የሸዋል ኢድ በዓል በዓለም ቅርስነት ተመዘገበ‼️

የሸዋል ኢድ በዓል በዓለም ቅርስነት ተመዘገበ‼️

የሸዋል ኢድ በዓል አከባበር በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና ባህል ተቋም (ዩኔስኮ) በማይዳሰስ ቅርስነት ተመዝግቧል።

በዚህም የሸዋል ኢድ በዓል ሀገራችን በማይዳሰስ ቅርስነት በዩኔስኮ የተመዘገበ 5ኛ ቅርስ ያደርገዋል።

ኢትዮጵያ ካሏት ደማቅ ማህበራዊ እሴቶች ውስጥ አንዱ የሸዋል ኢድ በዓል አከባበር የአለም ቅርስ ሆኖ መመዝገቡ የቱሪስት ፍሰቱ እንዲጨምር ከማድረጉም ባለፈ የሀገር መልካም ገፅታ በመገንባት ረገድ ፋይዳው የላቀ መሆኑን የሐረሪ ክልል ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል።

የሸዋል ኢድ በዓለም ቅርስነት መመዝገቡ የክልሉን የቱሪዝም ማዕከልነት የሚያሳድገው ከመሆኑ ተጨማሪ የህዝብን ተጠቃሚነት ከማሳደግ አንፃር ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተጠቁሟል።

