



ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ መግባባትና ለአንድነታችን!” — አቶ ሙከረም በደዊ
ቀን 02/2019 ዓ.ም
19ኛው ብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ ቀን በእዣ ወረዳ በተለያዩ ዝግጅቶችና በቃል መሐላ ስነ-ስርዓት በድምቀት ተከበረ።
በዕለቱ የእዣ ወረዳ ዋና አፈ ጉባኤ አቶ ሙከረም በደዊ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ሰንደቅ ዓላማችን የነጻነታችን፣ የአርበኝነታችን፣ የሉዓላዊነታችንና የማንነታችን ግርማ በመሆኑ ለአንድነታችንና ለብሔራዊ መግባባታችን መጠናከር የጎላ ድርሻ እንዳለው ገልጸዋል።
በስነ-ስርዓቱ ከተላለፉት ዋና ዋና መልዕክቶችና ከተገባው ቃል መሐላ :- የአንድነትና የነጻነት ምልክት፦ ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ መግባባት፣ ለአንድነታችን፣ ለነጻነታችንና ለሉዓላዊነታችን ዘላቂ መቆሚያ ነው።
ልማትና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት፦ ድህነትንና ኋላ ቀርነትን አስወግደን፣ ሀገራችንን በልማትና በዴሞክራሲ ጎዳና የሕዝቦችን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የጀመርነውን የለውጥ ጉዞ አጠናክረን እንቀጥላለን።
የጋራ ትግልና ቁርጠኝነት፦ ያጋጠሙ ችግሮችን በአንድነትና በጋራ ስሜት በማስወገድ፣ በዓመቱ የታቀዱ የልማትና የመልካም አስተዳደር ዕቅዶችን ለማሳካት በሰንደቅ ዓላማችን ፊት ቃል እንገባለን።
See less







