ፅ/ቤቱ የ2016/17 ምርት ዘመን የተቀናጀ የግብርና ልማት ስራዎች የንቅናቄ መድረክ አካሂዷል ።

============================

በዘንድሮ መኸር ወቅት በዋና ዋና ሰብሎች 9129.5 ሄ/ር መሬት በማልማት 853ሺህ 950 ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ ግብ ተጥሏል እየተሰራ መሆኑን በጉራጌ ዞን የእዣ ወረዳ ግብርና ልማት ፅ/ቤት አስታወቀ ።
ፅ/ቤቱ የ2016/17 ምርት ዘመን የተቀናጀ የግብርና ልማት ስራዎች የንቅናቄ መድረክ አካሂዷል ።
በእለቱም መድኩን የመረቱ የጉራጌ ዞን ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት መምሪያ ሀላፊ ወ/ሮ ትብለጥ እስጢፋኖስ እንደገለፁት የግብርናው ዘርፍ እንደ ሀገር የሚደረገው ኢኮኖሚያዊ መዋቅራዊ ሽግግር የማይተካ ሚና አለው ።
ግብርናው የምግብ ዋስትናን ለማወጋገጥ እንዲሁም እንደ ሀገር የገጠመውን የዋጋ ንረት እና የኑሮ ውድነት ለመዋጋትና ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ የዳበረ ኢኮኖሚ ለመገንባት አይተኬ ሚና አለው ያሉት ሀላፊዋ አርሶአደሩ አመለካከት መለወጥ ሚቻለው ሙያተኛው በቁርጠኝነት መስራት ሲችሉ መሆኑን ተገንዝቦ በሁሉም የግብርና ዘርፎች የአርሶአደሩ የማምረት አቅሙ እንዲጨምር መስራት ያስፈልጋልም ብለዋል።
በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ ከምናመርትበት አካሄድ በአመት ከ3 ጊዜ በላይ ማምረት የምንችልበት የተለያዩ ሀገራዊ መነሳሳቶች ተቀርፀው ወደ ተግባር እንቅስቃሴ ተገብቷል ያሉት ወ/ሮ ትብለጥ እንደ ወረዳውን ይህንን ግብ መሳካት እንዲቻል በተለይም አመራሩና ባለሙያው ከወትሮ በተለየ ድጋፍ ትኩረት ሰጥቶ መረባረብ ይገባልም ብለዋል።
የእዣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘውዱ ዱላ በበኩላቸው እንደ ሀገር ከተረጂነት ተላቀን ወደ ምርትና ምርታማነት ለማሳደግና ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ኢኮኖሚ የመገንባት ግባችን ለማሳካት ቁልፍ ሚና ይጫወታል ብለዋል ።
እንደ ወረዳው በዘንድሮ ዓመት በትኩረት መምራት የተጀመሩ ያልታረሱ መሬቶች በስፋት የማረስ ፡ የ30-40-30 የፍራፍሬ ልማት ፡ ለምግብ ዋስትና ቁልፍ ሚና ሚጫወተው የእንሰት ልማት ስራ በስፋት የማልማትና በሽታን የመከላከል አፅዕኖት ተሰርቶት እንደሚሰራም ዋና አስተዳዳሪው አመላክተዋል።
ከዚህ በተጨማሪ እንደ ወረዳው ግብርናው በይበልጥ እንዲሻሻል ማነቆ ሆነው የተለየትን ጉለቶች በማረም የቡና ልማት ስራዎች ፡ የስራስርና የአዝዕርት ልማት እንዲሁም የአትክልት ስራዎች ፡ የሌማት ትሩፋት እና የአረንጓዴ አሻራ ልማት ልዩ ትርጉምና ትኩረት ይሻሉ ያሉት አቶ ዘውዱ ይህንኑ እውን ለማድረግ ከአመራር ጀምሮ እስከ አምራች አርሶአደር ድረስ በዚህ መኸር ልዩ ትኩረት መስጠትና ጠንካራ የማስፈፀም አቅም በመገንባት በሂደቱም በርካታ የስራ እድል በመፍጠር የተጀመረው የብልፅግና ጉዞ ለማረጋገጥ ሃላፊነታችን በአግባቡ መወጣት ይገባናልም ብለዋል ።
የእዣ ወረዳ ግብርና ልማት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ መቻል ተሰማ በ2016 በጀት ዓመት በእስካሁን ሂደት ዋና ዋና ወቅታዊ የግብርና ስራዎች ሰፊ ርብርብ በማድረግ ግብርናው ላይ ያሉት ማነቆዎችን ለመፍታት በርካታ ተግባራት የተፈፀመ ሲሆን በቀጣይም በመኸር እርሻ ሰፊ ርብርብ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል ።
በወረዳው በዘንድሮ መኸር ወቅት በአዝዕርት ፡ በፍራፍሬ ፡ በሆልቲከልቸር ሰብሎች 9129.5 ሄ/ር መሬት በማልማት 853ሺህ 950 ኩንታል ምርት ለማልማት ግብ ተጥሏል ያሉት ሀላፊ በዚህም ከ10 ሺህ በላይ አርሶአደሮች ተሳታፊም ይሆናሉ ብለዋል ።
የደንና አግሮፎረስተሪ ችግኝ ተከላ 9.5 ሚሊየን ችግኞችን የሚተከሉ ሲሆን ሌሎችም በርካታ የግብርና ልማት ስራዎች በተቀናጀና በተደራጀ መልኩ እንዲከናወኑ አስፈላጊውን የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ መሆኑንም የገለፁት አቶ መቻል ይህንኑ በሚገባ ተግባራዊ ለማድረግ ባለድርሻ አካላት የድርሻቸውን መወጣት እንዳለባቸውም መልዕክት አስተላልፈዋል ።
ተሳታፊዎቹም በሰጡት አስተያየትም በሁሉም ቀበሌዎች የተለዩት አርሶአደሩን በአግባቡ ያለማስጠቀም ጉለቶች እንዲታረሙ በባለቤትነት በመውሰድ የአርሶአደሩ ምርትና ማርታማነት ለማሳደግ በትኩረት እንደሚሰሩም ተናግረዋል ሲል የዘገበው የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው።

