የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የተለያዩ ሹመቶችን በዛሬው ዕለት ሰጥቷል። በዚህም መሠረት:-

=========የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የተለያዩ ሹመቶችን በዛሬው ዕለት ሰጥቷል። በዚህም መሠረት:-

1ኛ) ኢንጂነር አተረፈ ታምራት… የኮንስትራክሽን ባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር

2ኛ) ኢንጂነር ሲቲ ሙስጠፋ .. . ም/ዋና ዳይሬክተርና የመንግስት ኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች ግንባታ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር

3ኛ) ኢንጂነር ምህረተአብ ሳሙኤል .. . ም/ዋና ዳይሬክተርና የመንግስት ኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች ዲዛይንና ኮንትራት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር

4ኛ) ወ/ሮ ትብለጥ ኢስጢፋኖስ .. . ም/ዋና ዳይሬክተርና የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ልማትና ሬጉላቶሪ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሆነው ተሹመዋል።

ለሁሉም ተሿሚዎች አመራሮቻችን መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንላችሁ እንመኛለን።

See less

#ትልቅሀገር#ትልቅሕዝብ#ታላቅርዕይ

=====የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መልዕክት

ሠንደቅ ዓላማችን የመደመር ዕሴታችን፣ የአንድነታችንና የኢትዮጵያ ከፍታ ምልክታችን ነው!

ዛሬ 19ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀንን አክብረናል!

ሠንደቅ ዓላማ የቀደምት አባቶቻችንን የመሥዋዕትነት ታሪክ የሚያስታውሰን፣ የዛሬ ትጋታችንን የሚያንፀባርቅና የነገውን የብልፅግና ራዕያችንን የሚያመላክት የሀገራችን የከፍታ ዓርማ ነው።

የመደመር መንግሥት ዋነኛ ትኩረት ኢትዮጵያን በአንድነት፣ በሰላም፣ በልማትና በሁለንተናዊ ብልጽግና ወደ ላቀ ከፍታ ማሸጋገር ነው።

ሠንደቅ ዓላማችን የኅብረ ብሔራዊ አንድነታችን መገለጫ እንጂ የልዩነታችን ምንጭ መሆን የለበትም። በብሔር፣ በቋንቋ፣ በባህልና በእምነት የተለያየን ብንሆንም፣ በኢትዮጵያዊነታችንና በጋራ የልማት ራዕያችን አንድ ነን።

የመደመር ዕሳቤም ልዩነቶቻችንን እንደ ሀብት በመቁጠር፣ የጋራ ዕሴቶቻችንን በማጠናከርና በትብብር የሀገራችንን ታላቅነት በተግባር ለማረጋገጥ ያነሳሳናል።

በዚህ ታላቅ ብሔራዊ ቀን፣ ሠንደቅ ዓላማችንን ከፍ አድርገን እያውለበለብን ለአንድነታችን፣ ለሰላማችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለሀገራችን ብልጽግና ያለንን ቁርጠኝነት በተግባር እናረጋግጥ።

እንኳን 19ኛው ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን በሰላም አደረሰን!

#ትልቅሀገር#ትልቅሕዝብ#ታላቅርዕይ

See less

የጉራጊኛ ቋንቋ በዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘመን — አዲስ የምስራች

ወሄም ሳረናሁም፣ሳረንደም

የጉራጊኛ ቋንቋ በዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘመን — አዲስ የምስራች!

**^^

Ministry of Innovation and Technology በ STRIDE Ethiopia 2 Summit 2026 ላይ አዘጋጅቶ ይፋ ባደረገው አዲስ Digital Literacy Content Platform ላይ የዲጂታል እውቀት ማበልጸጊያ ይዘቶቹ (Contents) ከተዘጋጁባቸው 10 ቋንቋዎች ጉራጊኛ አንዱ ሆኗል!

ይህ ስኬት ጉራጊኛን የትምህርት፣ የሥራ እና የቴክኖሎጂ ቋንቋ ለማድረግ ሲደረግ የነበረው ጥረት ፍሬ ማፍራቱን ያሳያል።

በጉራጊኛ የተዘጋጁትን ይዘቶች በሚከተለው ሊንክ በመግባት ይጎብኙ፡ 🔗https://www.dlc.gov.et/public/index.php/search?categoryId=0&langId=8&search=

ይዘቶቹን ተመልክተው ያለዎትን አስተያየት እና ግብረ-መልስ ኮመንት ላይ ያጋሩን!

