የእዣ ወረዳ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት

የስነ-ምግባር ችግር ምክንያት በሚፈጠሩ አለመግባባቶች ከአገልግሎት አሰጣጥ ችግር አልፎ ለአደጋ መንስኤ መሆን እንደሌለባቸው ተገለፀ ።

የስነ-ምግባር ችግር ምክንያት በሚፈጠሩ አለመግባባቶች ከአገልግሎት አሰጣጥ ችግር አልፎ ለአደጋ መንስኤ መሆን እንደሌለባቸው ተገለፀ ።

ሰኔ 23/2018 ዓ.ም (አገና)

በእዣ ወረዳ እና አገና ከተማ መስተዳድር ለሚገኙ ባለ ሁለት ባለ ሶስት እና ባለ አራት እግር አሽከርካሪዎች የሙያ ብቃት እና የስነ ባህሪ ተሃድሶ ስልጠና ተሰጥቷል።

መድረኩ የመሩት የጉራጌ ዞን ትራንስፖርት እና መንገድ ልማት መምሪያ ምክትል ሀላፊ አቶ ግሩም ወ/ሰንበት የትራፊክ አደጋ በሰውና በንብረት ላይ እያስከተለው ያለው ህይወት መቅጠፍና ከፍተኛ የንብረት ውድመት ለመቀነስ አሽከርካሪዎች ያላቸው ከፍተኛ ሀላፊነት ተገንዝበው ዘወትር በጥንቃቄ ማሽከርከር እንደሚገባቸው ጥሪ አቅርበዋል።

አክለውም መንገድ ትራፊክ አደጋ እንደ ሀገር እያስከተለው ያለው የሰው ልጅ ህይወት መቅጠፍ ፡ ከፍተኛ የንብረት መውደምና አልፎም ተርፎም ቤተሰብ እስከመበተን ያለው ቀውስ ለመቀነስ ስነ-ምግባር ተላብሶና ህግን ጠንቅቆ በማወቅ ማሽከርከር እንደሚገባም ለሰልጣኞቹ አስገንዝበዋል።

የእዣ ወረዳ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ገዛኸኝ መልስ በበኩላቸው የትራንስፖርት አገልግልግሎት በአጠቃላይ የሀገራችን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴ እድገት ላይ ከፍተኛ ድርሻ እንደሚይዝ ገለፀው አሽከርካሪዎች የሚሸከሙት የሰው ነብሰ እንደመሆኑ መጠን እያንዳንዱ እንቅሰቃሴዎች በስነምግባር እና በጥንቃቄ የተሞላ መሆን እንዳለበት አሳስበዋል ።

ሃላፊው አክለውም የትራፊክ አደጋ በሰውና በንብረት ላይ እያስከተለው ያለው ህይወት ማሳጣትና ከፍተኛ የንብረት ውድመት ለመቀነስ አሽከርካሪዎች አሁን የተሰጣቸው ስልጠና በተግባር በማዋል በጥንቃቄ ማሽከርከር እንደሚገባቸው መልዕክት አስተላልፈዋል ።

የአገና ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ሞገስ ንማኒ በኩላቸው የመንገድ ትራፊክ አደጋ መንስኤ ከከተማው ብሎም ከወረዳው የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ አሽከርካሪዎች ስነ-ባህርይና ስነ-ምግባር አኳያ ስንመለከት አንዳንድ ጠንቃቃ እና ትሁት አሽከርካሪዎች እንዳሉ ሁሉ በተለይ በአንዳንድ የባለ 3እግር ባጃጅና አነስተኛ ተሽከርካሪ አሽከርካሪዎች የስነ-ምግባር ችግር ምክንያት በሚፈጠሩ አለመግባባቶች ከአገልግሎት አሰጣጥ ችግር አልፎ ለአደጋ መንስኤ ሲሆኑ ይታያልም ብለዋል ።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ የመንገድ ትራፊክ ደህንነት ዳይሮክትሬት የትምህርት ስልጠና ግንዛቤ ማስጨበጫ ኤክስፐርት አቶ ክፍሌ አሼቦ የስልጠናው ሰነድ ባቀረቡበት ወቅት በአሽከርካሪዎች ከሚስተዋሉ የጥንቃቄ ችግሮችና ለመንገድ ትራፊክ አደጋ መንስኤ ከሆኑት መካከል ለአብነት ያለብቃት ማሽከርከር ፡ የተሽከርካሪ ደህንነት ሳያረጋግጡ ማሽከርከር ፡ ከተፈቀደ የፍጥነት ወሰን ማለፍ ፡ የመንገድ ትራፊክ ህጎች አለማክበር በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው ብለዋል ።

በስልጠናው ተሳታፊ አሽከርካሪዎችም ስልጠናው እጅግ አስፈላጊና ወቅታዊ በመሆኑ በሚያሽከረክሩበት ወቅትም የበለጠ እንዲጠነቀቁ የሚያደርግ እንደሆነም በአስተያየታቸው ተናግረዋል በመጨረሻም የስልጠናው ተሳታፊዎች ለተቸገሩ ወገኖቻች የሚውል የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ስልጠናው ተጠናቋል ሲል የዘገበው የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ነው ።