#በውብ_እጆች_የተሰሩ_የዕደ_ጥበብ_ውጤቶች

===================================================================

#በውብ_እጆች_የተሰሩ_የዕደ_ጥበብ_ውጤቶች
➳➳➳➳➳➳➳➳➳➳➳➳➳➳➳➳➳
የጉራጌ ማህበረሰብ የሠው ልጅ ተፈጥሮን ለእርሱ በሚመቸው አይነት መልኩ መግራት ከጀመረበት ዘመን አንስቶ ተፈጥሮ የቸረችውን ከአካባቢው የሚገኙ ግብዓቶችን በመጠቀም ለየዕለት ህይወቱ አስፈላጊ የሆኑትን ቁሶች ከማምረት ባሻገር ለረዥም ጊዜ አገልግሎት ሊሰጡ የሚችሉ መገልገያዎችን ጭምር በመስራት ዕውቀቱን ለትውልድ አሸጋግሯል፡፡ እያሸጋገረም ይገኛል፡፡
ከእነዚህ የጉራጌ መለያ ናቸው የሚባሉት የዕደ-ጥበብ ውጤቶች መካከል ጥቂቶቹን ለአብነት እንኳ ብንጠቅስ እንደ የብረት፣ የሸክላ፣ የእንጨት፣ የቀንድ፣ የሽመና፣ የቆዳ፣ የቃጫ፣ የስንደዶ እና የቄጠማ ስራዎች እናገኛለን፡፡
የማኅበረሰቡ ዕውቀትና ክህሎት አሻራ በእነዚህ የዕደ-ጥበብ ዘርፎች አርፎባቸዋል፡፡ ዛሬ ዛሬ በጉራጌ ዞን በሚገኙት አንዳንድ ወረዳዎች ከስንደዶ፣ ከአክርማ፣ ከቃጫና ክር የሚመረቱ የዕደ-ጥበብ ውጤቶች ከአካባቢውና ከአገር አልፈው ከባህር ማዶም ባሉት ገበያዎች ላይ ተፈላጊነታቸው እየጨመረ መጥቷል፡፡
ከነዚህ ውብ የእደ ጥበብ ውጤቶች መካከል ጥቂቶቹ፡-
1. #ይወደረ
በእንሰት አብቃይነቱ የሚታወቀው የጉራጌ ብሔር እንሰትን ከምግብነት በተጨማሪ ለተለያዩ ግልጋሎቶች ይጠቀሙበታል፡፡ ከነዚህም ለምግብ ማዘጋጃነትና ማቅረቢያነት፣ ለመኝታና ለቤት ውስጥ ንጣፍነት ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ይወደረ ለምግብ ማቅረቢያነት የሚያገለግል ሲሆን የሚሰራውም የእንሰት ውጤት በሆነው በቃጫ ነው፡፡ ይህም ውበት እንዲኖረው በተለያየ ቀለማት ይነከራል፡፡ አንድ ጥሩ የተባለ ይወደረ ሰርቶ ለማውጣት እስከ አንድ ወር ጊዜ
የሚፈጅ ሲሆን እንዲህ አይነቱ ይወደረ ቁመቱ ሁለት ሜትር፣ ጎኑ[ስፋቱ] ደግሞ አንድ ሜትር ያህል ይሆናል፡፡
ይወደረ በተለይ ትላልቅ ክብረ-በዓላትና ትላልቅ ዝግጅቶች ሲኖሩ ቤት ውስጥ ወለል ላይ በተነጠፈ ሰፊና ምርጥ ጅፐ [ጅባ] ላይ ይዘረጋና ቆጮ፣ ክትፎ፣ አይብና የጎመን ክትፎ በጣባ ወይም በጥለስ [ከእንሰት ቅጠል የተሰራ ለመመገቢያነት የሚያገለግል] እንዲበላበት ለታዳሚው ይዘረጋል፡፡ በተለይ በመስቀል ወይም በአረፋ ክብረ በአላት ጊዜ ይወደረ እንዳይቆሽሽ ተጠቅልሎ በንጽህና ከተቀመጠበት ቦታ ይወጣና እስከ በዓላቱ ፍፃሜ ድረስ
ጅፐ ላይ ተዘርግቶ ማዕድ ማቅረቢያ ሆኖ ሲያገለግል ይቆያል፡፡
2. #ጅፐ [ጅባ]
ሌላው ከእንሰት ተክል እና ከቄጠማ የሚሰራው የዕደ-ጥበብ ውጤት ጅፐ [ጅባ] ይባላል፡፡
ይህ የዕደ-ጥበብ ውጤት ከእንሰት ተክል ከሚገኘው ቃጫና ኮባ የሚሰራ ሲሆን ለቤት ውስጥ ወለል ንጣፍነትና ለመኝታ አገልግሎት ይውላል፡፡
የተለያየ መጠንና ጥራት ያላቸው የጅፐ አይነቶች ሲኖሩ በጣም ምርጥ የተባሉት ልክ እንደ ይወደረ ለተለያዩ ክብረ-በዓላትና ለትላልቅ ዝግጅቶች ብቻ ግልጋሎት
የሚሰጡ ናቸው፡፡
መሃከለኛ የሆኑት ደግሞ ዘወትር ተነጥፈው በህዝቡ የዕለት ተዕለት ህይወት ውስጥ ጥቅም ላይ ይውላሉ፡፡
3. #ሰፍ [መሶብ]
ሰፍ [መሶብ] ከስንደዶና ከአክርማ የሚሰራ ሲሆን በጉራጌ ብሔረሰብ ዘንድ የተለያየ ቅርፅና መጠን ያላቸው ሰፍ [መሶብ] እየተሰሩ ለተለያዩ የማዕድ አገልግሎቶች ሲውሉ ይስተዋላሉ፡፡
እነዚህ በልዩ ልዩ ህብረ-ቀለማት ያጌጡ ውብና ማራኪ የዕደ-ጥበብ ውጤቶች ከቡና ቁርስ ማቅረቢያነት እስከ እንጀራና ዳቦ ማስቀመጫነት ሲያገለግሉ ትላልቅ
ሆቴሎችና ሬስቶራንቶችም በዋናነት ይጠቀሙባቸዋል፡፡
ልዩ ልዩ የሸክላ ምርቶች በጉራጌ እጅግ መጠነ ሰፊ ግልጋሎት የሚሰጡ የሸክላ ስራ ውጤቶች ይሰራሉ፡፡
እነዚህ የዕደ-ጥበብ ውጤቶች ለምግብ ማብሰያነትና ማቅረቢያነት፣ ለመጠጫነት፣ እንዲሁም የሚበሉና የሚጠጡ ምግቦችና መጠጦችን ሳይበላሹ ለረዥም ጊዜ ማቆያነት [ማስቀመጫነት] የሚጠቀሙበት ሲሆን አንዳንዶቹም
ከአንድ በላይ ለሆነ ጠቀሜታ ይውላሉ፡፡
እንደ ጀበና፣ የክትፎ አይብ ማቅረቢያና ማዋሃጃ ጣባ፣ ቅቤ ወይም ማር ወይም ወተት ማስቀመጫ፣ ጥዋ፣ የሸክላ ድስት፣ እንስራና ጋን ታዋቂ የብሔሩ የዕደ-
ጥበብ ውጤቶች ናቸው፡፡
4. #አንቀፎ [ማንኪያ]
ጉራጌ ከከብት ቀንድ የተለያዩ የቤት ቁሳቁሶችን ይሰራል፡፡ ከነዚህም ውስጥ አንዱና ዋንኛው አንቀፎ [ማንኪያ] ነው፡፡
አንቀፎ የተለያየ መጠን ያለው ሲሆን አነስተኛው ለክትፎ፣ ለአይብ፣ ለዝማሙጃት፣ ለኸቋት፣ ለፍንታፍንቶ፣ ለኦዛት፣ ለድኩቸ እና ለማር ወለላ መመገቢያነት ሲያገለግል ትልቁ ደግሞ በትልቅ ጣባት ክትፎ፣ አይብ፣ ዝማሙጃት እና የጎመን ክትፎ ከቅቤና ሚጥሚጣ ጋር ለመለወስና ለማቀላቀል
ይጠቀሙበታል።