#DigitalLiteracy#Guragigna#WolkiteUniversity#TechnologyInLocalLanguages#DigitalEthiopia See less

See less

የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መብራቴ ወልደማሪያ ከዞኑ አስተባባሪ አካላት ጋር በቀጣይ በሚሰሩ ተግባራት ዙሪያ ውይይት አካሄዱ።

======የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መብራቴ ወልደማሪያ ከዞኑ አስተባባሪ አካላት ጋር በቀጣይ በሚሰሩ ተግባራት ዙሪያ ውይይት አካሄዱ።

ጥቅምት 01/2019(ወልቂጤ)

የጉራጌ ዞን አስተባባሪ አባላት በቀጣይ በዞኑ በሚፈፀሙ የፖለቲካ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ላይ ውይይት አካሂዷል ።

በዞኑ ሰላምን የማፅናትና የህዝቡን የልማት ተጠቃሚነት የማረጋገጥ ጉዳይ ልዩ ትኩረት እንደሚሰጠው ተመላክቷል።

ባለፉት አመታት የተጀመሩ ህዝቡን ያሳተፉ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉና በ7ተኛው ጠቅላላ ምርጫ በህዝባዊ ውይይት መድረኮች ሲነሱ የነበሩ ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ ታቅዶ ይሰራል ተብሏል።

የብልፅግና ፓርቲ በህዝብ ውስጥ ያሉትን ፀጋዎች ለይቶ በማውጣት፣በማቀድና ህዝብን ባሳተፈ መልኩ በመስራት ብልፅግናን ለማረጋገጥ እንደሚሰራና ይህንኑ በዞኑ እውን ለማድረግ በትኩረት ይሰራል ተብሏል።

በክልልና በሀገር አቀፍ ደረጃ ዞኑ የሚታወቅባቸው ውጤታማ ስራዎች ተጠናክረው የሚቀጥሉ እንደሆነና ያልተጠናቀቁ ፕሮጀክቶችም በማጠናቀቅ ለአገልግሎት እንዲውሉ ይደረጋል ተብሏል።

በቀይ በታቀዱ ተግባራት የዞኑ ህዝብና ተወላጆች እንደዚሁም አጋር አካላት ከዞኑ አመራር ጎን በመቆም ሊያግዙ እንደሚገባም ተጠይቋል።

See less

ምክር ቤቱ አቶ ክብሩ ፈቀደ የዞኑ ዋና የመንግስት ተጠሪ አድርጎ ሰየመ።

=====ምክር ቤቱ አቶ ክብሩ ፈቀደ የዞኑ ዋና የመንግስት ተጠሪ አድርጎ ሰየመ።

ጥቅም 1/2019 (ወልቂጤ)

የጉራጌ ዞን ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ተኛ ዙር 14ተኛ ዓመት 12ተኛ አስቸኳይ ጉባኤ በወልቂጤ ከተማ እያካሄደ ነው።

ምክር ቤቱ በአስቸኳይ ጉባኤው አቶ ክብሩ ፈቀደ የጉራጌ ዞን ዋና የመንግስት ተጠሪ ሆነው እንዲያገለግሉ ሰይሟል።

See less

ምክር ቤቱ አቶ መብራቴ ወልደማሪያም ብዛ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አድርጎ ሰየመ።

=====ምክር ቤቱ አቶ መብራቴ ወልደማሪያም ብዛ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አድርጎ ሰየመ።

ጥቅም 1/2019 (ወልቂጤ)

የጉራጌ ዞን ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ተኛ ዙር 14ተኛ ዓመት 12ተኛ አስቸኳይ ጉባኤ በወልቂጤ ከተማ እያካሄደ ነው።

ምክር ቤቱ በአስቸኳይ ጉባኤው አቶ መብራቴ ወልደማሪያም ብዛ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሆነው እንዲያገለግሉ ሰይሟል።

