==================

==================

=====================

===================

=========================================

===================================
ጥቅምት 17/2016 ዓም
በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ የፈጠራ ሥራዎችን በማበረታታት ተማሪዎች የማህበረሰቡ ችግር ፈቺ እንዲሆኑ መስራት እንደሚገባ በጉራጌ ዞን የእዣ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት ገለፀ ።
የእዣ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት እና የወረዳው ትምህርት ፅ/ቤት በጋራ የተዘጋጀ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ስራዎች ድጋፍ ክትትል አቅም ግምባታ ፡ የ2015 ዓም አፈፃፀም እና የ2016 ዓም ማጠናከሪያ ፡ በሳይንስ ክበባት እንዲሁም በአእምሮ ንብረት ጥበቃ ዙሪያ ለባለ ድርሻ አካላት ስልጠና ሰጥቷል ።
በእለቱም የእዣ ወረዳ ም/ አስተዳዳሪና የትምህርት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ተጠምቀ በርጋ እንደገለፁት ቴክኖሎጂን በመዘርጋትና በማስፋፋት በህብረተሰቡ ውስጥ የዘመናዊ ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ክፍተት ማጥበብ ያስፈልጋል ።
ለዚህም ትልቅ እድል ሚፈጥረው በትምህርት ተቋማት ተማሪዎች በንድፈ ሀሳብ ያገኙትን እውቀት ተግባራዊ ማድረግ የሚቻሉባቸው በቂና ምቹ የሆነ ምህዳር መፍጠር እንደሚገባም ሀላፊው ጨምረው ገልፀዋል ።
የፈጠራ ስራዎችን በትምህርት ቤት ደረጃ በስፋት እንዲተገበሩ መደገፍና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት መስራት አስፈላጊ እንደሆነ የገለፁት አቶ ተጠምቀ በተቋማት በዘርፉ እየተስተዋለ ያለውን የግብዓትና ሌሎችም ክፍተቶች ለመቅረፍ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን መወጣት እንዳለባቸውም አመላክተዋል ።
የእዣ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት ሀላፊ ወ/ሪት ራሂማ ሙክታጅ በበኩላቸው በቀጣይ ለሚደረገው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ኤግዚብሽን ውድድር ላይ ዝንባሌ ያላቸውን ተማሪውች የፈጠራ ስራቸው ከወዲሁ እንዲያዘጋጁና ከወረዳው አልፎ በዘርፉ በሚኖሩ ኤግዚብሽንና የባዛር ውድድሮች እንዲሳተፉ በማቀድ ከአሁኑ የተቀናጀ ስራ ሊሰራ ይገባል ብለዋል።
የፈጠራ ስራዎችን በትምህርት ቤት ደረጃ በስፋት እንዲተገበሩ ፅ/ቤቱ አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ያሉት ሀላፊዋ በተለይም በትምህርት ቤቶች የተለያዩ ፈጠራ ስራዎችን የሚሰሩ ተማሪዎችን በማበረታታት ሀገራችን ኢትዮጵያ በተክኖሎጂ ዘርፍ ውጤታማ እንድትሆን ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ ጨምረው ገልፀዋል ።
በጉራጌ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ የፈጠራ ስራዎች ድጋፍ ክትትልና አቅም ግንባታ ዳይሮክቴሬት ዳይሬክተር ታሪኩ ንዳ እንደገለፁት ሳይንስና ቴክኖሎጂ ለሁሉለንተናዊ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ወሳኝ እንደሆነ በመገንዘብ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ውጤቶችን ለማሳደግ በተለይም የትምህርት ተቋማት ከፍተኛ ሀላፊነት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል ፡፡
በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ የፈጠራ ሥራዎችን በማበረታታት ተማሪዎች ችግር ፈቺ እንዲሆኑ የወረዳው ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት እየሰራ ያለው ተግባራት ለሌሎችም ተሞክሮም ጭምር የሚችል በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል ይገባል ብለዋል።
በመድረኩ የተሳተፉት ባለድርሻ አካላት በሰጡት አስተያየትም ተቋሙ እያደረገው ያለው እንቅስቃሴ የሚደነቅ መሆኑን ጠቁመው አሁንም እስከ ትምህርት ተቋማት ድረስ በመውረድ እያከናወነው ያለው ተግባር አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም ተናግረዋል ።
በእለቱም በተቋሙ በ2015ዓም በጀት ዓም ጥሩ አፈፃፀም ያላቸው ከ1- 3 የወጡ ባለሙያዎች የማበረታቻ ሽልማት ተሰጥቷል ሲል የዘገበው የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው ።

