






የብልጽግና ፓርቲ በ2018 ጠቅላላ ምርጫ እዣ ቁ 1 የምርጫ ክልል እጩ ተወዳዳሪዎች ይፋ አደረገ
መጋቢት 1/2018 ዓ.ም (አገና)
የብልጽግና ፓርቲ በ2018 ዓ.ም በሚካሄደው ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በእዣ ቁ 1 ምርጫ ክልል ፓርቲውን ወክለው ለፓርላማ እና ክልል ምክር ቤት የሚወዳደሩ እጩዎቹን በይፋ አስተዋውቋል።
ፓርቲው እጩዎቹን የመረጠው በህዝብ ዘንድ ያላቸውን ተቀባይነት፣ የትምህርት ዝግጅት፣ የስራ ልምድ እና የፓርቲውን ራዕይ ለማስፈጸም ያላቸውን ቁርጠኝነት መሰረት በማድረግ መሆኑን ገልጿል።
“ኢትዮጵያ ወደ ተምሳሌት ሀገር” የሚል መሪ ቃል እና “የስንዴ ነዶን” የመወዳደሪያ ምልክት አድርጎ ወደምርጫ መግባቱን የገለፀው ፓርቲው የሀገር ጥቅምን ባስቀደመ መልኩ የሰላምና አንድነት፣ የልማት ፣ የሁለቱ ውሃዎች ፣ የዲሞክራሲ ግንባታ ጉዳዮች የምርጫ ቅስቀሳ የትኩረት ነጥቦች እንደሚሆኑም ተመልክቷል።
በዕጩዎች ይፋ መደረግ መርሃ-ግብር ላይ እንደተገለጸው፣ ፓርቲው በምርጫው አሸናፊ ሆኖ ለመውጣት የሚያስችለውን የምርጫ ማኒፌስቶ እና ስትራቴጂ ቀርጾ ወደ ስራ መግባቱን አመልክቷል።
በመድረኩ የጉራጌ ዞን ባህል ቱሪዝም መምሪያ ሃላፊ ወ/ሮ መሰረት አመርጋን ጨምሮ የእዣ ወረዳ እና የአገና ከተማ አስተዳደር አስተባባሪና ጠቅላላ አመራሮች ተሳታፊ ሆነዋል ሲል የዘገበው የእዣ ወረዳ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው።