See less

የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 1ኛ መደበኛ ስብሰባው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የቀረቡ የካቢኔ አባላትን ተቀብሎ አጸደቀ

======የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 1ኛ መደበኛ ስብሰባው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የቀረቡ የካቢኔ አባላትን ተቀብሎ አጸደቀ

መስከረም 28/2019 ዓ.ም (ወልቂጤ) 7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 1ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ስብሰባው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የቀረቡ የካቢኔ አባላትን በሙሉ ድምጽ አፅድቋል፡፡

በዚህም መሰረት፡-

1. አቶ ተመስገን ጥሩነህ – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር

2. ጌዲዮን ጢሞቲዎስ(ዶ/ር) – የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር

3. አቶ አዲሱ አረጋ – የግብርና ሚኒስትር

4. ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) – የገንዘብ ሚኒስትር

5. አቶ መሀመድ እድሪስ – የሀገር መከላከያ ሚኒስትር

6. ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ – የትምህርት ሚኒስትር

7. ወ/ሮ ሀና አርያስላሴ – የፍትህ ሚኒስትር

8. ወ/ሮ ያስሚን ወሀብረቢ – የንግድና ቀጠናዊ ስትስር ሚኒስትር

9. ፍስሃ ይታገሱ (ዶ/ር) – የኢንዱስትሪ ሚኒስትር

10. ዶክተር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ – የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር

11. ዶ/ር መቅደስ ዳባ – የጤና ሚኒስትር

12. አቶ አወሉ አብዲ – የስራና ክህሎት ሚኒስትር

13. ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ – የገቢዎች ሚኒስትር

14. አቶ በረከት ፍስሃፅዮን – የብሔራዊ ስትራቴጂ ሚኒስትር

15. ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ – የባሕልና ቱሪዝም ሚኒስትር

16. ወ/ሮ አለምፀሃይ ጳውሎስ – የማዕድን ሚኒስትር

17. አቶ ሳዳት ነሻ – የሎጅስቲክስ ሚኒስትር

18. ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ – የሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር

19. አቶ ሙሳ አደም – የሰላም ሚኒስትር

20. ፍሬሕይወት ታምሩ – የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር

21. ኢ/ር መሀመድ አብዱርሃማን – የከተማ እና መሰረተ ልማት ሚኒስትር

22. ዶ/ር ኢ/ር ሱልጣን ወሊ – የመስኖ እና ቆላማ ሚኒስትር

23. ዶ/ር አክሊሊ ታደሰ – የወጣቶች እና ስፖርት ሚኒስትር

የካቢኔ አባላት የተሰጣቸውን ኃላፊነት በአግባቡ በመወጣት ኢትዮጵያን ወደተፈለገው የብልፅግና ደረጃ ለማድረስ በጊዜ የለኝም መንፈስ መሥራት እንደሚጠበቅባቸው ተነስቷል፡፡

የካቢኔ አባላት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፊት ቀርበው ቃለ መሃላ ፈፅመዋል።

See less

“ጤና ለሰው ልጅ መሠረታዊ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን ከምርታማነት፣ ከትምህርትና ከማህበረሰቡ አጠቃላይ ዕድገት ጋር የተቆራኘ ነው” አቶ ዘውዱ ዱላ የእዣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ!!

“ጤና ለሰው ልጅ መሠረታዊ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን ከምርታማነት፣ ከትምህርትና ከማህበረሰቡ አጠቃላይ ዕድገት ጋር የተቆራኘ ነው” አቶ ዘውዱ ዱላ የእዣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ!!

መስከረም 26/2019 ዓም

የእዣ ወረዳ ጤና ጥበቃ ፅ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት የጤና ጉባኤ አካሂዷል።

“ሁሉን አቀፍ የጤና አገልግሎት ለማህበረሰብ ተጠቃሚነት” በሚል መሪ ቃል የ2018 በጀት ዓመት የእዣ ወረዳ ጤና ጉባኤ ተካሄደ።

ጉባኤው በ2018 በጤናው ዘርፍ የተከናወኑ ሥራዎችንና የተገኙ ውጤቶችን በመገምገም፣ ያሉ ክፍተቶችን በመለየት ለ2019 በጀት ዓመት የሚተገበሩ የጤና አጀንዳዎችንና የሥራ አቅጣጫዎችን ለመወሰን ያለመ ነው።