 

በጉራጌ ዞን የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ የ2ኛ ቀን ፈተና

============

በጉራጌ ዞን የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ የ2ኛ ቀን ፈተና የዞኑ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ክብሩ ፈቀደ፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ት/ቢሮ የትምህርት ልማት ዘርፍና የቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አስከብር ወልዴ እና የዞኑ ት/ት መምሪያ ኃላፊ አቶ መብራቴ ወ/ማርያም ሶር ገረፋ ት/ቤት ተገኝተው አስጀምረዋል።
በዞኑ ፈተናው በሁሉም ጣቢያዎች በጥራት ከኩረጃ ነፃ በሆነ ሁኔታ እየተሰጠ እንደሚገኝ ማረጋገጣቸውን ገልጸዋል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ት/ቢሮ የትምህርት ልማት ዘርፍና የቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አስከብር ወልዴ የ8ኛ ክፍል የ2ኛ ቀን ፈተና ሲያስጀምሩ እንዳሉት ተዘዋውረው እንዳዩት ፈተናው ሂደቱን ጠብቆ በጥሩ ሁኔታ እየሄደ ነው።
በፈተና ሂደቱ ተማሪዎች ያለምንም ኩረጃ በራሳቸው ጥረት ተረጋግተው እየተፈተኑ መሆናቸውን፣ ፈታኝ መምህራን፣ ሱፐርፋይዘሮችና የፈተና ጣቢያ ኃላፊዎች የተሰጣቸውን ኃላፊነት በአግባቡ እየተወጡ መሆናቸውን ማረጋገጣቸውን ገልጸዋል።
ለዚህም የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በተሻሉ መምህራን የቲቶሪያል ትምህርት በአካልና በቪዲዮ በመስጠት ተማሪዎች ለፈተናው ብቁና በራስ የመተማመን መንፈስ እንዲያዳብሩ በትኩረት መሰራቱን አቶ አስከብር ጠቁመዋል።
የጉራጌ ዞን ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ክብሩ ፈቀደ የዛሬ ፈተና ሲያስጀምሩ እንደገለጹት ክልል አቀፍ ፈተናው የትምህርት ጥራት ለማረጋገጥ የሚደረገው ጥረት ውጤታማ እንዲሆን ከሌላ ጊዜ በተለየ ትኩረት እየተሰጠ ነው።
ኩረጃ ለማስቀረት የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በዩኒቨርስቲና የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች በክላስተር ማዕከል መሰጠቱ በራሳቸው የሚተማመኑ እውቀት ያላቸው ሀገር ተረካቢ ትውልድ ለማፍራት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት አቶ ክብሩ ገልጸዋል።
አክለውም በዞኑ 326 ትምህርት ቤቶች ላይ ከ25 ሺህ በላይ የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተናውን ተረጋግተው እየተፈተኑ መሆኑን ጠቁመዋል።

