













የቶቶት የወጣቶች ማህበር ስራ አስፈፃሚ ህዳር 15/2017ዓ.ም 6ኛ ዙር ዓመታዊው የሀገርህን እወቅ ጉዞ አስመልክቶ የሚከተሉት ውሳኔዎች አሳልፏል፤
ዓመታዊው የቶቶት የሀገርህን እወቅ ጉዞ ይዘቶች ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጎ የጋራ መግባባት ተደርሶበታል። በዋናነት በጉራጌ አካባቢ የሚገኙ ሰው ሰራሽ እና ተፈጥሯዊ ቅርሶች፣ባህሎችና አጠቃላይ የጉራጌ ማህበረሰብ አኗኗር ባህልና እሴት ለማስተዋወቅ እንዲሁም የአካባቢው የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ለማነቃቃትን አላማው አድርጎ የሚካሄድ መሆኑ የታወቀ ነው።
ማህበሩ ባለፋት ስድስት ( 6) ዓመታት አምስት ጉዞዎችን ማድረጉ ይታወቃል።
የመጀመሪያ ጉዞ በ2012ዓ.ም የጢያ አለማቀፍ ቅርሶች(መካነ መቃብር)፣በ2013ዓ.ም የጊቤ ብሔራዊ ፓርክ፣በ2014 አረቅጥ ሀይቅ(ጉዞ አጋዝ ዳርሳሞ)፣በ2015ዓ.ም እዣ ወረዳ ውስጥ የሚገኘው የቆጠር ገድራ ጥብቅ ደን (ጉዞ ደስታ ጣድየ) እና በ2016ዓ.ም ቸሀ ወረዳ የሚገኘው (የጆካ ባህላዊ ዳኝነት ስርአትና የጠናቃ ጀፎረ) እንዲሁም በቸሀና ጎማረ ወረዳ ውስጥ የሚገኘው የወገፐቻ ጥብቅ ደን (ጉዞ ኧጅ ዮካ ) አካሂዷል።
በተጨማሪም በ2013ዓ.ም በጊቤ ብሔራዊ ፓርክና በ2014 ዓ.ም በሞህር አክሊል ወረዳ ቆረር ቀበሌ(ጉዞ የቃቄ ወርድወት) የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር በማድረግ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሂዷል።
የዘንድሮው የቶቶት የ6ኛ ዙር የሀገርህን እወቅ ጉዞ የካቲት 8 እና 9 /2017 ዓ.ም ( ቅዳሜና እሁድ ) ወደ ታሪካዊው በጉራጌ ዞን ጔታ ወረዳ የሚገኘው የዛራ ጥብቅ ደን እንዲሆን የተወሰነ ሲሆን ከወዲሁ ፕሮግራምዎን በማስተካከል በዚህ ጉዞ እንዲሳተፉ ሲል ቶቶት የወጣቶች ማህበር ለማህበራችን አባላቶች ፣ ለጉራጌ ተወላጆች እና ለሁሉም ኢትዮጵያዊ በጉዞ ላይ እንዲሳተፍ ጥሪ እያቀረበ ጉዞውን የተመለከቱ ዝርዝር ማብራሪያዎችን በቅርብ የሚገልጽ ይሆናል።
“ቶቶት” ለተሻለ ነገ