======================
ሀይማኖታዊ የመስብ ሰፍራዎች ከእምነት አስተምሮ በተጨማራ የስራ ባህልን በማዳበር በልማቱ ግንባሮ ቀደሚ ሚና በመጫወት የኑሮ ውድነት ማሸነፍ እንደሚገባ ብፁዕ አቡነ መልከፄዴቅ ሳልሳይ የጉራጌ ሀገር ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ዜና ማርቆስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ሀላፊ አሳሰቡ ።
የጉራጌ ሀገረ ስብከት ፅ/ቤት የየወረዳ የቤተክህነት ስራአስኪያጆችና የሀገረ ስብከት ሰራተኞች በእዣ ወረዳ በሚገኙ አድባራትና ከዳማት የልማት ስራ ጉብኝት ተካሂዷል ።
በዛሬው እለት በደረሬ ደብረ ብስራት ቅ/ገብርኤል “ገዳም ወደብር ፡ በአትርፎ ደብረወርቅ ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድራል እና የገጨ ቅዱስ ሩፋኤል ገዳም ውስጥ የተሰሩ የተለያዩ የልማት ስራዎች ተጎብኝተዋል።
በእለቱ የተገኙት እንግዶች በጉብኝቱ እጅግ አስተማሪ የልማት ስራዎች የተሰሩ እንደተመለከቱ በመናገር በቀጣይ በያሉበት ወረዳ ተሞክሮን ለማስፋት ጥረት እንደሚያደረርጉ ተናግረዋል ።

======================
በጉራጌ ዞን በእዣ ወረዳ አገና ከተማ ኑር መስጅድ የእዣ ሊቃ አከባበር ላይ የሀይማኖት አባቶች ባህላዊ የተዛቡ አመለካከቶች እዲጠፉ ዱ አድርገዋል፡፡ የሀይማኖት ተቋማት በፀሉት ወይንም በዱአ የሀገር ሰላምና አንድነት እንዲመጣ ሚናቸው የጎላ ነው ።ይህም ፕሮግራም ለሀገርና ለህዝቡ ሰላምና ፍቅር እንዲሁም አብሮነትን እንዲሰፍን የሀይማኖት አባቶች ዱዓ እያደረሱ ይገኛሉ ።

=========
ህዳር 3/2016
በማናቸውም የሰለጠኑ ሀገራት ለስልጣኔያቸው መረት የሆነው የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ዘርፍ ላያ የፈሩ ባለሙሉ ክህሎት፤ዕውቀትና አስተሳሰብ ያላቸው አምራች ዜጎች መሆናቸው አያጠያይቅም።ዛሬም ሀገራችን ወደ ያደጉ ሀገራት ተርታ ለመሰለፍ በምታደርገው ጥረት በተለያዩ ኢንደስትሪዎች የሚፈለገውን የሰለጠነ የሰው ሀይል ምንጩ ይህንኑ ዘርፍ እንደመሆኑ መጠን የአገና ኮንስትራክሽንና ኢንደስትሪያል ኮሌጅ ዘርፉ የሚፈልገውን ብቁና የሰለጠነ የሰው ሀይል ለማፍራት የሚያስችል ቅድመዝግጅት በማጠናቀቅ ሰልጣኞች በመቀበል ላይ ይገኛል።በወረዳችንና በከተማችን ውስጥ እየተስፋፉ የሚገኙ የተለያዩ ኢንቨስትመንቶችና ሌሎች ከፍተኛ የሰው ሀይል የሚፈልጉ ተቋማት ፍላጎትና የወቅቱ የስራ ገበያ ጥናት መነሻ በማድረግ በሚከተሉት ሙያዎች ላይ 12ኛ ክፍል ያጠናቀቁ ተማሪዎች እስከ ህዳር 14/2016 ድረስ እየመዘገብን ስለሆንን ያለምንም ጊዜ ብክነት በአጭር ጊዜ ውስጥ የሙያ ባለቤት በመሆኑ የስራ ዕድል ተጠቃሚ ይሁኑ ይላል የአገና ኮንስትራክሽንና ኢንደስትሪያል ኮሌጅ!!