Visit Gurage

ገጣሚ ና መምህር ክፍሌ ተመስገን

=====================

ገጣሚ ና መምህር ክፍሌ ተመስገን
ጦቢያ ላይ ባልተለመደ መልኩ “ኬረዢ” የሚል ጉራግኛ ግጥም በማቅረብ እጅግ ከፍ ያለ አድናቆትን አትርፏል
# “ቡርሳዊ” በሚል ድንቅ ትረካም ይታወቃል
#በተጨማሪም እልል በር ጉራጌ የግጥም መድብል በቪሲዲ
#መርኸቱ መጽሐፍ
#ቅን የደፍ ግየ በቪሲዲ ከሰራቸው ስራዎች ጥቂቶቹ ናቸው።
ክፍሌ በባህሪም እጅግ ጥሩ ስብእናም ያለው ወንድማችን ነው
በቅርቡም “ኬረዢ”የሚል አዲስ መፅሀፍ ለአንባቢያን ለማቅረብ በእንቅስቃሴ ላይ ነው
ሶሬሳ ወንድማችንን በርታ እንበለው

” ውሳቻ “

=================

” ውሳቻ ”
የጉራጌ ማህበረሰብ እንደሌሎቹ የሀገራችን ብሄረሰቦች የራሱ የሆኑ የተለያዩ ባህላዊ እሴት ባለቤት ነው፡፡

እነዚህ ባህለዊ እሴቶች የሚከወኑት በማህበረሰቡ የእለት ተእለት እንቅስቃሴ ሲከወኑ ይስተዋላል ከነዚህ የእርስ በርስ የመደጋገፍና የመረዳዳት ባህልን ከሚያዳብሩ ባህላዊ እሴት አንዱ ውሳቻ ተጠቃሽ ነው::

ውሳቻ የቃሉ ቀጥተኛ ትርጉም የእንሰት አዝመራ ወይም የእንሰት ምርቶች የሚሰበሰብበት ወቅት ሲሆን የጉራጌ እናቶች በየአካባቢያቸው አንድ ላይ ሆነው
እንሰት የሚፍቁበት የደቦ ስርአት “ውሳቻ” ተብሎ ይጠራል፡፡