ትምህርት ቤቶች ሁለተናዊ እድገት የቀድሞ ተማሪዎች ህብረት እያደረጉት የሚገኘው እንቅስቃሴ የሚበረታታ እንደሆነ ተገለፀ ።

=======================================

ትምህርት ቤቶች ሁለተናዊ እድገት የቀድሞ ተማሪዎች ህብረት እያደረጉት የሚገኘው እንቅስቃሴ የሚበረታታ እንደሆነ ተገለፀ ።
በአገና ከተማ አስተዳደር የየስራይ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በቀድሞ ተማሪዎች የመጀመሪያ ዙር የእድሳት ስራ ተጀምሯል።
የአገና ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሀብቴ ዘርጋ የእድሳት ስራው በተጀመረበት ወቅት እንደገለፁት የትምህርት ጥራትና ተደራሽነት ለማሻሻል የትምህርት ማህበረሰቡ በየአካባቢው የሚገኙ ትምርት ቤቶች ግንባርቀደም ተሳታፊ ሊሆኑ ይገባል ።
የትምህርት ቤቶች ሁለተናዊ እድገት የቀድሞ ተማሪዎች ህብረት እያደረጉት የሚገኘው እንቅስቃሴ የሚበረታታ እንደሆነ የገለፁት ከንቲባው የየስራይ ትምህርት የቀድሞ የተማሪዎች ህብረት በራሳቸው ተነሳሽነት ትምህርት ቤቱ ለማሳደስና ለማሳደግ እያደረጉት ያለው እንቅስቃሴ የሚበረታታ ነው ብለዋል ።
ምቹ የማማሪያ ክፍሎች ፡ ፅዱና ሳቢ የሆነ የትምህርት ቤት አካባቢ መፍጠር የመማር ማስተማር ስርዓት ለማሻሻል ከሚረዱ ጉዳዮች አንዱ ነው ያሉት አቶ ሀብቴ የከተማው አስተዳደርም በሙያዊና በሌሎችም ጉዳዮች በማገዝ የድርሻውን ይወጣል ብለዋል።
ትምህርት ቤቱ እንዲያድግ የተጀመረው እንቅስቃሴ ይበል የሚያሰኝ በመሆኑ ይህንን አላማ እንዲሳካ ርብርብ እያደረጉት ያሉ አካላት ምስጋና ይገባቸዋል ያሉት ከንቲባው ስራው በተባለለት ጊዜ እንዲሳካ ማንም በሚችለው አቅም ለነገ ትውልድ ሲል ድጋፍ ማድረግ እንዳለበትም መልዕክት አስተላልፈዋል።
የቀድሞው የየስራይ ትምህርት ቤት ህብት ሰብሳቢ አቶ አየለ ተሰማ በበኩላቸው እንደገለፁት ትምህርት ቤቱ ረጅም ዘመናት ከማገልገሉ የተነሳ እርጅና ተጫጭኖት የሚገኝ መሆኑን ገልፀዋል።
በመሆኑም ይህንን ችግር ያስጨነቃቸው በት/ቤቱ የቀድሞ ተማሪውች ጥረት የተጀመረው የእድሳትና የማሻሻል ሀሳብ በመንግሥት እና በህብረተሰቡ ተቀባይነት አግኝቶ ልበ ቀና በሆኑ የቀድሞ ተማሪዎች የገንዘብ መዋጮና በአገና ከተማ አስተዳደር እገዛ የመጀመሪያው ዙር የእድሳት ስራ መጀመሩንም አቶ አየለ አብራርተዋል ።
የትምህርት ቤቱ እድሳትና ማሻሻያ ሶስት ዋና ዋና ክፍሎች ያሉት ነው ያሉት አቶ አየለ በቀጣይም ትምህርት ቤት ካለበት ችግር ለማላቀቅና ደረጃውን የጠበቀ ትምህርት ቤት እንዲሆን ሁሉም ማህበረሰብ ተሳትፎ ማድረግ እንዳለበት ጥሪ አድርገዋል።
የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር አቶ ተሾመ ፈቀደ የየስራይ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ1961 ዓ.ም የተመሠረተው ሲሆን በርካታ ለአካባቢው ብሎም ለሀገር እያገለገሉ የሚገኙ ምህራን ትውልድ ያፈራና በወረዳው ከሚገኙ አንጋፋ ትምህርት ቤቶች መካከል የሚጠቀስ እንደሆነም አስረድተዋል።
ትምህርት ቤቱ ከብዙ ታሪካዊ የስኬት ጉዞ በኋላ በቅርብ አመታት ለብዙ ችግሮች ተጋልጦ የበረ ስለሆነ አሁን በቀድሞ ተማሪዎች እየተደረገውን ያለ እንቅስቃሴ ከነበረበት ማነቆ የሚያወጣው በመሆኑ ስራው እንዲሳካ ትኩረት ሰጥቶት ይሰራልም ብለዋል ።
ከዚህ በተጨማሪ ትምህርት ፡ የእንስሳት ርባታ ስራ ፡ የፍራፍሬ ችግኞች የመትከልና ሌሎችም በተለያየ መልኩ ለማሳደግ ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ተሾመ በቀጣይም ትምህርት ቤቱ በብዙ መልኩ ተለውጦ ውጤታማ እንዲሆን የመስራቱ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላልም ብለዋል።

የአገና ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ የተለያዩ የቴክኖሎጂ ምርቶች አምርቶ ለሽያጭ ማቅረቡን አስታወቀ ።