በጉባኤው ላይ ንግግር ያደረጉት የእዣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘውዱ ዱላ ጤና ለሰው ልጅ መሠረታዊ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን ከምርታማነት፣ ከትምህርትና ከማህበረሰቡ አጠቃላይ ዕድገት ጋር የተቆራኘ መሆኑን ገልጸዋል።

የማህበረሰቡን የጤና ፍላጎት የሚመልሱ አዳዲስ አጀንዳዎችን በመንደፍና በተግባር በማስረገጥ ጤናማና ምርታማ ማህበረሰብ ለመገንባት በጋራ መሥራት እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

አመራሮችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት የጤና ሥራዎች ዘላቂና ውጤታማ በሆነ መንገድ እንዲቀጥሉ ትኩረት ሰጥተው መሥራት እንደሚጠበቅባቸው ጠቁመው፤ በየደረጃው ያለ አመራር የህዝብን አጀንዳ መሠረት በማድረግ ጤናን እንደ ቁልፍ የማህበረሰብ አጀንዳ በመቁጠር መሥራት እንደሚገባ አፅንዖት ሰጥተዋል።

በተለይም የግልና የአካባቢ ንጽህናን መጠበቅ፣ መንደሮችን ጽዱና ለኑሮ ምቹ ማድረግ የጤናማ ማህበረሰብ ግንባታ ዋና አካል በመሆኑ ሁሉም አካል በኃላፊነት ሊሳተፍ እንደሚገባም ገልጸዋል።

በመቀጠል የእዣ ወረዳ ጤና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መሀመድ ሰዒድ የ2018 በጀት ዓመት የጤና ዘርፉን አፈጻጸም፣ የተገኙ ውጤቶችን፣ የታዩ ክፍተቶችንና ለ2019 በጀት ዓመት የተያዙ የሥራ አቅጣጫዎችን በዝርዝር አቅርበዋል።

አቶ መሀመድ በንግግራቸው በ2018 በጤና ዘርፉ የተከናወኑ ሥራዎችን በመገምገም የተገኙ ውጤቶችን ማስቀጠልና ያሉ ክፍተቶችን በጋራ መፍታት እንደሚገባ አመልክተዋል።

በተጨማሪም የጤና አገልግሎቱ በሁሉም ደረጃ ተደራሽ፣ ጥራት ያለውና ለማህበረሰቡ ተጠቃሚ እንዲሆን የጤና ባለሙያዎች፣ አመራሮችና ማህበረሰቡ በቅንጅት መሥራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

ከጤና ጽህፈት ቤቱ የአፈጻጸም ሪፖርትና የ2019 የሥራ አቅጣጫ አቀራረብ በኋላ በቀረቡት ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች በጤና አገልግሎት ጥራትና ተደራሽነት፣ በማህበረሰብ ተሳትፎ፣ በጤና ተቋማት አፈጻጸምና በዘርፉ የሚታዩ ተግዳሮቶች ላይ ሀሳቦችን አንስተዋል።

በውይይቱ የተነሱ ሀሳቦችና የቀረቡ ጥያቄዎች በመጠናቀቅ፣ የጤና ዘርፉን ውጤታማነትና ተጠቃሚነት ለማሳደግ በትብብር መሥራትና የተለዩ ክፍተቶችን በቀጣይ ሥራ ላይ በተገቢው መንገድ ማስተካከል እንደሚገባ በመግባባት ላይ ተደርሷል።

የጉባኤው ማጠቃለያ አካል በመሆንም በ2018 በጀት ዓመት በጤና ዘርፍ የላቀ አፈጻጸም ላሳዩና ለጤና ሥራዎች አስፈላጊ ድጋፍና አስተዋፅዖ ላበረከቱ አካላት የማበረታቻና የዕውቅና ሽልማት ተበርክቷል።