ውሳቻ የሚጀምረው በብሄረሰቡ የዘመን አቆጣጠር መሸ ወይም ጥቅምት አጋማሽ ጀምሮ እስከ ታህሳስ መጨረሻ ድረስ ባለው ነው፡፡

ይህ ሲባል ሁሉም አካባቢ በተመሳሳይ ወቅት ይጀምራል ለማለት አያስችልም ለምሳሌ የደጋው አካባቢ ከወይና ደጋ አካባቢዎች አስቀድመው እንደ ሚጀምሩ የማህበረሰቡ እናቶች ያሰረዳሉ ።

ውሳቻ ከሌሎች ለየት የሚያደረገው አቅም የሌላቸው እናቶች መስራት አትችሉም ተብለው ማግለል ሳይሆን የቻሉትን ያህል ተሳታፊ ሆነው የእንሰት ምርታቸውን መሰብሰብ መቻላቸውና አቅመ ደካሞችን የነፃ ጉልበት እርዳታ ማድረጋቸው ውሳቻን ልዩ ያደርገዋል።

እንዲሁም በአካባቢ ለቅሶ ከተከሰተ የለቀስተኛው ቤት አንድ ዙር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በመስጠት የእንሰት ምርት እንዲሰበሰብ ይደረጋል።

ከዚህ በተጨማሪ ሌሎች ማህበራዊ ጉዳዮች ሲገጥሙ የመረዳዳት ባህላዊ እሴቶች ጎልቶ ይታያል።
ይህ ውብ ባህላዊ እሴት ሲከወን የተለያዩ ባህላዊ ጨዋታዎች ይዜማሉ ከነዚህም ውስጥ ዋይ ወቶ ተጠቃሽ ነው ።

በጣም ደስ የሚል ውሎ ከእናቶቼ ጋር

==================

ራስን መሆን ማንነትን መምሰል ምንኛ ደስ ይላል በጣም ደስ የሚል ውሎ ከእናቶቼ ጋር ❤️????????#ጉራጌነት ማንም ያልሰጠን ፤ማንም የማይወስድብን ማንነታችን ነው ???????????????? #ጉራጌነት_ይለምልም
በጉራጌ ማህበረሰብ ውስጥ ብዙ የማይጠገቡ ተነግሮ የማያልቁ እሴቶች እና ባህሎች አሉ ።
እንደምታውቁት የጉራጌ እናቶች ልክ ጥቅምት ወር እንደገባ የሰፈር እናቶች ተሰብስበው በህብረት በወኔ በአንድነት ፤በተባበር #እንሰታቸው ይፍቃሉ እኔም ከጀግና ከታታሪ እጅግ ፍቅራቸው ከማይጠገቡ #እናቶቼ ጋር ቀኑ ሙሉ አሳለፍኩ
ከእናቶቼ ጋር ከተነሳኋቸው ፎቶዎች መሀል ????????

ሀይማኖታዊ የመስብ ሰፍራዎች

======================

ሀይማኖታዊ የመስብ ሰፍራዎች ከእምነት አስተምሮ በተጨማራ የስራ ባህልን በማዳበር በልማቱ ግንባሮ ቀደሚ ሚና በመጫወት የኑሮ ውድነት ማሸነፍ እንደሚገባ ብፁዕ አቡነ መልከፄዴቅ ሳልሳይ የጉራጌ ሀገር ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ዜና ማርቆስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ሀላፊ አሳሰቡ ።

የጉራጌ ሀገረ ስብከት ፅ/ቤት የየወረዳ የቤተክህነት ስራአስኪያጆችና የሀገረ ስብከት ሰራተኞች  በእዣ ወረዳ በሚገኙ አድባራትና ከዳማት የልማት ስራ ጉብኝት  ተካሂዷል ።

በዛሬው እለት  በደረሬ ደብረ ብስራት ቅ/ገብርኤል “ገዳም ወደብር   ፡ በአትርፎ ደብረወርቅ ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድራል እና የገጨ ቅዱስ ሩፋኤል ገዳም ውስጥ የተሰሩ የተለያዩ የልማት ስራዎች ተጎብኝተዋል።