===================

የአገና ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ የተለያዩ የቴክኖሎጂ ምቶች አምርቶ ለሽያጭ ማቅረቡን አስታወቀ ።
እንደሚታወቀው ኮሌጁ የማህበረሰብ ችግር ፈቺ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በማምረትና በማስተዋወቅ እንዲሁም በተግባር የሰለጠነ አምራች የሰው ሀይል በማፍራት እጅግ አኩሪ የሆኑ ተግባራቶች እየፈፀመ ይገኛል።
የአገና ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ በሚያከናወናቸው አዳዲስ ተግባራቶች ለተከታታይ አመታት በተለያዩ ዘርፎች ግንባር ቀደም ሆኖ በዞኑ ብሎም በክልሉ እውቅና እያገኘም ይገኛል ።
ለዚህም ትልቁ ስኬት በእውቀትና በቁርጠኝነት የተመራ የአመራር ስልትና ትጉህና እውቀቱን ለማሳደግ ዝግጁ የሆነ እንዲሁም ለማህበሩ ተቆርቋሪ ሰራተኛ ቅንጅታዊ አሰራር መኖሩን ተከትሎ መሆኑ በተለያየ ጊዜ በዘገብናቸው ዘገባዎች ላይ ለመገንዘብ ችለናል።
ኮሌጁ በቅርቡ በኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲሁም በአጫጭር ስልጠና ተግባራት ከአጠቃላይ የጉራጌ ዞን ኮሌጆች መካከል 1ኛ ደረጃ በመያዝ ተልዕኮውን በአግባቡ እየተወጣ እንደሚገኝ ተረጋግጧል ።
በአሁን ሰዓትም ኮሌጁ የተለያዩ የቴክኖሎጂ ውጤት የሆኑና ለአካባቢው ማህበረሰብ ጠቀሜታቸውን የጎላ የቴክኖሎጂ ውጤቶች አምርቶ ለሽያጭ አቅርቦአል ።
በኮሌጁ የአገና ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ጠቅላላ የምርቶ አገልግሎት ማምረቻና መስጫ የኢንተርፕራይዝ ማህበር ተመስርቶ ምርቱን የሚፈልጉ አካል መግዛት የሚችል ሲሆን ከተመረቱና ለሽያጭ ከቀረቡ ምርቶች መካከል :-
ተንቀሳቃሽ የዶሮ ቤት ፡ ተደራራቢ አልጋ ፡ የከተማ ቆሻሻ ማስወገጃ ጋሪ ፡ እህል መውቂያ ማሽን ፡ በሞተር ሀይል የሚንቀሳቀስ ማረሻና ስመር ማውጫ ማሽን ፡ ገብስ ማጨጃ እንዲሁም ደረቅ ቆሻሻ መጣያ ይገኙበታል ።
በአጠቃላይ በኮሌጁ እየተከናወኑ የሚገኙ እጅግ አበረታች ስራዎች ተጠናክሮ ይቀጥል እያልን ምርቶቹን የሚፈልግ ለተጨማሪ መረጃ :-
ይጎብኙ

የአገና ኮንስትራክሽንና ኢንደስትሪያል ኮሌጅ 1ኛ ደረጃ????????በመያዝ ተልዕኮውን በአግባቡ እየተወጣ እንደሚገኝ ተረጋግጧል።

================

የአገና ኮንስትራክሽንና ኢንደስትሪያል ኮሌጅ በኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲሁም በአጫጭር ስልጠና ተግባራት ከአጠቃላይ የጉራጌ ዞን ኮሌጆች መካከል ????1ኛ ደረጃ????????በመያዝ ተልዕኮውን በአግባቡ እየተወጣ እንደሚገኝ ተረጋግጧል።
ኮሌጃችን ለኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች በሚሰጠው የጥራትና ምርታማነት ማሻሻያ: የንግድ ስራ አመራርና የሙያ ክህሎት ማሻሻያ ስልጠናዎች አማካኝነት እየጨመረ ያለው የምርት ጥራት መጨመርና የበርካታ ተጓዳኝ ቢዝነሶች መስፋፋት ጥሩ ማሳያዎች ቢሆንም የግብርና ዘርፉን በተለይም በዶሮ እርባታ: በወተት ምርት: በንብ እርባታ….ወዘተ ማህበራት ከመደገፍ ጋር የተለያዩ ቴክኖሎጂዎች ተዘጋጅተው ለአብዢ ኢንተርፕራይዞች እየተሸጋገሩ ከመሆኑም በሻገር በልዩ ዕቅድ እየተመራ መሆኑ ተገልጿል።
ኮሌጁ ከዞኑ ቴክኒክና ሙያ ትም/ስልጠና መምሪያ: አገና ከተማና ከእዣ ወረዳ አስተዳደር ስር ከሚገኙ የዘርፉ አመራሮችና ባለሙያዎች: ከወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ እና ከወልቂጤ ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅ ጋር ባለው ጠንካራ የስራ ቅንጅት እየመጣ ያለውን ለውጥና በቀጣይ ከጥራት ጋር ተያይዞ መሰራት ስለሚገባቸው ጉዳዮች ከቦርድ አመራሮች ጋር በመገምገም አቅጣጫ ማስቀመጡና የተሻለ አፈጻጸም ያስመዘገቡ አሰልጣኞችና አስተዳደር ሰራተኞች ዕውቅና መስጠቱ ይታወሳል።
በመሆኑም የኮሌጃችን አሰልጣኞችና ማኔጅመንት አባላት እንኳን ደስ አላችሁ እያልን የተገኙ ውጤቶችና ተሞክሮዎችን በማስቀጠል የተጣለብንን ሀገራዊ ተልዕኮዎችን በጥራትና በፍጥነት በመፈጸም የኮሌጁ የማሰልጠን አቅም ወደ ደረጃ-5(ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅነት ደረጃ) በማሳደግ የህብረተሰባችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንደሚጠበቅብን በዚሁ አጋጣሚ እንገልጻለን????????
ዘገባው: የአገና ኮንስትራክሽንና ኢንደስትሪያል ኮሌጅ ነው::
website: https://www.agenacollege.edu.et

