




በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ በየቅመነ ሙሉ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት የተማሪዎች ምገባ ማስጀመሪያ ፕሮግራም ተካሄደ።
ህዳር 9/2019 ዓም
በወረዳው በ11 ትምህርት ቤቶች የምገባ ፕሮግራም የተጀመረ ሲሆን በቀጣይም በ31 ትምህርት ቤቶች ቅድመ አንደኛ ደረጃ ተማሪዎች ላይ እንደሚቀጥልም ተጠቁሟል ።
የእዣ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪና የትምህርት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ተጠምቀ በርጋ በመርሃ ግብሩ ተገኝተው እንደገለፁት ይህ የተማሪ ምገባ የትምህርት ሰዓት ብክነትን በመቀነስ ፣ ከመጠነ መቅረትና ማቋረጥ እንዲሁም በትምህርት አቀባበል ላይ አዎንታዊ ተፅኖ ስላለው በሁሉም ትምህርት ቤቶች ማጠናከር ፋይዳው የጎላ ነው ።
በዛሬው እለትም በወረዳው በየቅመነ ሙሉ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት የተማሪዎች ምገባ ማስጀመሪያ ፕሮግራም መካሄዱን የጠቆሙት ሀላፊው በወረዳው በ11 ትምህርት ቤቶች የምገባ ፕሮግራም የተጀመረ ሲሆን በቀጣይም በ31 ትምህርት ቤቶች ቅድመ አንደኛ ደረጃ ተማሪዎች ላይ እንደሚቀጥልም ተጠቁሟል ።
በቀጣይም በሁሉም ትምህርት ቤቶች ተግባራዊ ለማድረግና በተጀመሩባቸውም አጠናክሮ ለማስቀጠል መላው ማህበረሰቡና ተወላጆ የድርሻውን መወጣት አለበት ያሉት አቶ ተጠምቀ ትምህርት ቤቶች የውስጥ አቅም በማሳደግ ዘላቂነት ባለው መልኩ ተጠናክሮ እንዲቀጥል መረባረብ ይገባልም ብለዋል።
የየቅመነ ትምህርት ቤቶ ርዕሰ መምህ የሆኑት አቶ ይድነቃቸው በበኩላቸው የነገ ሀገር ተረካቢ ዜጎችን ለማፍራት ትምህር ትኩረት የሚሰጠው ጉዳይ ሲሆን የተማሪ ምግባ ፕሮግራም ደግሞ ጥራት ያለው ትምህርትና የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ያግዛል ብለዋል።
ከማህበረሰቡ ድጋፍ በተጨማሪ የወረዳው ትምህርት ፅ/ቤትም ለትምህርት ቤቱ በተለያየ መልኩ የሚያደርገውም ድጋፍ ምስጋናቸውን ያቀረቡት አቶ ይድነቃቸው ይህም የምገባ ፕሮግራም ቀጣይነት እንዲኖረውና የተጠናከረ ለማድረግ በተለይም የአካባቢው ማህበረሰብ በአቅሙ ልክ ለዚህ ምገባ የሚረዱ አስቤዛዎች ገዝቶ በማቅረብ ወይንም የቻለውን ገንዘብ በመደገፍ የድርሻውን መወጣት እንዳለበትም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
በምግባ ማስጀመሪያ መርሃ ግብሩም የትምህርት ፅ/ቤት ምክትል ሀላፊ አቶ አስቻለው ወልዴ ጨምሮ የትምህርት ቤቱ መምህራን ተገኝተዋል።
See less











































