በጉራጌ ዞን የእናቶች ቀን (አንትሮሽት) በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።

በጉራጌ ዞን የእናቶች ቀን (አንትሮሽት) በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።

የእናቶች ቀን (አንትሮሽት) በየዓመቱ በጥር ወር እናቶች ለትውልድ ቀጣይነት፣ ለሀገር ሰላምና ልማት መረጋገጥ ላበረከቱት ወደር የሌለው አስተዋጽኦዋቸው ከስራ ነጻ ሆነው በባሎቻቸውና በልጆቻቸው የተለያዩ ስጦታ በማበርከት እንክብካቤ ይደረግላቸዋል።

አንትሮሽት በጉራጌ ብሄረሰብ ዘንድ ፈረንጆች “ማዘር ዴይ” ብለው እንደሚያከብሩት ለረጅም ዘመናት ሲከበር እንደነበር የተለያዩ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

በፕሮግራሙ የክልል፣ የጉራጌ ዞን፣ የምስራቅ ጉራጌ ዞን፣ የወልቂጤ ዩኒቨርስቲና የወረዳ የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም የኦቢኤን ሆርን ኦፍ አፍሪካ ቴሌቪዥን ስራ አስኪያጅ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ እናቶችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በጉመር ወረዳ አበኬ ቀበሌ ላይ እየተከበረ ይገኛል።

በአገና ደብረ -ምጥማቅ ቅ/ድንግል ማርያም ቤተክርስቲያን በድምቀት እየተከበረ ይገኛል ።

የአስትሪዮ አመታዊ ክብረ በዓል
በአገና ደብረ -ምጥማቅ ቅ/ድንግል ማርያም ቤተክርስቲያን በድምቀት እየተከበረ ይገኛል ።
የአገና ደብረ ምጥማቅ ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተክርስቲያ ከተመሰረተ ከ108 ዓመት በላይ ሲሆን የጥንታዊ ቅርስ ባለቤትሞ ጭምር ነው ።

እጅግ ጥንታዊ ፡ ታሪካዊና እድሜ ጠገብ ቅርሶች

 

የአትርፎ ደብረ-ወርቅ ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድሪያል

ታምረኛው ፡ እጅግ ጥንታዊ ፡ ታሪካዊና እድሜ ጠገብ ቅርሶች ባለቤት የሆነውን በ12ኛው መቶ ክፈለ-ዘመን የተመሰረተው የትርፎ ደብረ-ወርቅ ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድሪያል ” የደቡብ ቁልቢ ” ከብዙው በጥቂቱ እናስተዋውቆ !!

እዣ ወረዳ በጉራጌ ዞን ከሚገኙ እጅግ አስደናቂ የሆኑ ታሪካዊ ፡ ተፈጥሮአዊ እና ባህላዊ ለቱሪስት ቀልብ የሚስቡ መስህቦች መገኛ ከሆኑት አካባቢዎች ውስጥ በግንባር ቀደም ተጠቃሽ ስትሆን እጅግ ማራኪና የአየር ንብረ ለውጥ ለመከላከል የሚያስችሉ ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ ደኖች ፡ ውብና ማራኪ ፏፏቴዎች ፡ ትክል ድንጋዮች ፡ ጥንታዊና በውስጣቸው እድሜ ጠገብ ቅርሶችን የያዙ ገዳማት ፡ መስጂዶች እና ካቴድሪያሎች ተጠቃሾች ናቸው ።

ከነዚህም መካከል እጅግ ታሪካዊ ፡ ጥንታዊና የሀገር ውስጥና የውጭ የጎብኚዎች ቁጥር እየጨመረ ያለው የአትርፎ ደብረ-ወርቅ ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድሪያል “የደቡብ ቁልቢ ” ከብዙው በጥቂቱ እናስተዋውቆ ።

የአትርፎ ደብረ-ወርቅ ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድሪያል በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ ገደብ ቀበሌ የገረሙጀ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ከዞናችን ዋና ከተማ ወልቂጤ በ52 ኪ ሜ እና የእዣ ወረዳ ዋና ከተማ ከሆነችው አገና በ10 ኪሜ ርቀት በስተ-ምስራቅ አቅጣጫ የሚገኝ ነው።