የብልጽግና ፓርቲ የማህበራዊ ድህረ-ገጽ

================

ግንቦት 27/2016ዓ.ም
የእዣ ወረዳ አመራሮች የብልጽግና ፓርቲ የማህበራዊ ድህረ-ገጽ የማሳደግ ዘመቻ በይፋ ተቀላቅለዋል።
ዘመቻው የብልጽግና ፓርቲ የማህበራዊ ሚዲያ ተከታዬች በማብዛት በፓርቲው የሚተላለፋ መረጃዎች ይበልጥ ለአባሉና ለህዝቡ ተደራሽ ለማድረግ ያለመ ነው።

የጉራጌ ብሔረሰብ አንድነትን የሚያጠናክሩ ልማቶች በማፋጠን ህብረተሰቡ ተጠቃሚ ለማድረግ ማህበሩ በትኩረት ሊሰራበት እንደሚገባ ክቡር ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው ገለጹ።

==================

ግንቦት21/2016ዓ.ም
================ የጉራጌ ብሔረሰብ አንድነትን የሚያጠናክሩ ልማቶች በማፋጠን ህብረተሰቡ ተጠቃሚ ለማድረግ ማህበሩ በትኩረት ሊሰራበት እንደሚገባ ክቡር ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው ገለጹ።
የጉራጌ ልማትና ባህል ማህበር ባካሄደው አመታዊ ጉባኤው የተለያዩ የቀጣይ አቅጣጫዎች በማስቀመጥ ተጠናቋል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ እንዳሻው ጣሰው በጉባኤው ማጠቃለያ በሰጡት የቀጣይ አቅጣጫ እንዳሉት ማህበሩ የጉራጌ ብሔረሰብ አንድነትን የሚያጠናክሩ ልማቶች በማፋጠን ማህበረሰቡ ተጠቃሚ ለማድረግ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች በማሳተፍ ተግባራዊ ማድረግ ይኖርበታል።
የጉራጌ ብሔረሰብ ባህላዊ እሴቶች፣ ቋንቋና ታሪክ በማልማት ሳይደበዝዝ ተጠብቆ ለተተኪው ትውልድ የማስተላለፍ ስራ ከመቼውም ጊዜ በላይ ትኩረት ተሰጥቶት ሊሰራበት ይገባል ብለዋል።
ማህበሩ ህልውናውን አስጠብቆ የተለያዩ ልማቶች በፍትሃዊነት እንዲሰራ የገቢ አቅሙ ማሳደግ እና ቴክኖሎጂ በመጠቀም አዳዲስ አሰራሮችን ተግባራዊ ማድረግ እንዳለበት ክቡር ርዕሰ መስተዳድሩ አሳስበዋል።
የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ በጉባኤው ላይ እንደገለጹት የጉራጌ ብሔረሰብ በሁለት አስተዳደር የሚመራ አንድ ህዝብ ነው።
ባለሀብቶች ለልማት ሁልጊዜ ገንዘብ ስጡ ከማለት ይልቅ ባለው የኢንቨስትመንት አማራጮችና ምቹ ሁኔታ ተጠቅመው ወደ አካባቢያቸው ገብተው እንዲያለሙ አቶ ላጫ ጥሪ አቅርበዋል።
በቀጣይ ማህበሩ የጀመራቸው የልማት ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ለአገልግሎት እንዲውሉ ለማድረግ የጉራጌ ተወላጆችና የልማት አጋሮች በማስተባበር ርብርብ እንደሚደረግ አስገንዝበዋል።
የምስራቅ ጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙስጠፋ ሀሰን በበኩላቸው የልማትና የባህል ማህበሩ ተቋማዊ አቅሙ በማሳደግ ህብረተሰቡ ተጠቃሚ የሚያደርጉ የልማት ስራዎች እንዲሰራ የተጀመረውን ሪፎርም የማድረግ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል።
ጉራጌ በሁለት የዞን አስተዳደር እንዲደራጅ ሲደረግ ማህበረሰቡ በልማትና በባህል አጠናክሮ በማስቀጠል የህዝቡ አንድነት ይበልጥ ለማጠናከር እንደሆነ አቶ ሙስጠፋ ገልጸዋል።
ጉልባማ ከዚህ ቀደም በልማት ላይ በሰራው ልክ በባህል ያልሰራ በመሆኑ በቀጣይ ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራ እንደሚገባ የገለፁት አቶ ሙስጠፋ ተወላጅ ባለሀብቶችም ወደ አካባቢያቸው ገብተው እንዲያለሙ ምቹ ሁኔታ የመፍጠር ስራ ተሰርቷል።
የጉራጌ ልማትና ባህል ማህበር ዋና ዳይሬክተር አቶ ቅባቱ ተሰማ ለጉባኤው ሪፓርት ሲያቀርቡ እንደገለጹት ማህበሩ ከረጂ ድርጀቶች በተገኘ የገንዘብ ድጋፍና በህብረተሰብ ተሳትፎ በሁለቱም ዞኖች በደቡብ ሶዶና በጉመር ወረዳዎች ት/ቤት፣ የጤና ኬላ፣ የንጹህ መጠጥ ውሃ ግንባታዎች በማካሄድ ማህበረሰቡ ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል።
የማህበሩ የቡታጅራ ሁለገብ ህንጻ ጂ+1 ወለልን በማጠናቀቅ ማከራየት የተቻለ ሲሆን የአዲስ አበባ የባህል ማዕከል ህንጻ አንደኛው ክንፍ ለማጠናቀቅ ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝ ዋና ዳይሬክተሩ አብራርተዋል።
የጉራጌ ብሄረሰብ ባህላዊ የዳኝነት ስርዓት ሰነዶችን በጽሑፍ መሰነድ፣ የጉራጊኛ ቋንቋ የትምህርትና የስራ ቋንቋ እንዲሆን የፊደል ገበታና ቃላት ማደራጀት እንዲሁም የጉራጊኛ ቋንቋ በአንደኛ ክፍል ደረጃ እንዲጀመር ከዞኑ አስተዳደርና ከወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመስራት የሙያና የቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉን አቶ ቅባቱ ተሰማ ተናግረዋል።
የጉባኤው ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት ሁሉም የጉራጌ ተወላጆች የማህበሩ አባል በማድረግ የውስጥ ገቢ አቅም ማጠናከር ይገባል ብለዋል።
የጉራጌ ተወላጅ ምሁራኖች የማህበረሰቡ ችግር ፈቺ የሆኑ ጥናቶች በማጥናት ባለሀብቶችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳታፊ የሚሆኑበት የምክክር መድረክ በማዘጋጀት ወደ ተግባር በመቀየር ማህበረሰቡ ተጠቃሚ እንዲሆን በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