==================================
ጋበር የእዣው ነፃ ኣውጪ
*****
የእዣን ህብረተሰብ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ለመቅረፍ ነሐሴ 17ቀን 2014ዓም በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን
ተመዝግቦ የተመሰረተው ጋበር የበጎ አድራጎት ማህበር ቅደሜ ህዳር 01ቀን 2016ዓም በወረዳው በሚገኙ ሁሉም ቀበሌዎች ለብርቱ
ጉዳይ ቀጠሮ ይዟል።
‘የጉራጌን ማህበረሰብ ማህበራዊ መሰረቶች መሸርሸር ፤ኣሳሣቢነቱና የመውጫው መንገድ’’ የሚል ፅሁፍ በሁሉም ቀበሌ ከሚገኙ
ከሁሉም እድሜና ፆታ የተውጣጡ ነዋሪዎች ጋር ውይይትና ምክክር ያደርጋል።በዚሁ ጉዳይ ላይ ሠፊ ውይይት እና ምክክር ተደርጎና
ከህብረተሰቡ የቀረቡትን የመፍትሄ ሀሳቦች ላይ የጋራ ግንዛቤ በመጨበጥ ጋበር ከወረዳችን የመንግስት አመራር ፡ከአገር ቤት ነዋሪው እና
ከከተማና ከአገር ውጭ ከሚኖሩ የእዣ ተወላጆች እና ወዳጆች ጋር በመመካከር ችግሮችን ደረጃ በደረጃ ለመፍታት የሚቀየስ ይሆናል።
የተቀየሱት ከችግር መውጫ መንገዶች የጋበርና የተወላጁ የቤት ስራ ሆኖ የሚሰራ ይሆናል።
ጋበር ቅዳሜ ህዳር 01 ቀን 2016ዓም በሁሉም የእዣ ወረዳ ቀበሌዎች ይጠበቃል።
ብዙ ኣይነት ጉዞ ወደ ትውልድ ቀዬ ተደርጎ ያውቅ ይሆናል።ለመስቀል ለአረፋ እንዲሁም ለዓመታዊ ክብረ በዓልና ለለቅሶም ጭምር።
እነዚህ ጉዞዎች ዓላማቸው የተለያየ ስለሆነ ከዚህኛው የጋበር ጉዞ በእጅጉ ይለያሉ።
ለምሳሌ የመስቀልና የአረፋ በዓል ለማክበር የሚደረገው ጉዞ ፉክክር የበዛበት ከእኛ ይልቅ እኔ የሚጎላበት ሲያልፍም ኢኮኖሚያዊ አቅም
ማሳያ(በተለይ የስጋ ከብት ግዢ በሚፈፀምበት ጊዜ) ነው።
የአሁኑ የጋበር ‘ቅዱስ ጉባዔ’ ከእኔ ወደ እኛ እየተቀየረ ያለ ጉዞ ነው። አንጋፋ የልማት ኣባቶች ለወጣቶች ልምድ የሚያካፍሉበት የተማሩና
የተመራመሩት አንጋፋ ምሁራን ለወጣቶች የአገር ፍቅርና ለወጡበት ማህበረሰብ ማገልገልን/አለማገልገልን እንደሚያስቆጭ/ እንዲሁም
ከምንም በመነሳት በጥረትና በትጋት ከሀብት ማማ ላይ ከሚገኙት ባለሀብቶቻችን በመስጠት የሚገኘው ደስታና ዝቅ ብሎ ገንዘብንም
ጊዜም ጉልበትም መስጠት የሚሰጠው ስሜት ለታዳጊ እና ወጣቶች ተግባራዊ የበጎነት ስልጠና የሚሰጥበት ጉባኤ ነው። ወላጆች ደግሞ
ይህን ጅምር በማየታቸው ሀሴት በማድረግ የጎደለው ክፍተት እንዲሟላ ተንከባክበውና አስተምረው ያሳደጉትን ልጃቸው ባለሀብትና
ምሁር ልጃቸው ‘’ምር ይፈዝ ምር ይብስ’’ ለማለት ነውና ህዳር አንድ ለጋበር ጠንሳሾች አደራጆች ደጋፊዎች እና አባላት የስኬት መሰረት
የሚጣልበት የጋበር ራዕይ ላም አለኝ በሰማይ ሳይሆን የሚታይና የሚጨበጥ እንደሆነ ማሳያ ታሪካዊ ቀን ነው።የትውልድ አካባቢን
እንደዚህ ለማገልገል መብቃት መታደል ነው።
ጋበር እንደ 5G
ጋበር የጉራጌን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮች ለመቅረፍ የሙከራ ስርጭቱን ከእዣ ጀምሯል።
ጋበር በትምህርት በጤና እና በግብርናው ዘርፍ ዕምርታዊ ለውጥ በማምጣት ጉራጌን ከርሀብና ከኋላቀርነት ነፃ ለመውጣት ትክክለኛው መንገድ ነው።