ካቴድሪያሉ በ12ኛው መቶ ክፈለ-ዘመን በስደት ከአክሱም ፂዮን “ወሰናይ ” ተብለው ይጠሩ በነበሩት አባት ከብዙ በጉዞአቸው ላይ ከነበረው ከድቅና ብዙ ታዓምር በኋላ ይዘው በማምጣት እንደሰየሙት በጉራጌ ሀገረ-ስብከት የእዣ ወረዳ ቤተ-ክህነት ስራስኪያጅ እና የአትርፎ ደብረ-ወርቅ ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድሪያል አስተዳዳሪ የሆኑት መላከ ብርሃን ብስራት አካለ ወልድ ይናገራሉ ።

በየ ዓመቱ ጥር 18 በርካታ የውጭና የሀገር ውስጥ ቱሪስቶች በመሳተፍ በድምቀት የሚከበረው ካቴድሪያሉ በአባታችን በአቡነ መልከ-ፄዲቅ ከተለያየ ቦታ በመምጣት እጅግ ቁጥር ያላቸው እንግዶች በክብረ -በዓሉ መገኘትና የተሳሉትን ስለት ቶሎ የሚሰማ መሆኑን ብዙዎቹ በመመስከራቸው ምክንያት ” የደቡብ ቁልቢ ” የሚል ስያሜ እንደሰጡትም የደብሩ አስተዳዳሪ መላከ ብርሀን ብስራት አካለወልድ ያስረዳሉ ።

በካቴድሪያሉ ከነሀስና ብር የተሰሩ ጥንታዊ መስቀሎች ፡ ፅዋዎች ፡ የተለያዩና እድሜ ጠገብ የብራና መፅሀፎች ፡ የጥበቃ መሳሪያዎችና በርካታ ቅርሶች የሚገኙ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ በቀድሞ ሀገርመሪ በነበሩ እንደ አፄ ሚኒሊክ ፡ ደጅ አዝማች ፡ ደጅ አዝማች ባልቻ ፡ ደጅ አዝማች ሀብተ -ጊዮርጊስ የተበረከቱ ቅርሶች በካቴድሪያሉ ቅጥር ግቢ ውስጥ በተሰራው ዘመናዊ ሙዚየም ውስጥ መመልከት ወይም መጎብኘት ይቻላል ።

ካቴድሪያሉ ከሀይማኖት ስርዓት በተጨማሪ ከእምነቱ ተከታዮች ውጪ ያሉትም ጨምሮ በተለያየ ማህበራዊ ችግር ያለባቸውን ሰዎች ድጋፍ በማድረግ የሚታወቅ ሲሆን በደንና አካባቢ ጥበቃ ስራ አሻራ እያኖረ ያለና ከቫይረሱ ጋር ለሚኖሩ 22 ወገኖች በቋሚነትም ይረዳል ።

በየዓመቱ ጥር 18 እጅግ በአስደናቂ ሁኔታ የሚከበረው የአትፎ ደብረ-ወርቅ ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድሪያል በወረዳው የቱሪስት ፍሰት እንዲጨምር በማድረግና የገቢ አቅም በማሳደግ ረገድ የራሱ ድርሻ እንዳለውም የሚታመን ነው ።

ይህን ታሪካዊ ፡ ተፈጥሮዓዊ እና የበርካታ ቅርስ ባለቤት የሆነውን ካቴድሪያል እንድትጎበኙ እንጋብዛለን ።

“አንትሮሽት” የጉራጌ የእናቶች በዓል በጉራጌ ዞን በእዣ ወረዳ በቀጣነ ቀበሌ በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት እየተከበረ ይገኛል ።

=============================

“አንትሮሽት” የጉራጌ የእናቶች በዓል በጉራጌ ዞን በእዣ ወረዳ በቀጣነ ቀበሌ በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት እየተከበረ ይገኛል ።

“አንትሮሽት” እናቶች ለትውልድ ቀጣይነትና ለሀገር ስልጣኔ ያበረከቱትን አስተዋጽኦ ትልቅ በመሆኑ ውለታቸውን ለማስታውስ፣ ክብር ለመስጠትና ለማመስገን የሚደረግ ክብረ በዓል ነው።