ዕውቅናው ለሞዴል እናቶች፣ ለጤና ባለሙያዎች፣ ለጤና ጣቢያዎችና ጤና ኬላዎች፣ ለተቋማት፣ ለሊቀመንበሮች እንዲሁም በጤናው ዘርፍ በጎ አስተዋፅዖ ላበረከቱ ድርጅቶችና ሌሎች አካላት የተሰጠ ሲሆን፣ ሽልማቱ በዘርፉ የተመዘገቡ ጥሩ ተሞክሮዎችን ለማበረታታትና በቀጣይም የበለጠ ውጤት እንዲመዘገብ ለማነሳሳት ያለመ ነው።

See less

አዲሱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ አቶ ደምስ ገብሬ የሥራ ርክክብ አደረጉ

=======አዲሱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ አቶ ደምስ ገብሬ የሥራ ርክክብ አደረጉ

ወራቤ ፣መስከረም 26/2019 ፣ስልጤ ዞን ኮሙኒኬሽን

የክልሉ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ ሆነው አዲስ የተሾሙት አቶ ደምስ ገብሬ ከቀድሞ የቢሮው ኃላፊ ከነበሩት ከአቶ ሰላሙ አማዶ ጋር የሥራ ርክክብ አድርገዋል።

እስካሁን በዘርፉ የተመዘገቡ ስኬቶችና በቀጣይ የለውጥ ዓመታት የሚተገበሩ የልማት ዕቅዶችን ለአዲሱ ኃላፊ የማስተዋወቅና የማስረከብ ሥራ ተከናወኗል።

በርክክቡ ወቅት የቀድሞው የቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ ሰላሙ አማዶ ለአዲሱ ኃላፊ በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፎች የሚከናወኑ የሥራ እንቅስቃሴዎች ገለጻ አድርጓል።

አቶ ሰላሙ አማዶ በቆይታቸው ከተቋሙ ማኔጅመንትና አጠቃላይ ሠራተኞች በመቀናጀት ያከናወኗቸውን የሥራ ስኬቶች የገለጹ ሲሆን

አዲስ ለተሾሙት የቢሮው ኃላፊ መልካም የስራ ዘመንና የትጋት ጊዜ እንዲሆን ምኞታቸውን ገልጸዋል።

የቢሮው ለአዲሱ ኃላፊ አቀባበል እና ለቀድሞው ኃላፊ ሽኝት ያደረገ ሲሆን የቢሮው ምክትል ኃላፊዎችና ማኔጅመንት አባላት በሰጡት አስተያየት የቀድሞ ኃላፊ ላበረከቱት አገልግሎትና ላከናወኑት የሥራ አፈጻጸም አድናቆታቸውን ገልጸው፣ በቀጣይ የሥራ ዘመን መልካም ስኬትን ተመኝተዋል።

አዲሱ የቢሮ ኃላፊ አቶ ደምስ ገብሬ ለተደረገላቸው አቀባበል ምስጋና አቅርበው፤ በሚኖራቸው ቆይታ ቢሮውን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።

በሥራ ርክክቡ ወቅት የቢሮው ምክትል ኃላፊዎች፣ የማኔጅመንት አባላትና እንዲሁም ጠቅላላ ሠራተኞች ተገኝተዋል።

See less

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዛሬ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያደረጉት ንግግር ዋና ዋና ነጥቦች

======ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዛሬ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያደረጉት ንግግር ዋና ዋና ነጥቦች

✍ የኢትዮጵያ ሕዝብ በበርካታ ውዥንብሮች እና የጸጥታ ፈተናዎች ውስጥ አልፎ በምርጫው ላሳየው ተሳትፎ በማመስገን፤ ይህ ሂደት የኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ባህል መሠረት እየጠነከረ መምጣቱን አረጋግጧል ብለዋል።

✍ ዓለም ፈጣን፣ ያልተጠበቀ እና መተንበይ በማይቻል የጂኦፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ለውጥ ውስጥ መሆኗን ጠቁመዋል።

✍ ኢትዮጵያ ባለፈው ታሪኳ ከኢንዱስትሪ አብዮቶችም ሆነ ከውጭ ወረራዎች አኳያ በነበራት አለመዘጋጀት የከፈለችውን ዋጋ በማስታወስ፣ አሁን ላይ ለሚመጣው የዓለም ለውጥ በንቃት መዘጋጀት እንዳለባት አሳስበዋል።