ባለሀብቶች በኢንቨስትመንት ዘርፍ በመሰማራት እያደረጉት ያለዉ በጎ እንቅስቃሴ አጠናክረዉ መቀጠል እንዳለባቸዉ የጉራጌ ዞን ኢንቨስትመንትና ኢንዲስትሪ መምሪያ አስታወቀ፡፡

=========================

ባለሀብቶች በኢንቨስትመንት ዘርፍ በመሰማራት እያደረጉት ያለዉ በጎ እንቅስቃሴ አጠናክረዉ መቀጠል እንዳለባቸዉ የጉራጌ ዞን ኢንቨስትመንትና ኢንዲስትሪ መምሪያ አስታወቀ፡፡
በጉራጌ ዞን እዣ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ያለበት ደረጃ ጉብኝት ተካሂዷል ።
የጉራጌ ዞኑ ኢንቨስትመንት መምሪያ ሀላፊ አቶ ናስር ሀሰን እንደገለፁት የአካባቢ ተወላጅ እና ሌሎችም ባለሀብቶች በዞኑ ላይ ያለዉን የመሬት አማራጮችን ተጠቅመዉ በተለያዩ ዘርፎች ኢንቨስት በማድረግ ተጠቃሚነታቸዉ በተጨባጭ ማረጋገጥ እየቻሉ ነው ብለዋል ።
የመስክ ምልከታው አላማ በወረዳው በኢንቨስትመንት የተሰማሩ ባለሀብቶች የስራ እንቅስቃሴያቸው ያለበት ደረጃ ተዟዙረው በመመልከት የተሻሉ ስራዎች ለማስቀጠልና ወደ ስራ ያልገቡ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ወደ ስራ እንዲገቡ ለማስቻል እንደሆነም ሀላፊው አመላክተዋል ።
በዞኑ በኢንዱስትሪና በግብርና ዘርፍ ፍቃድ ወስደው ወደ ተግባር ያልገቡ 25 ፕሮጀክቶችን ውል በማቋረጥ 359 ሄክታር ወደ መሬት ባንክ ማስገባታቸው የተናገሩት ኃላፊው ወደ መሬት ባንክ ከገባው ውስጥ ለአልሚ ባለሀብት በማስተላለፍ ወደ ተግባር መገባቱንም አቶ ናስር አስረድተዋል ።
በተለያዩ ዘርፎች መሬት ተረክበዉ ያላለሙ ባለሀብቶች በፍጥነት ወደስራ መግባት እንዳለባቸዉ ያሳሰቡት አቶ ናስር ያላለሙትንም በየደረጃው እየተወሰደ ያለውን የእርምት ርምጅ ተጠጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል ።
የእዣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘውዱ ዱላ በበኩላቸው እንዳሉት ኢንቨስትመንት የሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊ እድገትን በማፋጠንና የዜጎችን የስራ ዕድል በመፍጠር ፣ የቴክኖሎጂ ሽግግርና በተለያዩ መልኩ የሚያደርጉት አስተዋፅኦ ከፍተኛ ነው ብለዋል።
በወረዳው በኢንቨስትመንቱ ዘርፍ በተደረጉ ምች ሁኔታዎች በርካታ ባለሀብቶች በተለያየ ዘርፈ በመሰማት ውጤታማ ስራ እየሰሩ ይገኛሉ ያሉት አቶ ዘውዱ ከእነዚህም መካከል በአበባ እርሻ ልማት ፣ በዉሃ ማሸግ ፡ በችቡድ ፋብሪካ ፡ በሆልቲ ከልቸር ፡ ብረት ብረትና ፕላስቲክ ማምረቻ ፋብሪካዎች ተጠቃሾች ናቸው ብለዋል።
እንደወረዳው 63 ኢንቨስትመንቶች ፈቃድ ወስደው የሚገኙ ሲሆን ከነዚህም መካከል 12 የሚሆኑትን ለረጅም ጊዜ አጥር አጥረው በማስቀመጥና ባለማልማት ውላቸው መቋረጡንም ገልፀዋል።
በቀጣይም መሬት ወስደዉ በሙሉ አቅማቸዉ ወደ ስራ ያልገቡ ባለ ሀብቶች በአፋጣኝ ማልማት እንዳለባቸዉና የማያለሙ ከሆነ መንግስት ተገቢዉን እርምጃ ተጠናክሮ የሚቀጥል እንደሆነም ገልፀዋል።
በኢንቨስትመንቱ ዘርፍ የተሰማሩ ባለሀብቶች በሰጡት አስተያየትም እንደዚህ መሰል ምልከታዎች ጉለቶቻቸውን እንዲቀርፉ ሰፊ እድል የሚፈጥር በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጥል እንዳለበት ተናግረው ሆኖም የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች በሙሉ አቅማቸው እንዲያመርቱ ለማስቻል ያሚያጋጥማቸው በተለይም የመብራት የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች የሚመለከታቸው አካላት ተቀናጅተው ሊሰሩ ይገባናል ብለዋል።
በጉብኝቱ በወረዳው የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴዎች እየተጎበኙ ሲሆን የማጠቃላይ የውይይት መድረክ በወልቂጤ ከተ ማ የጆካ ሆቴል መሰብሰቢያ አዳራሽ ላይ ተካሂዷል።
በእለቱም የጉራጌ ዞን ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ መምሪያ ፡ የእዣ ወረዳ ኢንቨስትመንት ኮሚቴ አመራሮች እንዲሁም በወረዳው በኢንቨስትመንት የተሰማሩ ባለሀብቶች ተሳታፊ ሆነዋል ሲል የዘገበው የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው።