=============================================================

ነሀሴ 29/2015 ዓም
=============================================
በየደረጃው የሚነሱት የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመፍታት በእቅድ መምራት እንደሚገባ ተገለፀ ።
በጉራጌ ዞን የእዣ ወረዳ አመራሮች በ100 ቀናት ውስጥ የሚፈፀሙ በመንግስትና በፓርቲ ሊሰሩ የሚገቡ ተግባራቶች ዕቅድ ላይ ውይይት አደረጉ ።
በእለቱም የእዣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘውዱ ዱላ እንደገለፁት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ በአዲስ መልክ ተደራጅቶ ወደ ስራ መገባቱን ተከትሎ በቀጣይ ለሚከናወኑ ተግባራቶች በየደረጃው ባሉ መዋቅሮች የ100 ቀናት እቅድ ታቅድ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ።
በየደረጃው የሚነሱት የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመፍታት በእቅድ መምራት እንደሚገባ የገለፁት ዋና አስተዳዳሪው በአዲሱ ክልልም መደበኛና ወቅታዊ ስራዎች በብቃት ተመርተው የሽግግር ጊዜው ውጤታማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ እና እንደ ወረዳው ልማቶች እንዲፋጠኑ በተለይም አመራሩ በትጋት መስራት ይጠበቅበታል ብለዋል።
ነሀሴ 29/2015 ዓ.ም

በቀጣይ 100 ቀናት እያንዳንዱ ተግባር በአደረጃጀት እና በተግባር እንዲፈፀሙ ማድረግ ያስፈልጋል ያሉት አቶ ዘውዱ በተለይም እንደ ወረዳው በመኸር ሰብል ልማት አርሶአደሩን በመደገፍ ምርታማነት እንዲጨምር በመደገፍ ፡ በትምህርት በስራእድል ፈጠራ ፡ በየአካባቢው ሰላማና ደህንነት እና በሌሎችም ጉዳዮች ትኩረት ሰጥቶ መስራት ይጠበቃልም ብለዋል።
የእዣ ወረዳ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ተሾመ ስራኒ በበኩላቸው የህዝብ ጥያቄ በፓርቲው ምላሽ መሰጠቱ እንደ ምቹ አጋጣሚ በመጠቀም አመራሩ በተጠናከረ መንገድ አንድነትን ማጠናከርና ልማትና ማፋጠን ላይ ከሌላ ጊዜ በተሻለ ሁኔታ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ይገባዋል ብለዋል ።
የቀጣይ በዓል መሰረት ተደርጎ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ስራ ማጠናከር አለበት ያሉት ዋና የመንግስት ተጠሪው ይህም ማሳካት ሚቻለው የመንግስትና የፓርቲ አደረጃጀቶች በማጠናከር ውጤታማ ስራ ሲሰራ እንደሆነም አመላክተዋል ።
እያንዳንዱ የሚፈፀሙ ስራዎች በፓርቲው መርህ ተከትሎ መስራት እንደሚገ ጨምረው የገለፁት አቶ ተሾመ በየተቋማት የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ ስርዓት በማሻሻል አንገብጋቢ የህዝብ ችግሮች ለመፍታት ጥረት ማድረግ ያስፈልጋልም ብለዋል።
በመድረኩ ክልላዊ ፡ ዞናዊና ወረዳዊ ወቅታዊ የሆኑ ጉዳዮች ላይና የቀጣይ 100 ቀን ላይ ትኩረት ያደረገ ሰነድ ቀርቦ ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን እንደ ወረዳው በሁሉም መስኮች መሰራት የሚገባቸው ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሶ መድረኩ ተጠናቋል ሲል የዘገበው የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው ።

©2023. የእዣ ወረዳ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት ከአገና ኮንስትራክሽን እና ኢደስትሪያል ኮሌጅ ጋር በመተባበር. All Rights Reserved.