ተጠናቋል ሲል የዘገበው የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ነው።