ይህም በዓል የሚከበርላቸው እናቶች እድሜ ጠገብ የሆኑ የልጅ ልጅ ያዩ እናቶች ቤት የሚከበር ሲሆን ዕለቱ ግን ሁሉም እናቶች ያካተተ በዓል ነው፡፡

ይህ የእናቶች ቀን በሀገር አቀፍ የሁሉም በዓል እንዲሆን ከማድረግ ባለፈ በአለም አቀፍ ደረጃ በቀጣይ ለማስተዋወቅ በትኩረት መሰራት ይኖርበታል።

ዝርዝሩን እናደርሳለን ይጠብቁን !!

በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ ቆጠር ገድራ ቀበሌ ነቖ ወይንም የጉራጌ የልጃገረዶች ቀን በዓል በድምቀት ተከብሯል ‼️

=======================================

በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ ቆጠር ገድራ ቀበሌ ነቖ ወይንም የጉራጌ የልጃገረዶች ቀን በዓል በድምቀት ተከብሯል ‼️
የጉራጌ ብሔረሰብ የበርካታ ባህሎች ባለቤት በመሆኑ አሁንም ትኩረትና ክትትል በማድረግ በተለያዩ ጥናቶች በመደገፍ ባህሉን ለማልማትና ለትውልድ ይዘቱ ጠብቆ ለማስተላለፍ የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል ይገባል።
የእዣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘውዱ ዱላ እለቱን አስመልክተው እንደተናገሩት ነቆ ረጅም ታሪክ ያለውና ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተቀዛቀዘ የመጣ በመሆኑ መንግስትና ማህበረሰቡ በመተባበር ባህሉ እንዲጠናከር በማድረግ ዳግም ሚያንሰራራበት ሁኔታ እየተፈጠረ ይገኛል።

የጉራጌ ዞን ባህልቱሪ ዝም መምሪያ ሀላፊ ወ/ሮ መሰረት አመርጋ በበኩላቸው ነቆ የልጃገረዶች በዓል ሲሆን በዓመት ጥር ወር የሚገናኙበት ተሰብስበው የጋራ አላማቸው ሚያቅዱበት ነው ብለዋል።

የእዣ ወረዳ ባህል ቱሪዝም ፅ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ የሺ ተካ ነቆ ልጃገረዶች በድምቀት እንዲያከብሩ ወላጆች አስፈላጊው እገዛ የሚያደርጉላቸው ሲሆን ልጃገረዶቹም ማንነታቸው ሚያውጁበትና ፍላጎታቸውን የሚገልፁበት ነው ብለዋል ።
በዕለቱም ነቆ ወይንም የልጃገረዶች በዓል በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሮ ውሎአል ።

በጉራጌ ዞን የእዣ ወረዳ የ2016 በጀት ዓመት የ6 ወር የአመራር የብቃት ማረጋገጫ የምዘና ከትላንትና ጀምሮ ዛሬም ተጠናክሮ ቀጥሏል ።

============================

በጉራጌ ዞን የእዣ ወረዳ የ2016 በጀት ዓመት የ6 ወር የአመራር የብቃት ማረጋገጫ የምዘና ከትላንትና ጀምሮ ዛሬም ተጠናክሮ ቀጥሏል ።

በዚህ ምዘና መድረክ የፓርቲና የመንግስት ስራዎች የ6ወር አፈፃፀም ግምገማ ለአመራሩ ምዘና ውጤት የሚሰጥበት መሆኑን የተገለፀ ሲሆን ምዘናው የፓርቲና የመንግስት ተግባራት የተፈፀሙበት አግባብን በመገምገም አመራሩ ለቀጣይ የፓርቲና የመንግስት ስራዎች ራሱን በደንብ እንዲያዘጋጅ አቅም የሚፈጥር እንደሆነም ተጠቁሟል።