“ጽዱ ኢትዮጵያን እንፍጠር” ንቅናቄ ቀድሞ ማሳካት እንደተቻለ የዞኑ ጤና መምሪያ አስታወቀ፡፡

================================

ግንቦት12/2016ዓ.ም
================ በጉራጌ ዞን “ጽዱ ጎዳና ኑሮ በጤና” በሚል መሪ ሀሳብ ህብረተሰቡ የአካባቢውን ንጽህና እንዲጠብቅ የተጠናከረ ስራ በመሰራቱ በሀገሪቱ የተጀመረውን “ጽዱ ኢትዮጵያን እንፍጠር” ንቅናቄ ቀድሞ ማሳካት እንደተቻለ የዞኑ ጤና መምሪያ አስታወቀ፡፡
በዞኑ እዣ ወረዳ በቆጠር ገድራ ቀበሌ ሙዳ መንደር እና በቸሃ ወረዳ አዘር ቀበሌ ቆረሚያ ሁለት መንደር ከአይነ-ምድር ነፃ መሆናቸውን በማረጋገጥ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በይፋ ተመርቀዋል፡፡
የጉራጌ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ አየለ ፈቀደ በፕሮግራሙ ላይ እንዳሉት የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር ዓብይ አህመድ ያስጀመሩት ጽዱ ኢትዮጵያ እንፍጠር ንቅናቄ የዞኑ አመራሮችና የጤናው ሴክተር ባለሙያዎች በመቀላቀል በርካታ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ፡፡
ዞኑ ቀደም ብሎ “ጽዱ ጎዳና ኑሮ በጤና” በሚል መሪ ሀሳብ ህብረተሰቡ የአካባቢውንና የግሉ ንጽህና እንዲጠብቅ ግንዛቤ የመፍጠር ስራ ሲሰራ በመቆየቱ ጽዱ መንደር፣ ቀበሌ፣ ወረዳና ዞን ለመፍጠር የተቀመጠውን ግብ ለማሳካት በጥሩ ሁኔታ እየሄደ መሆኑን ኃላፊው ተናግረዋል፡፡
በዚህም በዞኑ እዣ ወረዳ በቆጠር ገድራ ቀበሌ ሙዳ መንደር እና በቸሃ ወረዳ አዘር ቀበሌ ቆረሚያ ሁለት መንደር ነዋሪዎች የተሻሻሉ መጸዳጃ ቤቶች እየተጠቀሙ መሆናቸወንና አካባቢዎቹ ከአይነ-ምድር ነፃ መሆናቸውን በማረጋገጥ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በይፋ መመረቃቸውን ለተግባሩ መሳካት ማሳያ መሆኑን አቶ አየለ ገልጸዋል፡፡
ንጽህናው የሚጠብቅ ሰው ከሚያገኘው ማህበራዊና ኢኮሚያዊ ፋይዳው በተጨማሪ በማህበረሰቡም ዘንድ ከበሬታን እንደሚያገኝ የገለጹት አቶ አየለ ይህንንም ይበልጥ ውጤታ ለማድረግ በዞኑ አብዛኛው ማህበረሰብ የተሻሻሉ መጸዳጃ ቤቶች ተጠቃሚ ቢሆኑም ሁሉም ተጠቃሚ እንዲሆኑ የማድረግ ስራ በትኩረት ይሰራል፡፡
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ከልል ጤና ቢሮ የበሽታ መከላከልና የጤና ማጎልበት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ፍሰሃ ለዕመንጎ በፕሮግራሙ ላይ እንደገለጹት ጽዱ መንደር፣ ቀበሌ፣ ወረዳ፣ ዞንና ክልል መፍጠር ጽዱ ሀገር በመፍጠር ሀገርን ማስከበር ነው፡፡