በእለቱ የተገኙት እንግዶች በጉብኝቱ እጅግ አስተማሪ የልማት ስራዎች የተሰሩ እንደተመለከቱ  በመናገር በቀጣይ በያሉበት ወረዳ ተሞክሮን ለማስፋት ጥረት እንደሚያደረርጉ ተናግረዋል ።

======================

በጉራጌ ዞን በእዣ ወረዳ አገና ከተማ ኑር መስጅድ የእዣ ሊቃ አከባበር ላይ የሀይማኖት አባቶች ባህላዊ የተዛቡ አመለካከቶች እዲጠፉ ዱ አድርገዋል፡፡ የሀይማኖት ተቋማት በፀሉት ወይንም በዱአ የሀገር ሰላምና አንድነት እንዲመጣ ሚናቸው የጎላ ነው ።ይህም ፕሮግራም ለሀገርና ለህዝቡ ሰላምና ፍቅር እንዲሁም አብሮነትን እንዲሰፍን የሀይማኖት አባቶች ዱዓ እያደረሱ ይገኛሉ ።

ጀፎረ”/ጀፎሮ/:- የጉራጌዎች ውብ ስፍራ

*****================*******

ጀፎረ”/ጀፎሮ/:- የጉራጌዎች ውብ ስፍራ

ጀፎረ ውብ፣ ፅዱና ማራኪ በአባቶች ባህላዊ እውቀትና ጥበብ የተከሸነ ሰፊ አረንጓዴ ጎዳና፤ በግራና በቀኙ በልምላሜያቸው ተውበው በሚታዩ እፀዋቶች የታጠረ፤ ሳቢና ማራኪ በሆኑ በባህላዊ እደ ጥበብ በተሽቆጠቆጡ ቤቶች የታጀበ፤ በየመሃሉ ላይ እንደ ሊባኖስ ዝግባ የገዘፉ ዛፎች ያሉት፣ ወደ መንደሩ ለሚገባ ሁሉ ለአይምሮ እፎይታን፣ ለነፍስ ደግሞ እርካታን የሚያጎናፅፍ የጉራጌዎች ልዩ ስፍራ ነው።

ጀፎረ በጉራጌ ማህረሰብ ዘንድ ልዩ ታሪክ እንዳለው ይነገርለታል። ጀፎሮ አገልግሎቱ ሁለገብ ነው። ለመንደሮች ውበት መላበስ ጉልህ አስተዋፅኦ ያበረክታል።

ጀፎረ ማለት የመንደር ወይም የጎጥ ነዋሪዎች የጋራ መጠቀሚያ፣ መተላለፊያ፣ መግቢያ እና መውጫ፣ ሰፊ መሰብሰቢያ፣ ጠዋት ከብቶች ከመሰማራታቸው በፊት ማታ ደግሞ ወደ ቤታቸው ከመግባታቸው በፊት ለማቆሚያነት የሚያገለግል የጋራ ስፍራ ማለት ነው።

ጀፎረ የጎኑ ስፋት 100-150 ሜትር፣ ርዝመቱ በመሃል የሚያልፍ ገደል፣ ደን፣ ወንዝ እስከሌለ ድረስ ሳይቋርጥ ይቀጥላል። ከጥንት ጊዜ ጀምሮ የሚለካው በዘፈቀደ ሳይሆን በባህሉ በተመረጡ አባቶች ወይም “የዥር ዳነ” የመሬት ልኬት ዳኞች አማካኝነት መሆኑን የዘርፉ አጥኚዎች ይናገራሉ።

የጉራጌ ማህበረሰብ ለጀፎሮ ትልቅ ትኩረት ከመስጠቱ የተነሳ ጀፎሮ ላይ የተተከለ የዛፍ ቅርንጫፍ፣ አፈር ወይም ሌሎችንም ነገሮች ይዞ ወደ ግል ቤት ማስገባት ክልክል ነው።