በቀጣይም የፓርቲና የመንግስት ስራዎችን አፈፃፀም መሰረት በማድረግ አመራሩ ያለበትን ቁመና የሚለካበት መሆኑንና ለተግባር አፈፃፀም ማነቆ የሆኑ ችግሮች ተለይተው የመፍትሄ አቅጣጫ የሚሰጥባቸው መሆኑንም ተመላክቷል።

ኢትዮጵያ የባሕር በር የምታገኝበትን የመግባቢያ ስምምነት ከሶማሊ ላንድ ጋር ተፈራረመች

May be an image of map and text

====================================

ኢትዮጵያ የባሕር በር የምታገኝበትን የመግባቢያ ስምምነት ከሶማሊ ላንድ ጋር ተፈራረመች
****************
ኢትዮጵያ የቀይ ባሕር በር ለማግኘት እና ለማልማት የሚያስችላትን ስምምነት ከሶማሊ ላንድ ጋር ፈፅማለች።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የሶማሊ ላንድ ፕሬዚዳንት ሙሴ ባሂ ሁሉን አካታች የሆነውን የጋራ መግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል።
በዚሁ መሠረት ለብዙ ዘመናት ወደብ አልባ ሆና የቆየችው ሀገራችን ከሶማሊ ላንድ ጋር ባደረገችው ስምምነት በሊዝ የወደብ ባለቤት መሆን ያስችላታል ሲል EBC ዘግቧል ።

ገዢ ትርክት

=======================

ገዢ ትርክት አንድነቷን የጠበቀች አገር ለመገንባት የነገ ሀገር ተረካቢ ትውልድ ለማነፅ በእጅጉ የሚያስፈልግ በመሆኑ የጋራ እሳቤዎቻችንን በማጉላት ሀገራችን ለማበልፀግ ሁሉም የድርሻውን መወጣት ይገባል !!
በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ ከእዳ ወደ ምንዳ በሚል መርህ 3ኛ ቀኑን የያዘው የሲቭል ሰርቫንቱ ስልጠና ሀገራዊ ገዢ ትርክት በሚል ርዕስ ዛሬም ተጠናክሮ ቀጥሏል ።
ሰነዱን ያቀረቡት የእዣ ወረዳ ረዳት የመንግስት ተጠሪ አቶ ሸምሱ አክመል ትርክት ማለት የአንድ ማህበረሰብ የወል ማንነት ለመግለፅ የሚያስፈልጉ የተሰነዱ እና በማህበረሰቡ ምግባር በሰፊው ተቀባይነት ያገኙ ታሪካዊ ክስተቶች ፡ ቁሳዊና ኢ -ቁሳዊ ትሩፋቶችና እሴቶች ማለት እንደ ሆነ አመላክተዋል ።
አብሮነትን በማጠናከርና ሰላማዊ መስተጋብርን ለመፍጠር ትርክት እና ስነ-ምግባር ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳለው በሰነዱ አቶ ሸምሱ አመላክተዋል ።
ትርክት አዎንታዊና አሉታዊ በሚል ሁለት ገፅታዎች ያሉት ሲሆን ነጠላ እና ገዢ ትርከት በሚል በሁለት የሚከፈል እንደሆነም በሰነድ በማብራራት ከነጠላ ትርክ ይልቅ ገዢ ትርክት ለሀገር አብሮነትና አድነት መሰረት ሆኖ የሚያገለግል መሆኑንም ተገልጿል ።
በአጠቃላይ ገዢ ትርክት አንድነቷን የጠበቀች አገር ለመገንባት የነገ ሀገር ተረካቢ ትውልድ ለማነፅ በእጅጉ የሚያስፈልግ በመሆኑ የጋራ እሳቤዎቻችንን በማጉላት ሀገራችን ለማበልፀግ ሁሉም የድርሻውን መወጣት እንደሚገባ ተመላክቷል ።
የቀድሞ መጥፎ የሆኑ ታሪኮች ብቻ ነጥሎ በማውጣት ዛሬን አንድ እንዳንሆንና በሰላም እንዳንኖር የሚደጉት የፖለቲካ ሸፍጦች በመለየት የበለፀገች ሀገር ለመገንባት ፐብሊክ ሰርቫንቱ የድርሻውን መወጣት ይገባል።
ብሄራዊነት ሀገራዊ አንድነት ሳይሸረሽር የጋራ አላማዎችን የሚያጠናክር በመሆኑ ብልፅግና ፓርቲም ብሄራዊነትን ገዢ ትርክት በማድረግ በሁለንተናዊ መልኩ ያደገች ሀገር ለመገንባት አንግቦ እየተንቀሳቀሰ መሆኑንም በሰነዱ ተገልፆአል።
ይህን ሰነድ መነሻ በማድረግ በ3ቱም ቡድኖች ሰፊ ውይይት እየተደረገ ይገኛል ።