ጠቅላይ ሚኒስቴር ደ/ር አብይ አህመድ ጽዱ ኢትዮጵያ መፍጠር የሚል ንቅናቄ ከማወጃቸው በፊት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በአንዳንድ ወረዳዎች ጽዱ ኢትዮጵያ ለመፍጠር ከፍተኛ የንቅናቄ ስራ መስራት በርካታ ከአይነ ምድር ነጻ መንደሮች፣ ቀበሌዎችና ወረዳዎች መፍጠር መቻሉን አብራርተዋል፡፡
ዛሬ ከአይነ-ምድር ነጻ በመሆናቸውን ተረጋግጠው በይፋ የተመረቁ በእዣና በቸሃ ወረዳዎች ውስጥ የሚገኙ መንደሮች መረጃ እንደሚያሳየው ህብረተሰቡ ሙሉ በሙሉ መጸዳጃ ቤት የሚጠቀም ቢሆንም በተወሰነ ደረጃ የተሻሻሉ መጸዳጃ ቤት የማይጠቀሙ ማህበረሰቦች ተጠቃሚ እንዲሆኑ በትኩረት ሊሰራበት እንደሚገባ አቶ ፍሰሃ ተናግረዋል፡፡
ወ/ሪት ቃልኪዳን አሳልፍና ወ/ሮ ትግሉ ሰፋ የእዣና የቸሃ ወረዳዎች ጤና ኤክስቴሽን ባለሙያዎች ናቸው፡፡ ሁለቱም በሰጡት አስተያየት ህብረተሰቡ የሴቶች የልማት ህብረት፣ እድሮች፣ ተዋቂ ግለሰቦችና የሃይማኖት አባቶች ተጠቅመው ግንዛቤ የመፍጠር ስራ በሰፊው በመስራታቸው ህብረተሰቡም በጥሩ ሁኔታ ተቀብሎ የግሉና የአካባቢው ንጽህና መጠበቅ እንዲሁም የተሻሻሉ መጸዳጃ ቤቶች በመጠቀም ከአይነ ምድር ነጻ በማድረግ ማስመረቅ መቻላቸውን ተናግረዋል፡፡
በመሆኑም ህብረተሰቡ ከውሃ ወለድና ከተላላፊ በሽታዎች ተጠቂነት በመከላከል ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን ማረጋገጥ መቻላቸውን አብራርተዋል፡፡

ስፖርት

===================================

በትላንትናዉ እለት በተደረገው የጤና ስፖርት ውድድር ወልቂጤ ከተማ ጤና ቡድን እዣ ወረዳ ጤና ቡድንን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፎል ።
የእዣ ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ፅ/ቤት የስፖርት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ክንፈ ክፍሌ እንደገለፁት የጤና ስፖርት ውድድር በማስፋፋት ጤናማና አምራች ማህበረሰብ ከመፍጠርም ባሻገር የእረስ በእርሱ ግንኙነት በማጠናከር ሚናው የጎላ ነው ።
ስፖርት ለጤና ለሰላም ለፍቅር ለእርስ በርስ ግንኙነት ለአንድነት ያለው ጠቀሜታ ከፍተኛ መሆኑን በመረዳት ሁሉም ማህበረሰብ የስፖርት እንቅስቃሴዎች በማድረግና ስፖርትን በመደግፍ የድርሻውን መወጣት እንዳለበት ሀላፊው ጨምረው ገልፀዋል ።
በትላንትናዉ እለት  በተደረገው የጤና ስፖርት ውድድር ወልቂጤ ከተማ ጤና ቡድን እዣ ወረዳ ጤና ቡድንን አቻውን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፎል ሲል የዘገበው የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው።