የእዣ ወረዳ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት

የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን አገልግሎት

===የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን አገልግሎት ማህበረሰቡ ለህክምና የሚያወጣውን ከፍተኛ ወጪ በማስቀረት የዜጎችን የኑሮ ጫና የቀነሰ በመሆኑን በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተገለፀ።

ጥር 19/2018 ዓም

በጉራጌ ዞን የእዣ ወረዳ ጤና ጥበቃ ፅ/ቤት በወረዳ ማዐጤመ አፈፃፀም ከባለድርሻ አካላት ጋር ገምግሟል።

የእዣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘውዱ ዱላ እንዳሉት የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን አገልግሎት ማህበረሰቡ ለህክምና የሚያወጣውን ከፍተኛ ወጪ በማስቀረት የዜጎችን የኑሮ ጫና የቀነሰ በመሆኑን በትኩረት መስራት ይገባል ።

በዘንድሮ አመት ከማጤመ ጋር ተያይዞ ስራዎች ቢሰሩም አሁንም ጉለት እንዳለ የጠቆሙት አቶ ዘውዱ ማጤመን ከፋይዳ መታወቂያ ጋር አስተሳስሮ በመስራት የማጤመ ተጠቃሚ አባላቶች የፋይዳ መታወቂያ ተጠቃሚ መሆን ይጠበቅባቸዋልም ብለዋል።

በቀጣይም እንደ ወረዳው በቀበሌዎች ተለዩ ጉለት ቶሎ በማረም በአፋጣኝ ማህበረሰቡ በትኩረት መስራት እንዳለበትም አቶ ዘውዱ አስገንዝበዋል።

የእዣ ወረዳ ጤና ጥበቃ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ መሀመድ ሰኢድ በበኩላቸው ፍትሀዊና ቀልጣፋ የጤና አገልግሎት ለመስጠት ሁሉም ማህበረሰብ የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን ተጠቃሚ እንዲሆን በትኩረት መሰራት የሚጠይቅ ነውም ብለዋል።

እንደ ወረዳው የማዐጤመ አፈጻጸምና የጤና አገልግሎት አሰጣጥ የተለያዩ ስራዎች መሰራታቸውን የጠቆሙት ሀላፊው ይሁን እንጂ በዘርፉ የሚፈለገው ውጤት እንዲመዘገብ በቁርጠኝነት ፡ በቅንጅትና በሀላፊነት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።

በቀጣይም በዘርፉን ውጤታማ ለማድረግ አባላት በማፍራት ፡ ያልተመለሱ ገንዘቦች እንዲመለሱ በማድረግ ከዚህ በፊት የነበሩ ጉድለቶች በማረምና ጥንካሬዎችን በማስቀጠል ጤናው የተጠበቀ አምራች ዜጋ መፍጠር ይገባል ብለዋል።

ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየትም ማህበረሰቡ የማጤመ ተጠቃሚ በመደረጉ ጤናውን በአግባቡ እንዲጠብቅ ያስቻለው በመሆኑ በዘርፉ ያሉትን ጉለቶች በማረም ህብረተሰቡ ተጠቃሚ እንዲሆን በተጠያቂነት መንፈስ መስራት ይገባልም ብለዋል።