ያለንን ሀብት በአግባቡ በመጠቀም የበለፀገች ኢትዮጵያ ለመፍጠር ሲቭል ሰርቫንቱ የድርሻውን መወጣት እንዳለበት ተገለፀ።

ያለንን ሀብት በአግባቡ በመጠቀም የበለፀገች ኢትዮጵያ ለመፍጠር ሲቭል ሰርቫንቱ የድርሻውን መጣት እንዳለበት ተገለፀ።
በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ ከእዳ ወደ ምንዳ በሚል ሀሳብ በዛሬው እለት በሀብት አስተዳደር መፍጠርና አጠቃቀም ዙሪያ ያተኮረ ስልጠና ተሰጥቷል።
የስልጠናው ሰነዱ ያቀረቡት የእዣ ወረዳ ረዳት የመንግስት ተጠሪ አቶ አብድራህማን ሀሰን እንደገለፁት ሁሉም በተሰማራበት ጊዜን በአግባቡ በመጠቀም እራሳን ብሎም ሀገራችን መቀየር አለበት ።
በተለይም የጊዜ ታካኪነት በትላንት ወይም በዛሬ ብቻ ባለማሳበብ ለምን ይህ ሆነ ብሎ በማሰላሰል ከችግሮቻችን ተምረን አመለካከት በአንድ ጀንበር እንደማይቀየር በመገንዘብ ሀገር ማሳደግ እንደሚገባም በሰነዱ አመላክተዋል ።
በመደመር እሳቤ ሀገራዊ አንድነት የዜጎች ክብር በማስጠበቅ ብልፅግናን ማረጋገጥ እንደሚገባ በሰነዱ የተመላከተ ሲሆን የብልፅግና ማማ የደረሱ ሀገሮች ዋናው ሚስጥራቸው በትንሹ ሳይረኩ ጊዜን በአግባቡ ተጠቅመው ሌት ተቀን በልፋታቸው እዚህ መድረሳቸው መረዳት አለብንም ብለዋል ።
የትውልድ ሀብትና የብሄራዊ ሀብት እንዳይባክን እንዲሁም ሀብት ለመፍጠር የሚገጥሙ ተግዳሮቶች በመለትና መፍትሄ በማበጀት ወደ ተግባር ከመግባት አንፃር የብልፅግና ፓርቲ አመራርና አባላት በቁርጠኝነት ሊሰሩ የሚገቡ ስራዎች መኖራቸውንም ተገልጿል።
ካነጋገርናቸው ተሳታፊዎች መካከል አቶ ሽለጋ ምራኒ ፡ /ሮ ሙሉ ስፍር እና ወ/ሮ ዙርያሽ ሀይሌ በሰጡት አስተያየትም በየቦታው በእጃችን ያሉ ሀብቶች የራሳችን አድርገን አስተሳሰባችን በማጎልበት ሰርተን የኑሮ ውድነት መቀነስ ይገባናልም ብለዋል ።
በተለይም እንደ ወረዳው መልማት ሲገባቸው ያለሙ እና በባህር ዛፍ የተሸፈኑ መሬቶች ከታካኪነት አስተሳሰብ ወጥተን በተለያዩ የግብርና ዘርፎች ሁሉም ፐብሊክ ሰርቫንቱ በያለበትና በሚችለው አቅም መስራትና ማስተባበር እንደሚገባም አስተያየት ሰጪዎቹ ጨምረው ገልፀዋል ።
በእለቱም በ3ቡድኖች የተነሱት አስተያየቶችና ጥያቄዎች በየቡድኑ አወያዩች ሀሳብ ተሰጥቶባቸዋል ነው ።