ጀፎሮ በርካታ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳዎች አሉት። የተወሰኑትን ለመጥቀስ ያክል:- ሰው ሲሞት የለቅሶ ስነስርዓት ይከወንበታል፤ ሰርግ ሲኖር የሙሽሪትና የሙሽራው አጃቢዎችና ዘመዶች በባህላዊ ዘፈን በማጀብ ይሞጋገሱበታል፤ ባህላዊ የእርቅ ስነስርዓት ይከናወንበታል፤ ህፃናት ይጫወቱበታል፤ በቅሎና ፈረስ ይገራበታል፤ ወጣቶች የገና ጨዋታ ይጫወቱበታል፤ ወንዶችና ሴቶች የደቦ ስራ ለመስራት ቁጭ ብለው ይመካከሩበታል፤ በመስቀል በዓል አዛውንቶች፣ ጎልማሶች እና ወጣቶች በደመራው ስነስርዓት ላይ ተሰብስበው ይመራረቁበታል፤ አባቶች  ባርጩማቸውን ይዘው በመውጣት ንፁህ አየር ይቀበሉበታል።

ጀፎረ ለከብቶች መዋያነትም ያገለግላል። በተለይ በክረምት ወራት ከሰኔ እስከ መስከረም የግርጌ ሳር ከከብቶች መብልነት አልፎ ለቤት ክዳን መክደኛነት እስኪደርስ ድረስ እንደማስተንፈሻ ግልጋሎት መሰጠት ሌለኛው የጀፎሮ ተጨማሪ ጠቀሜታው ነው።

በጉራጌ ብሄረሰብ እያንዳንዱ የመንደሩ ነዋሪ ጀፎሮን የመጠበቅና የመንከባከብ ኃላፊነት አለበት። የመንደሩ ማህበረሰብ በዘመቻ መልክ በመውጣት በባለቤትነት ስሜት ጀፎሮን ያፀዳል።

የጀፎሮ መኖር ለእንሰት ተክል እድገት፣ ለቡናና ለሌሎች የጓሮ አትክልት ጉልህ አስተዋጽኦ አለው። በተለይም ከብቶች ጀፎሮ ላይ ስለሚሰማሩ እነዚህ የጓሮ አትክልቶች በከብቶች እንዳይበሉ ያደርጋል።

በመሆኑም ጀፎሮ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎች እንዳሉት በመረዳት በተለይ ወጣቱ አባቶች ጠብቀው ያቆዩልንን ሀብታችንን በመንከባከብ የሚጠበቅብንን ኃላፊነት በመወጣት እንዲህ አይነቱን ውብ ባህላችንን እንጠብቅ መልዕክታችን ነው።

ይወደረ

====================

ይወደረ
የጉራጌ ብሄር የፈጠራ ባለቤትነት መብት በማረጋገጥ በዘርፉ ለተሰማሩ አካላት የገቢ አቅም ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን የጉራጌ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ አስታወቀ፡፡
አምራቾች ይበልጥ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የገበያ ትስስር እንዲፈጠርላቸው መንግስት የበኩሉን አስተዋጽኦ ሊያበረክት ይገባል ሲሉ በዘርፉ የተሰማሩ አምራቾች ጠየቁ።
የጉራጌ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ መሰረት አመርጋ በእዣ ወረዳ ጉየና የሰዎ ቀበሌ በይወደረ ስራ ላይ የተሰማሩ ሴቶች በጎበኙበት ወቅት እንደተናሩት የጉራጌ ብሔር ከሚታወቅባቸው ሀገር በቀል እውቀቶች አንዱ የጋራ ማዕድ ማቅረቢያ ይወደረ ሲሆን እውቀቱ ተጠብቆ ከትውልድ ትውልድ እየተሸጋገረ መምጣቱን ማሳያ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
“ይወደረ” አንድነትና ፍቅርን የሚሰብክ፣ አብሮነትና መተሳሰብን የሚገልጽ ማዕድ በጋራ የሚቋደስበት ሲሆን በመስቀልና በአረፋ እንዲሁም በሰርግና ድግስ ወቅት በስፋት ጥቅም ላይ ይውላል።
ከዚህም ባለፈ የተከበረ እንግዳ ሲገባ ማዕድ ማቅረቢያ በመሆኑ አሰራሩንም ማስተዋወቅ እንደሚገባና በጉራጌ ባህል ልብስ ውስጥ መንጸባረቁ ለምን እንደሆነ ማስገንዘብ እንደሚጠበቅም አስታውቀዋል፡፡
ይወደረን በሚሰራበት ጊዜ ውበቱን ለመጠበቅ የሚጨመሩ ተግባራት -ማህበረሰባዊ ፍልስፍና እንዳላቸውም ወ/ሮ መሰረት ገልጸዋል፡፡
ይወደረ በሚሰራበት ወቅት በጋራ መሆኑና ተግባሩም በትውልድ ቅብብሎሽ እየተሸጋገረ መምጣቱን የገለጹት ኃላፊዋ ይወደረ ከገጠር አልፎ በከተሞች በተለይም በሆቴሎች ጭምር ተፈላጊነቱ በመጨመሩ አዲሱ ትውልድ በዘርፉ በማሳተፍ የገቢ ማስገኛም እንዲሆን ይሰራል ብለዋል፡፡
ይወደረ በጉራጌ ብሄር ያለውን አስተዋጽኦ በማስገንዘብ የፈጠራ ባለቤትነት መብት በማስጠበቅ ተመሳስለው ከሚሰሩ ምርቶችና ሌሎችም ቅሬታዎችን ቀድሞ ለመከላከል እየተሰራ መሆኑን ኃላፊዋ ተናግረዋል፡፡
የእዣ ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ የሺነሽ ተካ በበኩላቸው በእደ ጥበብ ውጤት ለተሰማሩ አካላት የተለያዩ ድጋፎች እየተደረጉ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የገበያ ትስስር በመፍጠር ስራዎችን የማስተዋወቅ ተግባር እንደሚከናወንም ገልጸዋል፡፡
በእዣ ወረዳ ጉየነሰ የሰየ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት ወጣት ግጥም ብርሃኑና እናቷ በይወደረ ስራ ተሰማርተው ኑሯቸው እየመሩ እንደሚገኙ ነግረውናል።
ወጣት ግጥም ከእናቷ ያገኘችውን እውቀት በመጠቀም ጥራት ያለው ውብና ማራኪ ይወደረ በመሰራት ለገበያ የምታቀርብ ሲሆን በምታገኘው ገቢ ቤተሰቦቿን እየረዳች መሆኗን ተናግራለች።
እናቶች እውቀታቸውን ለተተኪው ትውልድ በማሸጋገር ተጠቃሚ እንዲሆኑ እንዳስቻላቸው ተናግረዋል፡፡
የ”ይወደረ” ግብዓቶችን በጥንቃቄ በማዘጋጀት ይወደረ ሰርተው ለገበያ እንደሚያቀርቡ የተናገሩ ሲሆን ምርቶቻቸው በሚፈለገው ጊዜና መጠን መሸጥ እንዲችሉ በመንግስት በኩል የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸውም ገልጸዋል፡፡

Koter Gedra Forest

 

The Koter Gedra Forest is located in the kebele, which has a special name called Koter Gedra, in Edja District, and is located 52 km from the main town of the zone (Wolkite) and 10 km to the east of the district capital Agna. Kekere Gedra kebele and forest got its name from the Gedra /Asta/ bush that covered the area at that time. At present, the total area of Kore Gedra forest is 320 ha and it is free from any kind of contact. In addition to Habesha Tsed, there are occasional Kosona cedars in this forest. The dense forest of Kore Gedra seems to have been pruned by an expert to the extent that nature itself has pruned it for the special beauty and magnificence of the area. It is known that the Koter Gedra Forest has been discovered as a historical attraction in 2003, and 10 different caves containing many religious relics, which are said to be from the 6th century, have been discovered.

Woizera Forest

 

Woizera forest is located in the Kebele of Ezha district, 11 km from the capital of the district, Agena, and 53 km from the capital of the zone, Wolkite.