
















===============================================
ህዳር 27/2016 ዓም
በወረዳው እየተከናወኑ የሚገኙ አበረታች የሆኑ የልማትና መልካም አስተዳደር ተግባራቶች በማጠናከርና ጉለቶችን ቶሎ እንዲታረሙ በማድረግ ህብረተሰቡ ይበልጥ ተጠቃሚ ማድረግ እንደሚገባ ተገለፀ።
በጉራጌ ዞን የእዣ ወረዳ ምክር ቤት የ2016 ዓም 4ኛ ዙር 11ኛ ዓመት 40ኛ መደበኛ ጉባኤው አካሂዷል።
በጉባኤውም ወቅት የእዣ ወረዳ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ ሙከረም በደዊ እንደገለፁት በህዝቡ የሚነሱ ጥያቄዎች መንግስትና መሪው ፓርቲ ያስቀመጣቸው የአፈፃፀም አቅጣጫዎች በመከተል በተቀናጀ መልኩ ምላሽ እንዲያደርጉ በትኩረት መስራት ይገባል።
በወረዳው በህዝቡ የሚነሱ የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ተገቢውን ትኩረት ለመስጠት የሁሉም ባለድርሻ አካላት ሚና ወሳኝ በመሆኑ የምክርቤቱ አባላት ግንባር ቀደም አስፈፃሚ በመሆን ማከናወን ይገባቸዋል ብለዋል ።
በወረዳው እየተከናወኑ የሚገኙ አበረታች የሆኑ የልማትና መልካም አስተዳደር ተግባራቶች በማጠናከርና ጉለቶችን ቶሎ እንዲታረሙ በማድረግ ህብረተሰቡ ይበልጥ ተጠቃሚ ማድረግ ይገባል ያሉት አቶ ሙከረም ከዚህ በተጨማሪ ከሁሉም በላይ ሰላም መሆኑን ተረድተን የህዝባችን ሰላም እንዲረጋገጥ ሁላችንም የድርሻችንን በመወጣት ሁለተናዊ ብልፅግና ልናረጋግጥ ይገባልም ብለዋል ።
የእዣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘውዱ ዱላ እንደገለፁት በ2016 በጀት ዓመት የኛ ሩብ ዓመት የተከናወኑ ተግባራቶች ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን በሪፖርታቸውም በግብርናው ዘርፍ በ2015/16 ዓም መኸር እርሻ በዋናዋና ሰብሎች 5995 ሄክታር ለማልማት ታቅዶ 5988.5 ሄክታር የታረሰ ሲሆን ለዚህም NPSB ከ4145 ኩንታል ዩሪያ 1521 ኩንታል በላይ ጥቅም ላይ መዋሉን አመላክተዋል ።
ሌላው በዚሁ ዘርፍ 106050 የተለያዩ የፍራፍሬ ችግኞች በኩታገጠም ለማስተከል ታቅዶ 120980 ጉድጓድ ተዘጋጅቶ ተከላ ከእቅድ በላይ ተከናውውኗል ያሉት ዋና አስተዳዳሪው በ2016 ዓም መስኖ ልማትም 138 ሄክታር መሬት በማቀድ በእስካሁን ሂደት 26 ሄክታር መከናወኑንም ገልፀዋል ።
በበጀት ዓመቱ በጤናው ዘርፍ በ1ኛው ሩብ ዓመት ለ4346 እናቶች በጤና ተቋማት በሰለጠነ የጤና ባለሙያ የወሊድ አገልግሎት ለመስጠት ታቅዶ 1038 ለሆኑ አገልግሎት መሰጠቱን በሪፖርቱ ያመላከቱት አቶ ዘውዱ ክትባት ለሚያስፈልጋቸው ህፃናት የተለያዩ የክትባት አይነቶች ላይ አገልግሎት ተሰጥቷልም ብለዋል።
በትምህርት ዘርፍም በአጠቃላይ ከ1-12ኛ ክፍል 14792 ተማሪዎች በበጀት ዓመቱ ትምህርታቸው እየተከታተሉ ናቸው ያሉት ዋና አስተዳዳሪው የተማሪዎች ውጤትና ስነ ምግባር ለማሻሻል ከጋበር ድርጅት ጋር በመቀናጀት ከሌላ ጊዜ በተለየ መልኩ ሰፊ ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል ።
በስራ እድል ፈጠራ ዘርፍም በገጠርና ከተማ በበጀት ዓመቱ 2553 ታቅዶ 517 በእስካሁን ሂደት በተለያየ ዘርፎች የተፈጠረላቸው ሲሆን 1558000 ብር ለወጣቶች ብድር ተሰራጭቷል።
በአፈፃፀም ወቅት የታዩ ጉለቶች በሞክር ቤት አባላት ጥያቄና አስተያየት የተነሳ ሲሆን በሚመለከታቸው አካላት ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል።
ሌላው በምክር ቤቱ በዋናነት ከተያዙ አጀንዳዎች አንዱ የሆነው ለቀበሌ ምሊሻ አልባሳት በማህበረሰብ ተሳትፎ እንዲሆን የተዘጋጀ ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎአል ።
በመጨረሻም ምክር ቤቱ 60 በ40 እቅድ በአግባቡ የፈፀሙ ግንባር ቀደም 9 ተቋማት የእውቅና ሰርተፊኬት ሰጥቷል ሲል የዘገበው የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው ።