✍ ኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ቀንድ ቀጣና በቀይ ባሕር እና በሕንድ ውቅያኖስ መገናኛ ላይ እንዲሁም በዓለም የነዳጅ መተላለፊያ አቅራቢያ መገኘታቸው ልዩ ዕድልም ፈተናም መሆኑን ጠቅሰው፣ አቅም ገንብተን ጠንክረን ከተገኘን የራሳችንን ዕድል ራሳችን እንደምንወስን፣ ከደከምን ግን ሌሎች እንደሚወስኑብን አብራርተዋል።

✍ የሀገራችንን የዘመናት ቁጭት ወደ ሥልጣኔ ለመቀየር መፍትሔው የውጭ አስተሳሰቦችን እንዳለ መገልበጥ ሳይሆን፣ ነባር እና ሀገር በቀል እሴቶችን ከውጭው ጠቃሚ ዕውቀት ጋር በማዋሃድ በመደመር እሳቤ የኢትዮጵያን ሥልጣኔ መገንባት መሆኑን አስምረውበታል።

✍ ባለፉት ዓመታት ከተናጠል ዘርፍ ወደ ብዙኃ ዘርፍ በመሸጋገር በተተገበሩ ሪፎርሞች በማክሮ ኢኮኖሚ፣ በዲጂታል ቴክኖሎጂ፣ በግብርና፣ በኮሪደር እና የቱሪዝም ልማት፣ በአረንጓዴ አሻራ፣ እንዲሁም የልማት ድርጅቶችን ከኪሳራ በማውጣት በኩል ተስፋ ሰጪ ውጤቶች መመዝገባቸውን ዘርዝረዋል።

✍ ሀገራችን የገጠሟትን የኮቪድ-19 ጫና፣ የውጭ ዲፕሎማሲያዊ መገለል እና የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታን ለማስተጓጎል የተደረጉ ሙከራዎችን በጽናት መሻገሯን በማንሣት የኢትዮጵያን አይበገሬነት ማረጋገጥ ተችሏል ብለዋል።

✍ መንግሥት በቀጣይ የሥራ ዘመኑ በሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ግኝቶች ላይ ተመሥርቶ የሕገ-መንግሥት ማሻሻያ እንደሚያደርግ፣ ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር በጋራ እንደሚሠራ፣ እንዲሁም የጀመረውን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ከግብ እንደሚያደርስ ቃል ገብተዋል።

✍ ሙስናን፣ ሌብነትን እና አድሎአዊ አሠራሮችን ለማስወገድ መንግሥት ጥብቅ እርምጃዎችን እንደሚወስድ፣ የሲቪል ሰርቪስ አሰጣጥን እንደሚያዘምን እና የትምህርት ጥራትን በማስጠበቅ በትውልድ ግንባታ ላይ አበክሮ እንደሚሠራ አረጋግጠዋል።

✍ የኢትዮጵያን የባሕር በር ፍላጎት ከጎረቤት ሀገራት ጋር በሰላምና በጋራ ተጠቃሚነት ላይ በተመሰረተ የ”ሰጥቶ መቀበል” መርህ ለማሳካት እንደሚሠራ ጠቁመዋል።

✍ በቀጣናው የአየር የበላይነትን ጨምሮ ሀገራችንን ከማንኛውም ጥቃት አስቀድሞ መከላከል እና ማሸነፍ የሚችል ዘመናዊ፣ ፈጣሪ እና ዝግጁ የሆነ የመከላከያ እና የደኅንነት ኃይል እንደሚገነባ አብራርተዋል።

✍ በጫካ ያሉ ታጣቂዎች ወደ ሰላማዊ መንገድ እንዲመጡ፣ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ለብሔራዊ ጥቅም እንዲቆሙ፣ ወጣቶች እና አረጋውያን በዕውቀት እና በሥነ-ምግባር የሀገር ግንባታ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

✍ አዲሱ ፓርላማም የመንግሥትን ሥራዎች በቅርበት እንዲከታተል እና እንዲመራ አደራ ብለዋል።

#ትልቅ_ሀገር! #ትልቅ_ሕዝብ! #ታላቅ_ርዕይ!

#Ethiopia#EBC#Medemer#የመደመርመንግሥት

See less