







በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ የመንግስት ፡ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችና ማህበራት ቅንጅትና ትብብር ለማጠናከር እንዲሁም የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ም/ቤት ለማቋቋም የውይይት መድረክ ተካሂዷል።
ጥር 20/2018 ዓም
በመድረኩ የተገኙት የእዣ ወረዳ ረዳት የመንግስት ተጠሪ አቶ አብድራህማን ሀሰን እንዳሉት የሲቭል ማህበረሰብ ድርጅቶችና ማህበራት የማህበረሰቡ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ ሚናቸው የጎላ በመሆኑ ትብብርና ቅንጅታቸው ማጠናከር ይገባል።
ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማምጣት የሲቭል ማህበራትና ድርጅቶች ወሳኝ አላቸው ያሉት አቶ አብድራህማን በመሆኑም በቀጣይ ሀገራዊ ተልእኮዎች በብቃት ለመፈጸም እገዛቸው አጠናክረው እንዲቀጥሉ አሳስበው በሰላም፣በልማትና በዲሞክራሲ ግንባታ ይበልጥ እንዲሰሩ ገልፀዋል ።
የእዣ ወረዳ ፋይናንስ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ተካ ወርቁ በበኩላቸው ይህ ምክር ቤት መቋቋም የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችና ማህበራት የሚገጥማቸው ችግሮች በመቅረፍ በቀጣይ የተሻለ ስራ ለመስራት የጎላ በመሆኑን እነዚህ ማህበራትና ድርጅቶች በተቋቋመው ምክር ቤት የመንግስት ጣልቃ ገብነት ሳይደረግባቸው በራሳቸው ቅንጅት ፡ትብብርና አቅም እንደሚንቀሳቀሱ ባቀረቡት ሰነድ አመላክተዋል ።
በቀጣይ እነዚህ ማህበራትና ድርጅቶች በገቡት ውል መሰረት ኃላፊነት፣ተጠያቂነትና ግልጸኝነት በመፍጠር እየሰሩት ያለ ስራ በሚመለከተው አካል እያስገመገሙ እንዲሄዱ አቶ ተካ አስገንዘበዋል።
የእዣ ወረዳ ፍትህ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ አሸናፊ እንዳለ በበኩላቸው የሲቪል ማህበራቶችና ድርጅቶች በራሳቸው በጎ ፍቃድ አምነው የገቡበት ተግባር ከምንም ነገር ነጻ ገለልተኛ በመሆን ስራቸው በአግባቡ መስራት ይኖርባቸዋል ብለዋል ።
ፍቃድ ከወስዱ በኋላ በተፈቀደላቸው ሙያ መስራት ፡እቅድና ሪፖርታቸው ማስገምገም ፡ውላቸው ማደስና ወጥ የሆነ አሰራር ተከትለው እንዲሰሩም የጠቆሙት አቶ አሸናፊ የሚገጥማቸው ችግሮችም ሆነ ቅሬታዎች ሲኖሩ ከመንግስት ተቋማት ጋር ተግባቦት ፈጥሮ ጥራት ባለው ሁኔታ ስራዎችን መስራት ይገባል ብለዋል።
በውይይቱ የተገኙት አካላት በበኩላቸው የጋራ ምክር ቤቱ መቋቋሙ ለማህበረሰቡ ተጠቃሚነት በጋራ መስራት ፡የእርስ በርስ ግንኙነት መፍጠር ላይ ድርሻው የጎላ በመሆኑ የሚበረታታ ነው ብለዋል ።
በመጨረሻም ለተቋቋመው ምክር ቤት 7 የስራ አስፈጻሚ አካላት በመምረጥ መድረኩ ተጠናቋል።








