የእዣ ወረዳ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት

የጉራጌ ብሄረሰብ መገለጫ የሆኑ የጉራጊኛ ቋንቋ : የባህል እሴቶችና ሀገር በቀል እውቀቶችን ለትውልድ እንዲተላለፉ መላው ማህበረሰብ ሀላፊነቱ ሊወጣ እንደሚገባ በጉራጌ ዞን የእዣ ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ፅ/ቤት ገለፀ ።

*==============================*

የጉራጌ ብሄረሰብ መገለጫ የሆኑ የጉራጊኛ ቋንቋ : የባህል እሴቶችና ሀገር በቀል እውቀቶችን ለትውልድ እንዲተላለፉ መላው ማህበረሰብ ሀላፊነቱ ሊወጣ እንደሚገባ በጉራጌ ዞን የእዣ ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ፅ/ቤት ገለፀ ።
ፅ/ቤቱ በቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት እና በጉራጌ ብሄረሰብ ባህል ፡ ቋንቋና ሌሎችም እሴቶች ማጠናከር ላይ ትኩረት ያደረገ ለባለድርሻ አካላት ሰጥቷል ።
በእለቱም የእዣ ወረዳ አስተዳደር ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ይርጋለም ብዛ እንደገለፁት አንድ ቋንቋ ወይንም ባህል ሊያድግና ለቀጣይ ትውልድ ሊሸጋገር የሚችለው የዚህ ማህበረሰብ ውስጥ የሚገኝ የህብረተሰብ ክፍል በተለያዩ ማህበራዊ ጉዳዮች ወቅት ቋንቋውን ወይንም ባህሉን እራሱ ተናግሮ ለሌሌች ማስተዋወቅ ሲችል ነው ።
ለዚህም ስኬታማነት በዚህ ስልጠና የተሳተፉት ታዋቂ ሽማግሌዎች ፡ ተጠሪ መምህራንና ርዕሰ መምህራን የጉራጌ ብሄረሰብ መገለጫ የሆኑትን አኩሪ እሴቶች እንዲተዋወቁና ለትውልድ ተሻጋሪ እንዲሆኑ የድርሻቸው መወጣት እንዳለባቸውም አቶ ይርጋለም አስገንዝበዋል ።
ሌላው በወረዳችን ብሎም በሀገራችን ተስፋፍቶ የሚገኘው ድህነትና ስራአጥነት ለማስወገድ ከሚቻልባቸው ዋና ዋና መንገዶች አንዱ የሆነው የቱሪዝም ኢንዱስትሪ ልማት እንዲስፋፋ ማድረግ ተጠቃሽ ነው ያሉት አቶ ይርጋለም ህብረተሰቡ ከዚህ ዘርፍ ከኢኮኖሚ ተጠቃሚ እንዲሆን ማድረግ የሚቻለው ለቱሪስቱ ደረጃቸው የጠበቁ የመስተንግዶ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ባለቤቶች ሀላፊነት መወጣት እንደሚኖርባቸውም መልዕክት አስተላልፈዋል ።
የእዣ ወረዳ ባህል ቱሪዝም ፅ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ የሺተካ እንደገለፁት የጉራጊኛ ቋንቋ ብሎም ሌሎች እሴቶቻችን በትውልዱ የተሻለ ደረጃ ለጥቅም እንዲውሉ ከፍተኛ ሚና መጫወት ከሚችሉ ተቋማት አንዱ ትምህርት ቤቶች ተጠቃሾች መሆናቸው ገልፀው ለዚህም ክበባቶች በማጠናከርና የጉራጊኛ የቋንቋ ቀን በየሳምንቱ በማወጅ ተማሪዎች በዚህ ቋንቋ ብቻ የሚግባቡት ሂደቱ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ።
እነዚህ የብሄረሰቡ መገለጫ የሆኑት የባህል እሴቶችና ሀገር በቀል እውቀቶች ተጠቅሞ ለትውልድ እንዲተላለፉ ሁሉም ሀላፊነቱ መወጣት እንደሚገባ የገለፁት ወ/ሮ የሺ በተለይም ቀድሞ ማህበረሰቡ ሲጠቀምባቸው የቆዩ ውብና ቀልብ ሳቢ የነበሩትን የሰርግ ስነ-ስርዓት ፡ የቤት አሰራር ፡ የጀፎሮ አጠባበቅ ፡ ባህላዊ የዳኝነት ስነ-ስርዓትና ሀገር በቀል እውቀቶችን በመጠበቅና ለትውልድ እንዲተላወፉ ሁሉም የድርሻው ሊወጣ ይገባልም ብለዋል ።
ከዚህ በተጨማሪ እንደ ወረዳው የሚገኙ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር የጥራት ደረጃቸውና የአገልግሎት አሰጣጣቸው ለማሻሻል የድጋፍና ክትትል ስራ እየተሰራ ያለው ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ወ/የሺ ተካ ገልፀዋል ።
በፅ/ቤቱ የቱ/አ/ሰ/ተ/ ዋና ስራ ሂደት አስተባባሪ የሆኑት አቶ አብረሃም መላኩ የስልጠናው ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን የጉራጌ ብሄረሰብ መገለጫ የሆኑትን የተለያዩ አኩሪ እሴቶች እንዲተዋወቁ እንዲጠቅሙና ከትውልድ ወደ ትውልድ እዲሸጋገሩ ፅ/ቤቱ የድርሻውን እየተወጣ ቢሆንም አሁን ከዞን ጀምሮ በተደራጀና በተጠናከረ መልኩ የብሄረሰቡ እሴቶች ወደሚፈለጉበት ደረጃ እንዲደርሱ ከማድረግ አንፃር ቀሪ ስራዎች ይጠይቃል ብለዋል ።
የቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ማሟላት ከሚገባቸው ጉዳዮች መካከል የህንፃው ስነ-ውበት ማራኪና ሳቢ መሆኑን ፡ የተሟላ የንፅህናና የመፀዳጃ ቤቶች እንዲኖር ማድረግ ፡ የሰራተኛች አለባበስና ሥነ ምግባር እንዲኖራቸው ማድረግ የመግቢያ ቦታዎች ምቹና ንፅህናቸው የጠበቁ መሆን እንዳለባቸውንና የመሳሰሉት ተጠቃሾች መሆናቸውንም በሰነዱ አመላክተዋል ።
ተሳታፊዎቹም በሰጡት አስተያየትም ፅ/ቤቱ እነዚህን እሴቶች እንዲጠናከሩ እያደረገውን ያለው ስራ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትና የቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የአገልግሎ አሰጣጥ ደረጃው ለማሻሻል ከስልጠናው ብዙ ግንዛቤ ያገኙ በመሆኑ በቀጣይ የድርሻቸውን እንደሚወጡም ተናግረዋል።
በስልጠናው መጨረሻም ግንባር ቀደም የቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የማበረታቻ ሰርተፊኬት ተሰጥቷቸዋል ሲል የዘገበው የወረዳው መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው።